UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Ibn Ahmed shared a
Translation is not possible.

Sheikh Dr. Salih Fewzan Al-Fewzan

ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና የአይሁዶች በፈለስጢን አካባቢ መሰባሰብ የቂያም ቀን አንዱ ምልክት ነው ይላሉ።

አላህ እነዚህን ካፊሮች ከነ አጋሮቻቸው ከምድረ ገፅ ያጥፋቸው።

192 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ibn Ahmed shared a
Translation is not possible.

ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ ነገር አለ⁉️

========================

✍ የፈለስጢን (የጋዛ ሙስሊሞች) ጉዳይ በየቀኑ አሳዛኝነቱ ቀጥሏል። በየቀኑ የንጹሐን ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፣ በርካታ መሠረት ልማቶች እየወደሙ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት እስካሁን 5087 ሙስሊሞች በጽዮናዊቷ ያላባራ የቦምብ ዝናብ ተገድለዋል፣ ከነዚህ መካከል 2055 የሚሆኑት ህፃናት ሲሆኑ 1119 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። 217ቱ አዛውንቶች ነበሩ። 1500 የሚሆኑት በፍርስራሽ ስር እንደጠፉ ናቸው፤ ከመካከላቸው 800 የሚሆኑት ህፃናት አሉ። እስካሁን ድረስ ጀናዛቸው እንኳ አልተገኘም። 15,273 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አጠቃላይ የተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ አካባቢ ሲሆኑ፤ 685 ሺህ የሚሆኑት ከሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል፣ 565 ሺህ የሚሆኑት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞችና የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ (UNRWA) ጋር ግንኙነት ወዳላቸው ት/ቤቶች ተፈናቅለዋል፣ 101 ሺህ የሚሆኑት በመስጂዶች፣ በቤተ ክርስቲናትና በህዝባዊ ቦታዎች ተጠልለዋል፣ 70 የሚሆኑት በ67 ት/ቤቶች ተፈናቅለው ይገኛሉ።

የተለያዩ ሃገራት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት ያላትን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅማ የፈለስጢናዊያን ጭፍጨፋ እንዲቀጥል አድርጋለች።

ምን ያክል የፈለስጢን ህፃናትና ሴቶች ተጨፍጭፈው ሲያልቁ እንደምትረካ አይታወቅም።

ሌላውም ዓለም በሰልፍ ድጋፉ እያሳዬ ቢሆንም ከዚያ የዘለለ ማድረግ አልቻለም።

በጋዛ አሁንም ቢሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የምግብና የነዳጅ ማዕቀብ እንደተጣለ ነው። ባለፈ ብቻ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪኖች ገብተው ነበር። ግን ለ2+ ሚሊዮን ህዝብ ምንም ማለት አይደለም። የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመመከት በየቀኑ መቶ የጭነት መኪኖች መግባት አለባቸው።

አላህ በጥበቡ ከላይ ፈረጃውን አውርዶ ካሉበት በላእ ይገላግላቸው እንጂ እየተካሄደ ያለው ይፋዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሰቃቂ እልቂት ነው።

ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና ሁሌም ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸው።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group