Translation is not possible.

የቁርአን ተዓምር ሚዘለቅ አይደለም

የቀጠለ......

🔶የፕሮፌሰሩ ምላሽ🔶

ፕሮፌሰሩ(Dr. Moore) ስለ ክሊኒካል ፅንስ ጥናት(clinical embryology ) መጽሃፍም ጽፈዋል እና ይህንን መረጃ በቶሮንቶ ሲያቀርቡ በመላው ካናዳ ብዙ ግርምትን ፈጥሮ ነበር።  በካናዳ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ጋዜጦች የፊት ገጽ ላይ በሰፊው ወጥቶ ነበር እና አንዳንድ አርዕስተ ዜናዎች በጣም አስቂኝ ነበሩ።  ለምሳሌ አንድ ርዕስ እንዲህ ይላል፡- “በጥንታዊ የጸሎት መጽሐፍ ውስጥ የተገኘው አስገራሚ ነገር!” ከዚህ ምሳሌ እንደምንረዳው ሰዎች ነገሩ አልገባቸውም።አንድ የጋዜጣ ዘጋቢ ፕሮፌሰሩን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፣ “ምናልባት አረቦች ስለእነዚህ ነገሮች - ስለ ፅንሱ ገለፃ፣ መልክ እና እንዴት እንደሚለወጥ እና እንደሚያድግ ያውቁ ይሆናል ብለው አያስቡም? ምናልባት ሳይንቲስቶች ከነበሩና  በዚህ ጉዳይ በሰዎች ላይ ጥናት አድርገው ከነበረ። ፕሮፌሰሩ  ዘጋቢው አንድ በጣም አስፈላጊ ነጥብ እንዳመለጡ ወዲያውኑ ጠቆሙ።ሁሉም የፅንሱ ስላይዶች የታዩት እና በፊልሙ ውስጥ የተነደፉት በአጉሊ መነጽር(microscope)ከተነሱ ምስሎች የተገኙ ናቸው። ስለዚህ አንድ ሰው ከአስራ አራት መቶ አመታት በፊት ፅንሱን ለማወቅ ቢሞክር ሊያየው አይችልም"

በቁርአን ውስጥ ያሉት ሁሉም መግለጫዎች የፅንሱ ገጽታ በአይን ለማየት የማያስችሉ ናቸው። ስለዚህ አንድ ሰው ለማየት ማይክሮስኮፕ ያስፈልገዋል።ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱ መሣሪያ ከሁለት መቶ ለማይበልጡ ዓመታት ብቻ ስለነበረ ፕሮፌሰሩም እንዲህ ሲሉ ተሳለቁ፦

"ምናልባት ከአስራ አራት ክፍለ ዘመን በፊት አንድ ሰው በድብቅ ማይክሮስኮፕ ነበረው እና ይህን ምርምር አድርጓል የትም ቦታ ላይ ምንም ስህተት አልሰራም። ከዛ እንደምንም ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) አስተምሮ ይህንን መረጃ በመጽሃፉ ውስጥ እንዲያስቀምጠው አሳምኖታል። ከዚያም መሳሪያውን አጥፍቶ ለዘላለሙ ሚስጥር አድርጎታል።  ይህን ታምናለህ? ማስረጃ እስካላመጣህ ድረስ ማመን የለብህም ምክንያቱም ይህ የማይመስል ነገር ነው"

እንዲያውም፣ “ይህን በቁርኣን ውስጥ ያለውን መረጃ እንዴት ያብራራሉ?” ተብሎ ሲጠየቁ።  "በመለኮት ብቻ ነው የሚገለጥ!" ነበር ምላሻቸው።

የመጀመርያ ክፍል ለማንበብ

https://ummalife.com/post/199362

follow our page inshallah you will benefit.

https://ummalife.com/Marufabadir

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group