5 days Translate
Translation is not possible.

#ቅንነትና_ታማኝነት (#ኢኽላስ) #እንዲሁም_መልካም_ተነሳሽነት (#ኒይያህ)፤ #በማንኛውም_ንግግርና_ተግባር #ግልጽ_ይሁን_ድብቅ

#ክፍል_12

#ሐዲሥ 1 / 12

አቡ ዐብዱረሕማን ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑ አል ኸጧብ የአላህ መልዕክተኛ ተከታዩን ሲናገሩ አድምጫለሁ በማለት አስተላልፈዋል፦ \"ከእናንተ በፊት ከነበሩ ሰዎች መካከል፥ ሦስት ሰዎች ለጉዞ ተንቀሳቀሱ። ሲመሽባቸው ለአዳር ከአንድ ዋሻ ውስጥ ገቡ። ከተራራ ላይ የነበረ አንድ ቋጥኝ ተንከባሎ ዋሻውን ዘጋባቸው። \"አላህን በመልካም ተግባራችሁ ካልለመናችሁት በቀር ከዚህ ቋጥኝ የሚያድናችሁ ነገር አይኖርም\" ተባባሉ። ከመካከላቸው አንዳቸው እንዲህ አለ፦ \"አላህ ሆይ! አዛውንት ወላጆች ነበሩኝ። እነርሱ ከመጠጣታቸው በፊት ቤተሰቤንም፥ ከብቶቼንም፥ ወተት አላጠጣም ነበር። እንጨት ለቀማ ሩቅ ቦታ ሔድኩ። እስከተኙበት ጊዜ ድረስ አልተመለስኩም። ወተታቸውንም አለብኩላቸው። ተኝተው አገኟቸው። ልቀሰቅሳቸው አልከጀልኩም። ከነርሱ በፊት ቤተሰቤንና ከብቶቼን ማጠጣትንም አልፈቀድኩም። ወተት የያዘውን ዋንጫ በእጄ እንደያዝኩ መንቃታቸውን ስጠባበቅ ጎህ እስኪቀድ ድረስ ቆየሁ። ሕጻናት ከእግሮቼ ሥር ይንጫጫሉ። ወላጆቼ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ወተታቸውን ጠጡ። አላህ ሆይ! ይህንን ድርጊት የፈፀምኩት የአንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ በዚህ ቋጥኝ ሰበብ ከደረሰብን መከራ አውጣን\" ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ። መውጣት የማያስችላቸውን ያክል። ሌላኛው ደግሞ እንዲህ አለ፦ \"የአጎት ልጅ ነበረችኝ። እጅግ አፈቅራት ነበር\" በሌላ ዘገባ እደተወሳው፦ \"አንድ ወንድ አዲትን ሴት የሚያፈቅራትን የመጨረሻው የፍቅር እርከን ያክል አፈቅራታለሁ። ለወሲባዊ ተራክቦ ጠየቅኳት። ፈቃደኛ አለሆነችም። አንድ የድርቅ ዓመት ተከሠተ። (እርዳታዬን ፍለጋ) ወደ እኔ መጣች። የምፈልገውን እንድፈጽም ቃል አስገብቼ አንድ መቶ ሃያ ዲርሃም ሰጠኋት። ቃሏን አከበረች፤ ያሻኝን መፈጸም እስክችል ድረስ።\" በሌላ ዘገባ ላይ እንደተወሳው ደግሞ፦ \"በጭኖቿ መሐል እንደገባሁ፦ \"አላህን ፍራ! ያለ አግባብ ክብረ ንጽሕናዬን አትገርስስ\" አለችኝ። ዘወር አልኩ። ምንም ነገር ሳልፈጽም። ከማንም አብልጬ እወዳታለሁ። የሰጠኋትንም ወርቅ ተውኩላት። አላህ ሆይ! ይህንን ተግባር የፈፀምኩት የአንተን ውዴታ ከጅዬ ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን።\" ቋጥኙ ትንሽ ከፈት አለ። መውጣት ግን አይችሉም። ሦስተኛው እንዲህ አለ፦ \"ሠራተኞችን ቀጠርኩ። ለሁሉም ያገልግሎት ክፍያቸውን ከፈልኳቸው፤ ከመካከላቸው አንዱ ሲቀር። ድርሻውን እኔ ዘንድ ትቶ ሔደ። ትቶት የሄደውን ገንዘብ አባዘሁለት፤ ብዙ ሃብት እስኪሆን ድረስ። ከዘመናት በኋላ ወደኔ መጣ። እንዲህም አለኝ፦ \"ዐብደላህ ሆይ! ድርሻዬን ስጠኝ\" \"ይህ የምትመለከተው ሁሉ _ግመሉም፣ ከብቱም፣ ፍየሉም፣ ባሪያውም_ ድርሻህ ነው\" አልኩት። \"ዐብደላህ ሆይ! አትቀልድብኝ\" አለኝ። \"እየቀለድኩብህን አይደለም\" አልኩት። ሁሉንም ተረክቦ እየነዳ ወሰደ። አንዳችም ነገር አልተወም። አላህ ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት ያንተን ውዴታ በመሻት ከሆነ ካለንበት መከራ አውጣን።\" ቋጥኙ ተከፈተ። ወጥተው ጓቸውን ቀጠሉ።\" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ በመከራ ሰዓትና በሌላም ወቅት ዱዓ ማድረግ፥ እንዲሁም መልካም ተግባራትን እያወሱ አላህን መማጸን ይወደዳል።

2/ ለወላጆች በጎ መዋል፥ እነርሱን ማገልገልና ከልጅ፥ ከሚስት.... ይበልጥ ለነርሱ ቅድሚያ መስጠት ጠቃሚ ተግባር ነው።

3/ ከሐራም መጠበቅ _በተለይም ማድረግ እየቻሉ ለአላህ ሲሉ ብቻ መቆጠብ_ እጅግ ድንቅ ተግባር ነው።

4/ ቃልኪዳንን መሙላትና አደራን ለባለቤቱ መመለስ፥ መልካም ማኅበራዊ ውሎ ጽድቅ ክንውኖች ይህና ሌሎችንም የቁርኣንና የሐዲሥ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

5/ በጭንቅ ሰዓት በቅንነትና ታማኝነት (ኢኽላስ) የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል።

6/ አላህ በጎ ሠሪዎችን ውለታ አያጠፋም።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group