UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Followers
0
There are no followers
Ali Ahmed shared a
Translation is not possible.

ሐዲስ ከአርበዑነ አንነወዊያ~①

የእስልምና ሃይማኖት ደረጃዎች【مراتب الدين】

عَنْ عُمَرَ  قَالَ: " بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعْرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ. حَتَّى جَلَسَ إلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم . فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخْذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنْ الْإِسْلَامِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إنْ اسْتَطَعْت إلَيْهِ سَبِيلًا. قَالَ: صَدَقْت . فَعَجِبْنَا لَهُ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ! قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِيمَانِ. قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاَللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ. قَالَ: صَدَقْت. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ الْإِحْسَانِ. قَالَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّك تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاك. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ السَّاعَةِ. قَالَ: مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنْ السَّائِلِ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا؟ قَالَ: أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ. ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْنَا مَلِيًّا، ثُمَّ قَالَ: يَا عُمَرُ أَتَدْرِي مَنْ السَّائِلُ؟. قَلَتْ: اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ ". رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:8] .

《የሓዲሱ ትርጉም》 """""""""""""""""""""""""""""",,,,,,,,,,,,,,,,,,,""",,,,,,,,,,""""

የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ። “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና ነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።”

ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ።

ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።”

ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም”

ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።”

ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ይበልጥ ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ

“ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።”

№~ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።

《ከሓዲሱ የምንወስዳቸው ትምህርቶች》

“""""""""""""""""""""""""""""""",,,,,,,,,,,,,"""""""""""""""""""""""""""“"“"""""""""

1•ሙስሊሞች ጋር መቀላቀልና ለነሱ ደግሞ መልካም ባህርያትን ማሳየት እንዳለብን ።

2.ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ብሎ ዓሊምን መጠየቅ እንደሚቻልና ይህንን ያደረገ ደግሞ ልክ እውቀቱን የሚያሰተላልፈው ሰው አጅር ያገኛል።

3•እስልምና አምስት ማእዘናት እንዳሉት። ካለነሱ ደግሞ ዲን እንደማይቆም።

4.ኢማን ስድስት ማእዘናት እንዳሉት።

5.እስልምናና ኢማን አብረው ሲጠቀሱ የተለያየ ትርጉም እንዳላቸው። ለየብቻቸው ሲጠቀሱ ግን አንደኛው ሌላኛውን አጠቃሎ እንደሚይዝ።

6.የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሶስት ደረጃዎች እንዳላቸው። እነሱም ኢስላም(ሙስሊም) ኢማን(ሙእሚን) ኢሕሳን(ሙሕሲን) ።

7.የውመል ቂያማ ሰአቷ የተወሰነ እንደሆነ እና እሷንም መች እንደሆነች የሚያቃት አንድ አላህ ብቻ እንደሆነ። ምልክቶችም እንዳላት።

★አቡ ነራሃ★

🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢🪢

https://t.me/+KEtaSN1aDuthMzc0

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ali Ahmed Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group