UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ሙእሚን በዲኑ ላይ ጥንካሬ በለስላሳነቱ ላይ ድፍረት በርግጠኝነቱ ላይ ኢማን በመረዳቱ ላይ ጥልቀት በመልካምነቱ ላይ ፅናት በእውቀቱ ላይ ተግባር በቅንነቱ ላይ ንቃት በገርነቱ ላይ ብልጠትያለውና ስሜቱ የማያሸንፈው ሆዱ የማያዋርደው ሰዎች በሱላይ ነፃነት የሚሰማቸው ሰውን የማያማና በሰው ላይ የማይኮራ ነው ዓ.ኢ.አ.ጧ

Translation is not possible.

በታሪክ ውስጥ ትኩረትና ወኔ የሚባሉ ንጥረ ነገሮች ሳይጨመሩበት ወደ መሆን የመጣ መልካም ነገር አለ ለማለት ያስቸግራል ሁሉም ነገር ወደመሆን የሚመጣው በትኩረት ኃይል ነው ሁሉም ነገር ሊቀጥልና ሊሻሻል የሚችለው ትኩረት የተሰጠውን መጠን ያህል ነው ሁሉም ነገር ሊኖረን ይችላል ዳሩ ግን ያለትኩረት ልንጠቀምበት አንችልም አውቀት ብቻውን መረጃ ነው አላማ ብቻውን ሃሳብ ነው ብልህነት ብቻውን በቂ አይደለም ሀብት ብቻውን አይጠቅምም አነዚህ ነገሮች በሙሉ የመገልገያ መሳሪያዎች አንጂ ሌላ አይደሉም አነሱን የሚያንቀሳቅሰው ትኩረት የሚባለው ኃይል ነው አንድ ሰው ያለውን አቅም ለመጠቀም ትኩረት ካጣ አውቀትና ሙያ ስላለው ብቻ ተጠቃሚ ሆነ ጠቃሚ ሊሆን አይችልም ጉልበታችንን አውቀታችንን ሙያችንን ስልጣናችንን ትኩረት የሚባለው ኃይል ተጨምሮበት ነፍስ አንዲዘራበት ካላደረግነው ብቻውን ፋይዳ ሊሰጠን አይችልም የተጀመረው የሚቀጥለው የተበላሸው የሚስተካከለው የተወለደው የሚያድገው ትኩረት ከተሰጠው ብቻ ነው የፈለግነውን ወደመሆን ለመምጣት የተላነውን ገለል ለማድረግ ያለንን ይዞ ለመዝለቅ የትኩረት ኃይል ያስፈልገናል

አንድን ሁኔታ አሳጥረን ብንጠቀልለውም አስረዝመን ብንተረትረውም ትኩረትን የመፈለጉ ሂሳብ አንድ አይነት ነው ትኩረት ካለ ሁሉም ነገር አለ ትኩረት ከሌለ ሁሉም ነገር የለም ትኩረትን ያጣ ነገር ትልቁ ትንሽ ነው ትኩረትን ያገኘ ነገር ትንሹ ትልቅ ነው ማንም ሰው በማንኛውም ወቅት ማንኛውንም ነገር መጀመር ይችል ይሆናል ዳሩ ግን ያለ ትኩረት ይዞት መዘልቅ አይችልም ጦርነት በወሬ ደረጃ ቀላል ቢሆንም ተግባሩ ግን ከባድ ነው የዚህ ምክንያቱ ወሬ የተግባርን ያህል ትኩረት ስለማይሻ ነው በተመሳሳይ ሁኔታ ማንኛውንም ነገር ይዞ ከመዝለቅ መጀመር ቀላል የሚሆነው መጀመር ይዞ የመዝለቅን ያህል ስለማይከብድ ነው አርግጥ የ አንድ ነገር ጅማሮ የ አንድ ተግባር ግማሽ አካል ነው ሆኖም ግን ለፍሬው ሲባል የሚፈለግን ዛፍ ችግኙን ተክሎ ለታሰበለት ነገር ከመድረሱ በፊት የሚጨናገፍ ከሆነ የመትከል ትርጉሙ ምንድነው?

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
fuad mezid Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group