Translation is not possible.

ነውር ነው‼

=========

✍ በየትኛው መመዘኛ ቢሆን እኚህን አባት በዚህ ደረጃ ማመናጨቅና መደብደብ ተገቢነት የለውም። የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸው የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንጂ የህዝብን ሰላም ያውም ትልቅ አባትን በማዋረድ የውስጥ ጥላቻቸውን መወጣት አይደለም። ብልሹ ስነ ምግባራቸውን ያላስተካከሉ ሞራልና ርኅራኄ የሚባል ነገር ያልሠራባቸው ወንበዴ የፖሊስ አካላት በእንዲህ አይነት ቀና ብሎ ለማየት እንኳ በማያስደፍሩ አባቶች ላይ የሚፈፅሙት ውንድብና የጸጥታ አካሉን ስም የሚያቆሽሽ ነው።

እነዚህ ሙስሊም ሲመለከቱ በምን ሰበብ እንተናኮለው የሚሉ ሙስሊም ጠል ጽንፈኞች አስተሳሰባቸውን ካላረሙ ወይም ከምድረ ገፅ ካልጠፉ ሃገር ሰላም አትሆንም።

ይህ የፖሊስ አባል በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ተገቢው ተመጣጣኝና አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድበት ስንል በጥብቅ እንጠይቃለን።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመጅሊስ አካላትና የሚመለከታችሁ ሁሉ፤ አባታችንን በዚህ ደረጃ የደበደበውን ሞራለ ቢስ ወንበዴ የእጁን እስኪያገኝ ድረስ ለፍትሕ ልትሠሩ ይገባል።

በዚሁ አጋጣሚ የእኚህን አባት አድራሻ የሚያውቅ ካለ በውስጥ @Murad_Tadesse ላይ ያሳውቀኝ።

ይህን ቪድዮ ለሁሉም አሰራጩት።

https://vm.tiktok.com/ZM6bf6QY1/

||

t.me/MuradTadesse

fb.com/MuraadTadesse

ummalife.com/MuradTadesse

x.com/MuradTadesse

16 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group