1 year Translate
Translation is not possible.

ጀግኖች

1 year Translate

የእስራኤል ምርቶች በደቡብ አፍሪካ እንዲታገዱ ጥሪ ቀረበ

የደቡብ አፍሪካ ሶስተኛው ትልቁ የፖለቲካ ፓርቲ የኢኮኖሚ ፍሪደም ተዋጊዎች በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የፓርቲው መሪ ጁሊየስ ማሌማ የእስራኤል መንግስት “ለሰብአዊነት ምንም ክብር የለውም” ካሉ በኋላ ኤምባሲው እንዲዘጋ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ማሌማ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ቸርቻሪዎች በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በእስራኤል የሚመረተውን ዕቃ ከመደርደሪያቸው እንዲያወጡ አሳስበዋል። "ከእስራኤል ምርቶች ካላነሱ እኛ እራሳችንን እናስወግዳለን፣የእስራኤል ምርቶች በደቡብ አፍሪካ እንዲሸጡ አንፈልግም ፣የንፁሀን ደም በእጃቸው ላይ ካሉ ሰዎች ምግብ አንፈልግም" ሲሉ ማሌማ አክለዋል።

ደቡብ አፍሪካን በበላይነት የሚመራው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ አርብ ዕለት ከእስራኤል ኤምባሲ በራፍ ላይ ተመሳሳይ አድርጓል።የፓርቲው ምክትል ዋና ጸሃፊ ኖምቩላ ሞኮንያኔ ደቡብ አፍሪካውያን ከፍልስጤማውያን ጋር በመተባበር ከእስራኤል የሚገቡትን ምርቶች እንዲከለከሉ ጠይቀዋል።

ወይዘሮ ሞኮንያኔ ደቡብ አፍሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደውን ጦርነት አፋጣኝ የተኩስ ማቆም ጥሪዋን ደግማለች። ባለፈው ሳምንት የፓርቲው የሴቶች ሊግ ቃል አቀባይ ፓርቲው በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ውስጥ  የአይሁዳውያንን የደረሰባቸውን ጉዳት ማየት ባለመቻሉ ክስ አቅርቧል።

በስምኦን ደረጄ

#ዳጉ_ጆርናል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group