UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

🤲 ተውበት 🌅

ተውበት፡- በአላህ (عزوجل) ትእዛዝ ላይ ከማመፅ ለህግጋቱ ወደ መታዘዝ መመለስ ነው፡፡

ተውበት፡- ተውበት አላህ (عزوجل) ዘንድ በጣም የተወደደ ነው፡-

💎‹‹…አላህ ከኃጢአት ተመላሾችን ይወዳል ተጥራሪዎችን ይወዳል››

📚(አል በቀራህ 222)

ተውበት በእያንዳንዱ አማኝ ላይ ግዴታ ነው፡፡

💎‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ንፁህ የኮነችን ፀፀት በመፀፀት ወደ አላህ ተመለሱ…›› 📚(አል ተህሪም 8)

💎‹‹…ምእመናኖች ሆይ ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተፀፀቱ››

📚(አል ኑር 31)

መድህን (ፈላህ) ማግኘት ማለት አንድ ሰው የፈለገውን ማግኘት የሚፈራውን ነገር መዳን ነው፡፡

ፍፁምና እውነተኛ የሆነ ተውበት፡- የፈለጉትን ያህል ቢከብድና ያሻቸውን ያህል በብዙ እንኳን አላህ (عزوجل) ፍፁምና እውነተኛ ከሆነ ተውበት ኃጢአቶችን ሁሉ ይቅር ብሎ ምህረት ያደርጋል፡፡

💎በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡››

📚 (አል ዙመር 53)

ወንጀለኛው ወንድሜ ከጌታህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ የተውበት በር ፀሐይ በመጥለቂያዋ በኩል ተመልሳ እስከምትወጣበት ጊዜ ክፍት ነውና፡፡

ነብዩ እንዲህ ብለዋል

{إن الله يبسط يده بالليل ليتوب مسيء النهار ويبسط يده بالنهار ليتوب مسيء الليل حتى تطلع الشمس من مغربها }

‹‹ቀን ጥፋት የሰራ ሰው ተፀፅቶ ይመለስ ዘንድ አላህ ለሊት እጁን ይዘረጋል ለሊት ጥፋት የሰራ ሰው ተፀፅቶ ይመለስ ዘንድ እጁን ቀን ይዘረጋል ፀሐይ ከመጥለቂያዋ በኩል ተመልሳ እስከምትወጣበት ድረስ ነው፡፡››

በፈፀሙት ብዙና ከባድ ኃጢአቶች ተፀፅተው ወደእርሱ የተመለሰ የስንትና ስንቱን ፀፀት አላህ ተቀብሏል፡፡

💎አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፡-

‹‹እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡ በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል፡፡ ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡››

📚(አል ፉርቃን 68-7ዐ)

ፍፁምና እውነተኛ የሆነ ፀፀት (ተውበት አነሱሐ) አምስት መስፈርቶች ያሟላ ነው፡፡

1. ለአላህ (عزوجل) ፍፁማዊ መሆን)ኢኽላስ) ሲሆን ይህም ተፀፅቶ የሚመለስና ተውበት የሚያደርገው ለአላህ (عزوجل) ብሎ ምንዳውን ለማግኘትና ከቅጣቱ ለመዳን በማቀድ መፀፀት ማለት ነው፡፡

2. በሰራው ጥፋትና በፈፀመው ኃጢአት በመፀፀት ባልሰራሁት ብሎ ባሳለፈው ድርጊት መጸጸት፡፡

3. ከኃጢአቱ ወዲያውኑ መወገድና ከነጭራሹ እርግፍ አድርጐ መተው፡፡ የተፈፀመው ጥፋት ከአላህ (عزوجل) መብት ጋር የተያያዘ የተከለከለና ሀራም የሆነ ነገር ሰርቶ ከሆነ ወዲያውኑ ማቆም ማድረግ የነበረበት ነገር ትቶ ከሆነም ወዲያውኑ ወደስራው መሰማራት ነው፡፡ ጥፋቱ ከፍጡራን መብት ጋር የተያያዘ ከሆነም ራስን ወዲያውኑ ከዚያ ነገር ነፃ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ወይም የሚመለስ ነገር ከሆነ ለባለመብቱ መመለስ ወይም ጥፋት የተሰራበትን ሰው ፉፁማዊ ይቅርታና ልባዊ ምህረት በመጠየቅ ይሆናል፡፡

4. ወደፊት ወደዚያ ኃጢአት ጭራሽ ላለመመለስ ቁርጠኛና ፅኑ አቋም መወሰን፡፡

5. ተውበቱ በእድሜው ፍፃሚ መድረስ ምክንያት ወይም ደግሞ ፀሐይ በስተምዕራብ በኩል ተመልሶ በመውጣቷ የተውበት መቀበያ ጊዜው ያላለፈ መሆን አለበት፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል፡-

💎‹‹ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ «እኔ አሁን ተጸጸትኩ» ለሚል… አይደለችም፡፡››

📚(አል ኒሳእ 18)

ነብዩም እንዲህ ብለዋል

{من تاب قبل أن تطلع الشمس من مغربها تاب الله عليه }

“ፀሐይ ከመጥለቂያ በኩል ተመልሳ ከመውጣቷ በፊት ከሰራው ኃጢአት ተፀፅቶ የተመለሰ ሰው ፀፀቱን ይቀበላል፡፡››

📚ሙስሊም ዘግበውታል

አላህ ሆይ እውነተኛ የሆነ ልባዊ ተውበት ከእኛም ተቀበለን አንተ ሰሚውና በጣም አዋቂው ነህና፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ደስተኛ መሆን ቀላል ነው አንድ ካንተ የሚጠበቅብህ ነገር ዞር ብለህ ወደራስህ መመልከት እና ፈጣሪ የሰጠህን እያንዳንዱን በረከትህን ማየት ነው ከዚያም በደንብ አድርገህ አመስግነው ያለህ ከሌለህ እጅጉን ይበልጣል የማይጠቅምህን ነው የተከለከልከው እናም ፈጣሪህን በሰጠህ ነገር ስታመሰግን ደስታህ እጥፍ ድርብ ይሆናል !

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Dawud Yimer Сhanged his profile picture
10 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group