UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ቀድሩ አማን ኸድር

kedru Aman Сhanged his profile picture
11 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከዚህ የBBC ዘገባ ኮሜንት መስጫ ውስጥ ያገኘሁት አስተማሪ ታሪክ ነው አንብቡት

እረኛው በጎችን ይዞ ወደ ማደሪያቸው አስገብቶ በሮችን ሁሉ በሚገባ ዘጋው። የተራቡ ቀበሮዎች በጎቹን ሊበሉ ሲመጡ በሮች ሁሉ በሚገባ ተዘግተው አገኙት። በሮችን አልፈው መግባትን ተስፋ የቆረጡት ቀበሮዎችም፤ በጎቹን ከበሮች ቁጥጥር ውጭ ለማድረግ ሴራቸውን ይጠነስሱ ጀመር። በመጨረሻም ቀበሮዎቹ (የበጎች ነፃነት ይከበር) የሚል መፍክር ይዘው የበጎቹን ማደርያ ዙርያ ለመዞር ወሰኑ።

በጎችም ለነሱ ነፃነት እንዲከበር ቀበሮዎች ትልቅ አብዮት እንዳቋቋሙ ሲሰሙ ልባቸው ወደ ቀበሮዎቹ ይሸፍት ጀመር።

የነፃነት አብዮቱን ለመቀላቀል በርካታ በጎችም የግቢያቸውን አጥር በቀንዶቻቸው ይነቀንቁ ጀመር። ከረጅም ግዜ ረብሻ እና ትርምስ በኋላ በጎቹ ማደሪያቸውን አፍርሰው አብዮቱን ለመቀላቀል ወደ ጫካዎች ፈረጠጡ። ቀበሮዎችም ከበጎቹ ኋላ ይሮጡ ጀመር፤ እረኛውም ከኋላ ኋላ እየሮጠ አንዴ በድምፁ አንዴ በብትሩ ሊመልሳቸው ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም።

አብዮታዊ ሩጫው ቀጥሏል፤ በጎች ከፊት ቀበሮዎች ከኋላ....ብዙም ሳይርቁ ቀበሮዎች እና በጎች ያለ እረኛ ያለ ከልካይ ሰፊ በረሃ ላይ ተፋጠጡ። ያች ቀን የነፃነት አብዮትን ፍለጋ ለወጡት በጎች ጨለማ ስትሆንባቸው፤ ሴራን ላሴሩት ቀበሮዎች ግን የደስታ እና የፈንጠዝያ ቀን ነበረች።

በማግስቱ እረኛው ተነስቶ ወደ አብዮት የወጡትን በጎች ፍለጋ ወደ በረሃው ሲያቀና፤ የነፃነት መገለጫ የሆኑ ቀበሮዎች ነፃነትን ፍለጋ የወጡትን በጎች ስጋዎቻቸውን በልተው፣ አጥንቶቻቸውን በመሰባበር ሜዳው ላይ በትነዋቸው አገኘው።

_____

ድሮ የሰማናት ተረት ናት አይደል!!!

ግን በአለማችን የሚገኙ የሴቶች የነፃነት አብዮትን እና ቀበሮዎችን ምን ያህል እንደሚመሳሰሉ አስተውላችሁታል!!!? የሴቶች ነፃነት አብዮት የሙስሊም ቁጥብ፣ ጨዋ እና እንቁ ሴቶችን በቀላሉ ሊያገኝ አይችልም።

ምክንያቱም፦ አባቶቻቸው ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል።

ምክንያቱም፦ቤታቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘዋል።

ምክንያቱም፦ ሂጃብ አድርገዋል። ለዝያም ነው የሰው ቀበሮዎች <የሴቶች ነፃነት> የሚል መፈክር ይዘው ሚስተዋሉት። አላማው ግን <የሴቶች ነፃነት> ሳይሆን <ወደ ሴቶች መድረሻ ነፃነት> ነው።

https://t.me/sunnahaudio1/1202

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሚያስደስተኝ እኔ ሳይሽ

ተሸፋፍነሽ በኒቃብሽ

በሽተኛን አደናብረሽ

የሱናን ሰው ልቡን ማርከሽ

ረመድ ረመድ ስትይ አንገት ደፍተሽ

እያት እስኪ ተነቅባ

ሃያእ ከላይ ደራርባ

ብለው ሰዎች ሲያወሩ

በውበትሽ ሲፎክሩ

አይቅርብኝ እኔም ብዬ

በተቻለኝ ሞራል የአቅሜን ብዬ

የውበት ጥግ አላብሶሻል

አታውልቂው ያምርብሻል።

ከተወሰነ ማሻሻያ ጋር

C:- سميرة بنت شمسو

https://t.me/sunnahaudio1/1195?single

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ - ረሒመሁላህ - ሲሞቱ ጊዜ ታስረውበት በነበረው ወህኒ ቤት ውስጥ በሳቸው የእጅ ፅሑፍ የተፃፉ እንዲህ የሚሉ አሳዛኝ የግጥም ስንኞች ተገኝተዋል። በግርድፉ ተርጉሜዋለሁ።

“እኔ ነኝ ደካማው ከጃይ … ከሰማያቱ ባለቤት

በሁለመናዬ ስንኩል … እኔው ነኝ ምስኪኑ ማለት።

እኔው ነኝ የራሴ ጠላት … ነፍሴ እራሷ ነች በዳዬ

ኸይር ሁሉ የሚገኘው … ከሱ ብቻ ነው ጌታዬ።

ለራሴ እንኳን የማልሆን … የማላቀርብ አንዳች ፋይዳ

መከላከል አይሆንልኝ … በክፉ እንዳልጎዳ።

ሌላ ፈጣሪም የለኝ … ከሱ ውጭ ‘ሚያስተናብር

አማላጅም አይኖረኝ … ወደ ጌታ የሚያሻግር

በሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ … በፈጠረኝ በረሕማኑ

የሰማያቱ ባለቤት … እንዳወሳው በቁርኣኑ

ቅንጣት የሌለኝ ከንቱ … ያለ ጌታዬ ይሁንታ

አንዳች ተጋሪም የለው … በየትኛውም ሁኔታ

አጋዥ አይፈልግ ደጋፊ … ረዳት አይሻ የኔ ጌታ

ልክ እንደሚያስፈልጋቸው … ለወልዮቹ አይነታ።

ችግር ድህነት አርማዬ … የኔ ቋሚ መገለጫ

መብቃቃቱ የጌታ ነው … የሁልጊዜ ባለብልጫ

አንጋጣጭ ነው ወደ ጌታ … ፍጡር ሲባል ጠቅላላ

ሁሉም ተዋርዶ ይቀርባል … ቢሻው ጠላ ቢሻው ደላ።

ከፈጠረው ጌታ ውጭ … ምኞት ፍላጎት የሚሻ

ቂል፣ በዳይ፣ አረመኔ … አጋሪ ነው መጨረሻ።

ይመስገነው ፈጣሪዬ … አለሙን በፀጋው የሞላ

ላለፈውም ለመጪውም … ላደረገልን በመላ።

ከዚያም ሶላቱ ይትረፍረፍ … በምርጡ ነቢያችን ላይ

የፍጡራን ቁንጮ አይነታ … የሁሉ ላይ የላይ በላይ።” [አልዑቁድ፡ 391]

=

* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group