Translation is not possible.

ለማስታወስ ያክል‼

==============

①) በየትኛውም መልኩ ቢሆን ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን ከእምነታቸው ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች መተባበር አይቻልም።

ይህ ማለት በዓላቸውን መታደም ወይም አብሮ ማክበር፣ የበዓል ግብዣቸውን መታደም፣ ከእምነታዊ በዓላቸው ጋር በቀጥታ ተያያዥ የሆኑ ቁሳቁሶችን (ለምሳሌ፦ የገና ዛፍ)… መሸጥም ሆነ ከውጭ ማስገባት ወይም ማጓጓዝ አይቻልም።

*

②) በተደጋጋሚ የሚነሳው «የእንኳን አደረሳችሁ» ጉዳይም ይታሰብበት። በፍፁም አይቻልም። እንኳን አደረሳችሁ ስንል ትክክለኛ ያልሆነውን እሳቤያቸውን ከመደገፍ ነው።

እስልምና ምንም እንኳ ሙስሊም ባይሆንም ከእምነት ነክ ነገር ውጭ ሙስሊም ያልሆነን የሰው ዘር ሁሉ ሰላማዊ ሰው እስከሆነ ድረስ እገዛችንን ሲሻ እንድንረዳውና በጥቅሉ በመልካም እንድንኗኗረው ፈቅዶልናል።

እንኳን ለሰው ልጅ ለእንስሳት ጨምር እንድናዝን የታዘዝን ሰላማዊ ህዝቦች ነን።

ባለቤቱ ከአቅሙ በላይ ሥራ ስለሚያበዛበትና ስለሚያስርበው ግመል ስሞታውን ያዳመጠ አዛኝ ነቢይ ኡመቶች ነን።

እንኳን ሌላ እንዳትሰቃይ በሚል ዓይጥን በወጥመድ መግደል በተመለከተ እንደ ኢብኑ ዑሠይሚን ያሉ ዑለማዎች ከልክለዋል።

አይደለም ነፍስ ላለው ፍጡር ቅጠል እንኳ ያለ አግባብ እንዳንቆርጥ ታዘናል። የወንዝ ውሃም ቢሆን ያለ አግባብ እንዳናባክን ታዘናል።

እኛን ስለ መቻቻልና መከባበር፣ ስለ አዛኝነትና ስለ ሰላም መስበክ ለቀባሪ ማርዳት ነው።

ሆኖም ግን ገደብ አለን። እስከምንድረስ? የሚለው ተቀምጦልናል።

ምንም ቢሆን ምንም፣ ማንም ቢሆን ማንም፣ ሙስሊም ያልሆነን አካል በእምነቱ ጉዳይ በየትኛውም መልኩ መተባበር ፈፅሞ አይቻልምና ከማስመሰልና አጉል ይሉኝታ ወጥተን እስልምናን እንኑረው።

አላሁ አዕለም!

||

t.me/MuradTadesse

fb.com/MuradTadesseOfficial

fb.com/MuradTadesseOfficialPage

ummalife.com/MuradTadesse

twitter.com/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group