#ተውበት (#ጸጸት)
#ክፍል_1
ዑለሞች (ሙስሊም ምሁራን) እንደሚሉት፦ ከየትኛውም ኃጢአት መጸጸት (ተውበት) ግዴታ (ዋጂብ) ነው። የተፈፀመው ወንጀል በአላህና በሰውየው መካከል ብቻ ተወስኖ የሚቀርና ከሰው መብት (ሐቅ) ጋር ያልተነካካ ከሆነ ከእንዲህ ዓይነቱ ወንጀል ለመቶበት ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች (ሸርጦች) መሟላት አለባቸው፦
1/ ሰውየው ወንጀሉን ማቆም አለበት።
2/ ለሠራው ኃጢአት፥ ለፈፀመው ጥፋት መቆጨት ይኖርበታል።
3/ ወደፊት እንዲህ ዓይነቱን ኃጢአት ዳግም ላለመፈፀም ቁርጥ ውሳኔ ማድረግ ይጠበቅበታል።
ከነኝህ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ከጎደለ ተውበቱ ተቀባይነት የለውም። ወንጀሉ ከሰዎች መብት (ሐቅ) ጋር የተያያዘ ከሆነ ደግሞ ለተውበት አራት ሸርጦች መሟላት አለባቸው። ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱና ከሰውየው ሐቅ መጽዳት። ገንዘብ ወይም መሰል ነገር ከሆነ ይመልስለታል። በዝሙት ወይም በሐሜት ስሙን አጥፍቶ ከሆነ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል፥ ወይም ይቅርታውን ይጠይቃል.... አንድ ሰው ከሁሉም ኃጢአቶቹ የመቶበት ግዴታ አለበት። ከከፊሉ ብቻ ከቶበተም ከዚያ ኃጢአት መመለሱ ተቀባይነት ይኖረዋል። ሌሎች ወንጀሎች እንዳሉ ይቀራሉ። ተውበት ዋጂብ መሆኑን አያሌ የቁርኣን አንቀጾችና የሐዲሥ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የዑለሞች ስምምነትም (ኢጅማዕ) ይህንኑ ያጸድቃል።
አላህ እንዲህ ብሏል፦
\"ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት። ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ።\" (ሁድ፡ 3)
#ሐዲሥ 2 / 13
የአላህ መልዕክተኛ ተከታዩን ሲናገሩ አድምጫለሁ በማለት አቡ ሁረይራ አስተላልፈዋል፦ \"እኔ በየቀኑ ከሰባ ጊዜ በላይ አላህን ምሕረቱን እማጸናለሁ፤ ወደርሱም እመለሳለሁ።\" (ቡኻሪና ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ መልዕክተኛው ከወንጀል የተጠበቁና ከሰው ሁሉ በላጭ፥ እንዲሁም አላህ ጥቃቅን ግድፈታቸውን ሁሉ የማራቸው ከመሆናቸው ጋር በየቀኑ ከሰባ ባለነሰ ጊዜ አላህን ምሕረት ይለምናሉ፤ ወደርሱም በጸጸት ይመለሳሉ። ይህም በሙስሊሙ ኅበረተሰብ ላይ የተውበት ስሜት እንዲዳብር ግፊት ለማሳደር የተደረገ ነው።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1