لا يمكن الترجمة

እምባ የሚያመጣ ክስተት ነበር‼

=======================

✍ የሞንጎልንና የአባሲድን ታሪክ ስናነሳ አብሮ የሚመጣው ትልቁ የባጝዳድ ቤተ መጽሐፍት (بيت الحكمة - Grand Library of Baghdad) መቃጠል ነው። በነገራችን ላይ ያኔ የሞንጎል ጦር ባጝዳድን ወደ ደም ጅረት ሲቀይር በርካታ መሠረተ ልማቶቿንም አውድሞ ነበር።

እስካሁን ድረስ ብዙዎችን የሚቆጨውና ምናልባትም ፋናው አሁን እስካለንበት ድረስ የዘለቀው የዕውቁ ቤተ መጽሐፍና ዩኒቨርስቲ መቃጠል ነው። «የጥበብ ቤት –House of Wisdom» ይሰኛል።

የዚህ ቤተ መጽሐፍት መቃጠል አሁን ያለንበትን የሳይንስ እድገት ወደ ኋላ እንደገታውና እስካሁን ድረስ ያለው ሳይንስ ያልደረሰባቸው በርካታ የሳይንስ ጽንሰ ሃሳቦችም ያኔ ወደ አመድነት ተቀይረዋል። ከፊሎቹን ደግሞ ሰርቀው ወደ አውሮፓና ሌሎች አካባቢዎችም በመውሰድ የራሳቸው ሰዎች አዲስ ግኝት አስመስለው የታሪክ ሌባ ሆነዋል።

አሁን ላይ ዘምነናል የሚለው የቴክኖሎጂው ዓለም ሳይቀር ስሙን የሚጠራውና አልጎሪዝም የሚለው ጥልቅ የዘመናችን የኮምፒዩተር ዓለም ጽንሰ ሃሳብ በስሙ የሚጠራለት የፐርሺያው ጠቢብ ሙሐመድ ኢብኑ ሙሳ አል-ኸዋሪዚሚ የዚህ ቤተ መጽሐፍት ኃላፊ (head) ነበር።

ከዚህ የብዝሃ ሒሳብ ሊቅ (Polymath) ባሻገር የኢኩሊድን (Euclid) ሥራዎች የተረጎሙ፣ የእነ አርስቶትልን ፍልስፍና አሽመድምደው ቻሌንጅ ያደረጉ፣ የፊዚክስ ሊቁ አቪሴንያ፣ ጂኦግራፈሩ ሙሐመድ አል-ኢድሪሲ፣ የሒሳብ ሊቁና አስትሮመሩ መስለማ፣ ኢንጂነሮቹ የበኑ ሙሳ ወንድማማቾች፣ The father of statics የሚባለው ሣቢት፣ ባዮሎጂስቱ አልጃሂዝ፣ ፊዚያሺያኑና ኢንጂነሩ ኢስማዒል አልጀዘሪ (The Book of Knowledge of Ingenious Mechanical Devices in 1206 የሚል መጽሐፍ አለው)፣ ገጣሚ፣ የሒሳብና የፊዚክስ ሊቅ የሆነው ዑመር…  ስንቱን ዘርዝሬ ልጨርሰው… በዚህ ቤተ መጽሐፍት ላይ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ይህ ጊዜ «ወርቃማው የኢስላም ዘመን» ይሰኝ ነበር።

አንዳንድ የዘመናችን ጸሐፊዎች ይህን የዕውቀት ቤት የተሰኘውን ቤተ መጽሐፍት መቃጠል ለዘመናዊው ሳይንስ ያሳጣውን ጥቅም ድካውን ሲገልጹ፤ አሁን ላይ በዓለም ላይ ታዋቂ የሆኑት የአሜሪካ ኮሌጆች በሙሉ፤  እንደ ማሳቹትስ የቴክኖሎጂ ተቋም (MiT)፣ ስታንፎርድ፣ በርክሌይና ሃርቫርድ፣ የእንግሊዝ ኦክስፎርድና ካምብሪጅ፣ ሁሉም እንግሊዝኛ የሚያስተምሩና የማያስተምሩ ሁሉ ቢደመሩ፤ በይተል ሒክማህን አያክሉም። ይቦንሳቸዋል‼

Imagine if you will all of America’s Ivy League Colleges rolled into one; add to those the science and technological power of Carnegie Mellon, MIT, Stanford, and Berkley, then add Oxford and Cambridge to the mix, and the world’s great non-English-speaking universities. It comes close to what the House of Wisdom was like—except it was even more influential.

ድንቅ ታሪክ ያለን ህዝቦች ነን እኛ‼

||

t.me/MuradTadesse

ummalife.com/MuradTadesse

أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة