1 year Translate
Translation is not possible.

የጁሙዓ እና የጀማዓ ሶላት ትሩፋት

1. ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-«ገላውን ታጥቦ ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው፣የተመቸዉን ያህል ሰግዶ ኢማሙ ኹጥባውን እስኪፈጽም ድረስ አዳምጦ ከኢማሙ ጋር ጁሙዓ የሰገደ ሰው እስከተከታዩ ጁሙዓ ድረስ ላለው (ኃጢዓቱ)እና ከተጨማሪ ሶስት ቀናት ጋር ምህረት (ከአላህ)ይደረግለታል፡፡ (ለሶላቱ ቀርቦ) አሸዋ እየነካካ የተጫወተ ሰው በእርግጥ ቁም ነገር የለሽ ነገር ሠርቷል፡፡»(ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ)

2. ነብዩ (ሰ.አ.ወ) እንዲሁ ብለዋለ፡-«ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ

በሚታጠበው ዓይነት ገላውን ታጥቦ ለጁሙዓ ሶላት የሄደ ሰው ግመል ለመሰዋት እንዳበረከተ ሰው ይቆጠራል ፡፡በሁለት ሰዓት ወደ ጁሙዓ የሄደ ሰው ላም እንዳቀረበ ይቆጠራል፡፡ በሶስት ሰዓት የሄደ ሰው ቀንዳም በግ እንዳቀረበ ይቆጠራል፡፡በአራት ሰዓት የሄደ ሰው ዶሮ እንዳቀረበ ይቆጠራል ፡፡ በአምስት ሰዓት የሄደ ሰው ደግሞ እንቁላል እንዳቀረበ ይቆጠራል ፡፡ ኢማሙ ብቅ ሲል መላይካዎች (የአላህን )ውዳሴ ለማዳመጥ በቦታው ይገኛሉ፡፡»(ሙስሊም የዘገቡት)

3. ነቢዩ እንዲሁ ብለዋለ ፡-«የኢሻን ሶላት በጀማዓ የሰገደ ሰው የሌሊቱን አጋማሽ(አላህን) በመገዛት እንዳሳለፈ ሰው ይቆጠርለታል፡፡ የሱብህን ሶላት በጀመዓ የሰገደ ሰው ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ (አላህን በመገዛት) እንዳሳለፈ ሰው ይቆጠርለታል፡፡(ሙስሊም የዘገቡት )

4. ነቢዩ እንዲሁ ብለዋለ ፡-«አንድ ሰው በጀማዓ የሚሰግደው ሶላት በቤቱና በሥራ ቦታው ከሚሰግደው ሶላት ከሃያ ሶስት እስከ ሃያ ዘጠኝ ባሉት ቁጥሮች ደረጃ ያህል ብልጫ አለው፡፡ይኸውም አንድ ሰው የተሟላ ውዱዕ አሳምሮ በማድረግ ለሶላት ብቻ የሚንቀሳቀስ እና ዓላማው ሶላት ብቻ ሆኖ ወደ መስጊድ ከመጣ በያንዳንዱ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ የሚልና በዚያው ልክ ኃጢአቱ የሚሰረዝለት ቢሆን እንጂ መስጊድ እስኪደርስ ድረስ አንድም እርምጃ አይራመድም ፡፡ መስጊድ ሲገባም ሶላቱ እስከያዘው ድረስ ሶላት ውስጥ እንዳለ ሰው ነው የሚታሰበው፡፡ አንድ ሰው በሰገደበት ቦታ ላይ እስከ ቆየ ድረስ መላይካዎች አላህ ሆይ! እዘንለት፣ አላህ ሆይ! ምህረት አድርግለት ፣ አላህ ሆይ! ይቅር በለው እያሉ ጸሎት ያደርጉለታል ፡፡(ይህም)ሌሎችን ያላወከና ውዱዑን (ንጽህናውን)ካላፈረሰ ነው፡፡»(ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡተ ሐዲስ ሲሆን ቃሉ ከሙስሊም ዘገባ ነው)

Send as a message
Share on my page
Share in the group