ግን እስከ መቼ⁉️
============
(እስከ መቼ የንጹሐን ደም በጽንፈኞች እየፈሰሰ ይቀጥላል? እስከ መቼ ሰው በሰፈሩ በስጋት ይኖራል?)
||
✍ ሎሚ ሜዳ አካባቢ የሚገኘውን የዓሊ መስጅድ ጉዳይ መጅሊስ ይዞታል ስለተባለና ጉዳዩን ወደ ሚዲያ በማውጣት የበለጠ ልዩነት እንዳይሰፋና የጠላት መሳለቂያ እንዳንሆን በሚል በተደጋጋሚ ዝምታን መርጨ ነበር።
ግና የሰዎች እነዚህ ንጹሐን ሙስሊሞችን «ውሃብያ» የሚል ታፔላ ለጥፈው የሚያከፍሩና ደማቸውን ሐላል ያደረጉ የአሕባሽና በነርሱ የተጠለፉ የጥመት አንጃዎች፤ ከሙስሊሙ አንድነት ይልቅ ክፍፍሉን፣ ከከፍታው ይልቅ ዝቅታውን፣ ከጥንካሬው ይልቅ ድክመቱን፣ ከስልጣኔው ይልቅ ኋላ ቀርነቱን… የሚሹ ናቸውና ዛሬም እንደተለመደው ከጠሮ፣ በኒ፣ ከአንዋርና መሰል ከሚታወቁባቸው ሰፈሮች ተጠራርተው በየቦታው በመሄድ የተለመደውን የንጹሐን ደም ማፍሰስ አጠናክረው ቀጥለዋል።
ከአሁን በፊት በጠሮ፣ በፉል ውሃ ተውፊቅ፣ በፈላሕ መስጅድና በሌሎች መስጅዶች በሚያስነሷቸው ሁከቶች የሚታወቁት እነዚህ ስብስቦች፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሁከት አቅጣጫው ወደ ሎሚ ሜዳው ዓሊ መስጅድ ላይ ሆኗል።
በዚህ መስጅድ ውስጥ ከበፊት ጀምሮ መስጅዱን የቆረቆሩና ሰፈሩን ያቋቋሙ የአካባቢው ሙስሊሞች ሳይቀሩ፤ የመስጂዱን ኮሚቴዎች፣ ሴቶቻቸውን ሳይቀር ከመስጅድ ባሻገር ጨለማን ተገን አድርገው መንገድ ላይ በመጠበቅና መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ደማቸውን አፍሰዋል። በዛሬው ዕለትም ከጠዋት የመስጂዱን ምንጣፍ እየቀየሩ የነበሩ ሙስሊሞችን ከየቦታው ተጠራርተው መጥተው ደማቸውን አፍሰዋል፤ መስጂዱም በጸጥታ አካላት ተከቧል።
ነገር ግን ዛቻና ሁከታቸው አሁንም በአካባቢው ካለ የጸጥታ አካል በላይ ስለሆነ ተጨማሪ ኃይል ያስፈልጋል። በነዚህ አካላት ላይ ተገቢ የሆነ ተመጣጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ፤ ሰፈሩ በየቀኑ የስጋትና የሁከት ማዕከል እንዲሆን አድርጎታል። የሚመለከተው የመንግስትና የመጅሊስ አካል ይህን ቡድን ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ እርምጃ እንዲወሰድበት በማድረግ የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ሊመልስ ይገባል።
በየአካባቢው ካሉ ተላላኪዎቻቸው ጋር በመሆን ሁከት በተነሳበት ቦታ ሁሉ አዝማች በመያዝ ነገሩን የሚያጋግሉት በጣት የሚቆጠሩና የሚታወቁ ወጣቶች ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ሰንሰለታቸው ከማኅበሩ ሰዎችና ከታላላቅ የሃገሪቱ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር ነው። የዚህን ቡድን ሰንሰለት ከነ አጋሮቹ አፈላልጎ እርምጃ በመውሰድ የአካባቢውንና አጠቃላይ የህዝበ ሙስሊሙን ሰላም ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት ነው።
በሆነ ባልሆነው የሙስሊሞችን ደም ማፍሰስ ይቁም። በፊት ከነበረው ስርዓት ጋር አብረው ያፈሰሱት ደምና ያሰደዱት ሙስሊም አንሷቸው፤ ዛሬም በሌላ መልክ ተመሳሳይ በደል ሲፈፅሙብን ዝም ልንል አይገባም።
በቃን‼
ፍትሕ ለሎሚ ሜዳ ሙስሊሞች‼
♠
Cc:
===
Addis Ababa Police
Ethiopian Federal Police
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Mayor Office of Addis Ababa
Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
ummalife.com/MuradTadesse