Translation is not possible.

〽️ እንኖራለን በሀሴት

ኢንዲ ስትል ፃፈች - ያረገዘችው ብዕሬ

ለእጄ እንዳይከብደኝ - ክዳኗን ወርውሬ

እናም መፃፍ ጀመርኩ - እንዲህ ስል ጀምሬ

ግን ገንፍላለችና - ቀለሟ እንዳያልቅ

እውነቱን ላውጣው - ልቤ እንዳይጨነቅ

በሀቅ ትደሰት - ብዕሬ ትቦርቅ።

እስቲ ልሞነጫጭር - ሀሳቤን ልግለጥ

ግን አልችልም - ውብ ቃሎችን መምረጥ

አጣዳፊ ነውና - ያረገዘቺው የብዕሬ ምጥ።

የዕድሜችን ጉዞ ሽሽት

የተስፋችን ቅዠት

የመኖራችን ሚስጥር

የህይወት ቁም ነገር

የኑሮ ስንክሳር

እንጨነቃለን ይሀው - ምንም ላንፈጥር

በሆነ ጊዜና - ስትጠልቅ ጀምበር

ድቅድቁ አይሎ - ጨለማው ሲደራ

እኛም ረስተን - ሰባዓዊ ፉጥርነታችንን

ፍንትው ብሎ ወጣ - ይሀው ጭካኔያችን

ልብሳችን ሸፍኖት - ያን ትምኪት አንደበት

ስንኖር አምሮብን - ኑሮን ግን የውሸት

ሰው መች ይህን አወቀ - የእኛነታችንን እውነት

ፀሃይ ማብራት ስትጀምር - ለሰው ልጅ በተራ

ፍርድም ሲጓደል - እውነት ሲሆን ተራ

ከፋፍለን ስንጨርስ - ሰዎችን በጎራ

እናም አስተዛዘበን - የአስተሳሰባችን ስፍራ።

ጊዜም ሚስጥር ሆነ - እንደ ስልክ ኮድ

ሚከፍተውም የለም - አወይ የኛስ ጉድ

ወይስ በኮፒ እንክፈተው - በዘረፍነው ፓስዎርድ⁉️

ቀኑ ቶሎ መሸ - ለሊቱ ረዘመ

ልባችን ታመመ - እኛን እያከመ

ሀሴት መበፈለግ - ውስጣችን ከሰመ

እንቅፋት በዝቶበት - ደስታን ሚቀማ

ግራ ገብቶን አለን - በጭንቀት አላማ።

አርብን እየጠበቅን - ቅዳሜ ደረሰ

ቀናት ተፈራረቁ - ወርም ተጋመሰ

ጨለማው ረዝሞ - ብርሃን  ታመሰ

ደስታም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ

ቀኑ 24 ሰዓት - እኛ ግን ዜሮ

ማሳለፍ ለምደን - ጭንቀትን በጓሮ

ለውጥ ላናመጣ - አሰማን እሮሮ

ይሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ

ይሀውና አለን- እንደአምናው ዘንድሮ።

ደግነት ይፃፍበት - በጥላቻ ሰነድ

እውነት ይስፈርበት - በጨለማው መንገድ

እስቲ ደግ እንሁን - በቃ ሰው እንውደድ

በቃ ሰው እናክብር- ውስጣችን እንዳይናድ

ለውዴታችን ግን - ምላሽ አንጠብቅ

በሚመስጥ ትህትና - ከእውነት እንታረቅ

ተስማምተው ከሄዱ - እምነትና ተስፋ

ሃቅ ገኃድ ከወጣ - የሰው ልጅ ካልከፋ

እውነት ሚስጥር ካልሆነ - ካወጣነው ይፋ

ይሄኔማ ሰው እንሆናለን - ደግነት ያቀፈ

ሁሉም ለበጎ ይሆናል - ይጠፋል ብስጭት

መመኘት እንጀምራለን - እውነተኛ ምኞት

በደስታ ያበበ - ውብ ማራኪ ጊዜያት

እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት

እርሰበርስ ተገዳግፈን - እንኖራለን በሀሴት።

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇

Telegram: t.me/SharpSwords1

Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1

YouTube: youtube.com/@SharpSwords1

Instagram: Instagram.com/sharp_swords1

Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group