Translation is not possible.
#የሰዎችን #ውጫዊ #እንቅስቃሴና #ተግባር (#አምኖ) #መቀበልና #ውስጣቸውን #ለአላህ #መተው
#ክፍል_5
#ሐዲሥ 49 / 395
ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፥ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ የሙስሊሞች ጦር ወደ አጋሪዎች አዘመቱ። (ሁለቱ ኃይሎች) ተገናኙ። ከአጋሪዎች መካከልም ከሙስሊሞች አንዱን (በመግደል) ከፈለገ የሚገድል (አልሞ የማይስት) አንድ አጋሪ ነበር። ከሙስሊሞች መካከል አንዱ _ ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ ነው ብለን እናስባለን_ ሰውየው እስኪዘናጋ ጠብቆ (ሊገድለው) ሰይፍ ሲያነሳ (አጋሪው)፦ “ላ ኢላሀ ኢልለላህ” አለ። ግና ገደለው። ብስራት (መልዕክት) ነጋሪው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ ቀረበ። ጠየቁት፡፡ የሆነውን ሁሉ ይነግራቸው ጀመር። የሰውየውን ሁኔታና ምን እንደ ፈፀመ ሲነግራቸው (ገዳዩን) ጠርተው “ለምን ገደልከው?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሙስሊሞችን አወከ። እገሌን፥ እገሌን ገደለ” በማለት ስሞችን ዘረዘረላቸው። “ዘመትኩበት፡፡ ሰይፍ ሲያይ ላ ኢላሀ ኢልለላህ አለ” ሲልም (ምክንያቱን) ነገራቸው። የአላህ መልዕክተኛም፥ “ገደልከውን?” አሉት፡፡ “አዎ” አላቸው። “በዕለተ ትንሳኤ ላ ኢላሀ ኢልለላህ ስትመጣ ምን ልታደርጋት ነው?” አሉት፡፡ “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምሕረት ይጠይቁልኝ” አላቸው። “በዕለተ ትንሳኤ ላ ኢላሀ ኢልለላህ ስትመጣ ምን ልታደርጋት ነው?” ከማለት ውጭ ያከሉት ነገር የለም። (ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ ይህና ከዚህ ቀደም የተወሳው ሐዲሥ የሚተርኩልን አንድ ዓይነት ክስተት እንደሆነ ዑለሞች ይናገራሉ። የትረካ ስልቱ የተለያየው ሐዲሡን ያስተላለፉት ግለሰቦች በመለያየታቸው ነው። ስለዚህ ለላይኛው ሐዲሥ የተዘረዘሩ አስተምህሮዎችን ይህም ሐዲሥ ያስተምራል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group