Translation is not possible.

#አንድን_ግለሰብ_ለይቶ #ወይም #እንስሳን_መርገም_ስለመከልከሉ

#ክፍል_6

#ሐዲሥ 264 / 1556

አቡ ደርዳእ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው አንድን ነገር በሚረግም ጊዜ እርግማኑን ወደ ሰማይ ትወጣለች። የሰማይ በሮች ይዘጉባታል። ወደ ምድር ትወርዳለች። የምድር በሮች ይዘጉባታል። ከዚያም ቀኝና ግራ ትዞርና መግቢያ ካላገኘች ወደ ተረገመው አካል ትመለሳለች። ለእርግማኑ ተገቢ ሆኖ ካገኘችው ታርፍበታለች። ካለበለዚያ ወደ ረጋሚው ትመለሳለች።" (አቡ ዳውድ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ እርግማን ጥንቃቄ የሚሻ ነገር ነው። ምክንያቱም የምንረግመው ሰው ለእርግማኑ ተገቢ ያልሆነ ከሆነ እርግማኑ ረጋሚውን ራሱን መልሶ ይጎዳዋል።

2/ ስለዚህም አንድን ሰው ለይቶ መርገም አደጋ እንዳለው ዓሊሞች ይናገራሉ።

3/ መርገም ካለብን ባሕሪን ወይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን በግል ሳይሆን በጥቅሉ መሆን ይኖርበታል። ለምሳሌ፦ "ዋሾዎች የአላህ እርግማን ይውረድባቸው። በከሐዲያን ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ" ማለት ይቻላል። አንድን ሰው ለይቶ ግን፦ "እገሌ እንዲህ ይሁን" በማለት መርገም በራስ ላይ በላእ ሊያመጣ ይችላል።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group