Translation is not possible.

🔶ታዋቂው ካናዳዊ የፅንስ-ጥናት(Embryology) ፕሮፌሰር ስለ ቁርአን ምን አለ🔶

ከጥቂት አመታት በፊት በሪያድ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ የሆናክል ሰዎች ስለ ፅንስ ጥናት(Embryology) - በማህፀን ውስጥ ስላለው የሰው ልጅ እድገት የሚናገሩትን የቁርአን ጥቅሶች በሙሉ በመሰብሰብ ቁርኣን የሚናገረው እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ፈለጉ። የማታውቁ ከሆነ የዕውቀት ባልተቤቶችን ጠይቁ የሚለውን የቁርአን ምክር ተቀብለው በጣም እውቅ የሆነና ሙስሊም ያልሆነውን በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የፅንስ ጥናት ፕሮፌሰርን መረጡ።ይህም ፕሮፌሰር በዚህ ርዕሰ ጉዳይ መፅሀፍቶችን ፅፎዋል።እነርሱም ወደ ሪያድ ጋብዘውት "ይህ ስለ ርእሰ ጉዳይህ(ፅንስ-ጥናት) ቁርኣን የሚለው ነው። እውነት ነውን? ምን ልትነግረን ትችላለህ?" አሉት

ለትርጉም የሚፈልገውን ሁሉ እና የጠየቀውን ትብብር ሁሉ ሰጡት። ባገኘውም ነገር በጣም ተገረመና ካዘጋጃቸው መፅሀፍቶች ውስጥ አንዳንድ ይዘቶችን ቀየረ። እንዲያውም ከመወለዳችን በፊት(Before We Are Born) በተሰኘው መጽሐፉ ሁለተኛ እትም ላይ ስለ ፅንስ ታሪክ ክፍል በቁርኣን ባገኘው ነገር ምክንያት በመጀመሪያው እትም ላይ ያልነበሩ አንዳንድ ነገሮችን አካቷል።ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ቁርአን በወረደበት ዘመን የሰው ልጆች በጭራሽ ሊደርሱበት የሚችሉት ዕውቀት አልነበረም።

በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ እንዲህ ሲል ተናግሮዋል: ስለ ሰው ልጅ እድገት ቁርኣን የሚናገራቸው አንዳንድ ነገሮች እስከ ሰላሳ አመት በፊት ያልታወቁ ነበሩ። በተለይ ደግሞ ቁርኣን የሰው ልጅን በአንድ ደረጃ ላይ “አልቅት የመሰለ የረጋ ደም”(leech-like clot)(አለቃህ) የገለፀበት መግለጫ (ሱራህ አል-ሐጅ22፡5፤ አል-ሙእሚኑን23:14 እና አል-ጋፊር 40:67) ለእርሱ አዲስ ነበር ነገር ግን ባጣራው ጊዜ እውነት ሆኖ ስላገኘው በመጽሃፉ ላይ ጨመረው። እሱ “ከዚህ በፊት አስቤው አላውቅም” አለና ወደ እንስሳት ትምህርት ክፍል ሄዶ የአልቀት(leech) ምስል እንዲሰጠው ጠየቀ።ልክ የሰው ልጅ ፅንስ እንደሚመስል ሲያውቅ ሁለቱንም ሥዕሎች በአንዱ መጽሐፍ ውስጥ ለማካተት ወሰነ።

👉ይህ ገለፃ በዚህ ዘመን ሰዎች ለሳይንስ ከሰጡት ትልቅ ቦታ አንፃር ቁርአን በዚህ ረገድም ቢሆን ምንም ስህተት የማይነካው መሆኑን እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ እንጂ ቁርአን በሳይንስ አይመዘንም። ምክንያቱም ምሉዕ የሆነ የአላህ ቃል ነውና።

የፕሮፌሰሩ ጉዳይ በዚህ አላበቃም የህን ግኝቱን ይፋ ካደረገ በኋላ ከሃገሬው ህዝብ ምን ገጠመው ምንስ ምላሽ ሰጠ ሚለው አላህ ካለ ቀጣይ ክፍል ላይ እናያለን።

ምንጭ: Dr. Gary miller, The Amazing Quran.

Follow me inshallah you will benefit.

https://ummalife.com/Marufabadir

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group