UMMA TOKEN INVESTOR

About me

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَنطِلَ كَانَ زَهُوقًا And say, "Truth has come, and falsehood has departed. Indeed is falsehood, [by nature], ever bound to depart. Surah Al-Isra Ayat 81

Followings
0
No followings
5 month Translate
Translation is not possible.

🍂ከተወሰኑ ወራት በኋላ አንድ ታላቅ እንግዳ ይመጣል

አሁን ያለንበትን ድባብ ይለወጣል

ቀናቶች ያምራሉ ፣ ምሽቶች ይደምቃሉ

አማኞች ይደሰታሉ ፣ መስጂዶች ይሞላሉ

ሸይጣኖች ይታሰራሉ ፣ የጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይቆለፋሉ ፣ ኸይሮች ይሸመታሉ

አላህ ለታላቁ ረመዳን በሰላም ያድርሰን ደርሶም ከሚጠቀሙባቸው ያርገን ያረብ🤲

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
5 month Translate
Translation is not possible.

ልብህን በምቀኝነት አታቃጥለው በጥላቻ አትግደለው ፣ በስስትም አትበክለው ንፁህ ልብ ይኑርህ አዕምሮህን ከመጥፎ ሀሳብ አርቀው። ሰላም ሆነህ ሰላም ትኖራለህ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

የጁሙዓ እና የጀማዓ ሶላት ትሩፋት

1. ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-«ገላውን ታጥቦ ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው፣የተመቸዉን ያህል ሰግዶ ኢማሙ ኹጥባውን እስኪፈጽም ድረስ አዳምጦ ከኢማሙ ጋር ጁሙዓ የሰገደ ሰው እስከተከታዩ ጁሙዓ ድረስ ላለው (ኃጢዓቱ)እና ከተጨማሪ ሶስት ቀናት ጋር ምህረት (ከአላህ)ይደረግለታል፡፡ (ለሶላቱ ቀርቦ) አሸዋ እየነካካ የተጫወተ ሰው በእርግጥ ቁም ነገር የለሽ ነገር ሠርቷል፡፡»(ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ)

2. ነብዩ (ሰ.አ.ወ) እንዲሁ ብለዋለ፡-«ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ

በሚታጠበው ዓይነት ገላውን ታጥቦ ለጁሙዓ ሶላት የሄደ ሰው ግመል ለመሰዋት እንዳበረከተ ሰው ይቆጠራል ፡፡በሁለት ሰዓት ወደ ጁሙዓ የሄደ ሰው ላም እንዳቀረበ ይቆጠራል፡፡ በሶስት ሰዓት የሄደ ሰው ቀንዳም በግ እንዳቀረበ ይቆጠራል፡፡በአራት ሰዓት የሄደ ሰው ዶሮ እንዳቀረበ ይቆጠራል ፡፡ በአምስት ሰዓት የሄደ ሰው ደግሞ እንቁላል እንዳቀረበ ይቆጠራል ፡፡ ኢማሙ ብቅ ሲል መላይካዎች (የአላህን )ውዳሴ ለማዳመጥ በቦታው ይገኛሉ፡፡»(ሙስሊም የዘገቡት)

3. ነቢዩ እንዲሁ ብለዋለ ፡-«የኢሻን ሶላት በጀማዓ የሰገደ ሰው የሌሊቱን አጋማሽ(አላህን) በመገዛት እንዳሳለፈ ሰው ይቆጠርለታል፡፡ የሱብህን ሶላት በጀመዓ የሰገደ ሰው ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ (አላህን በመገዛት) እንዳሳለፈ ሰው ይቆጠርለታል፡፡(ሙስሊም የዘገቡት )

4. ነቢዩ እንዲሁ ብለዋለ ፡-«አንድ ሰው በጀማዓ የሚሰግደው ሶላት በቤቱና በሥራ ቦታው ከሚሰግደው ሶላት ከሃያ ሶስት እስከ ሃያ ዘጠኝ ባሉት ቁጥሮች ደረጃ ያህል ብልጫ አለው፡፡ይኸውም አንድ ሰው የተሟላ ውዱዕ አሳምሮ በማድረግ ለሶላት ብቻ የሚንቀሳቀስ እና ዓላማው ሶላት ብቻ ሆኖ ወደ መስጊድ ከመጣ በያንዳንዱ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ የሚልና በዚያው ልክ ኃጢአቱ የሚሰረዝለት ቢሆን እንጂ መስጊድ እስኪደርስ ድረስ አንድም እርምጃ አይራመድም ፡፡ መስጊድ ሲገባም ሶላቱ እስከያዘው ድረስ ሶላት ውስጥ እንዳለ ሰው ነው የሚታሰበው፡፡ አንድ ሰው በሰገደበት ቦታ ላይ እስከ ቆየ ድረስ መላይካዎች አላህ ሆይ! እዘንለት፣ አላህ ሆይ! ምህረት አድርግለት ፣ አላህ ሆይ! ይቅር በለው እያሉ ጸሎት ያደርጉለታል ፡፡(ይህም)ሌሎችን ያላወከና ውዱዑን (ንጽህናውን)ካላፈረሰ ነው፡፡»(ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡተ ሐዲስ ሲሆን ቃሉ ከሙስሊም ዘገባ ነው)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

ارجع اليهم فلنأتينهم بجنود تفسير

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 month Translate
Translation is not possible.

اَللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ مُحَمَّدٍ وَصَحْبِهِ وَسَلَّمْ

Send as a message
Share on my page
Share in the group