UMMA TOKEN INVESTOR

Mubarak kedir shared a
Translation is not possible.
የተውበት ኡኡታ
እኔስ ዋይ ጥፋቴ:
አቤት ሞኝነቴ:
ላጠፋ ደረስኩኝ የ²ሀገር ቤቴ:
አስቤ አልሜ የአፍታ ስሜቴ:
አላህን ረስቼ እንዲው መዋተቴ:
በሀራሙ ደስታ እራሴን መሳቴ:
ኧረ ምን ይዋጠኝ እንደው ምን ውስጥ ልግባ:
እተዋለሁ ብዬ ቃል እንኳን ብገባ:
ነገ እረሳዋለሁ በስሜት ስገባ:
ለነፍሴ ፈራሁኝ እሳት እንዳልገባ:
ብሄድ በዚ ሁኔታ  ምን ይለኛል ጌታ:
እኔስ አፍሪያለሁ መቅረብ እዛ ቦታ:
ምን ማረግ ቢያቅተኝ ሀሳቤም ቢምታታ:
አንድ ሀሳብ አለኝ ማይነፈግ ቦታ:
መመለስ ወደሱ ወደ አንዱ ጌታ:
አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው በአንድምታ:
ጌታዬዋ ስማኝ የተውበት ኡኡታ:
አማራጭ የላቸው ተሳሳቾች ሁላ:
ወንጀላቸው በዝቶ ምን ባህር ቢሞላ:
ከተውበቱ ውጪ አንድም የለው መላ:
ላይመለስበት ቃል ገብቶ መሀላ።
✍ሰዑድ ጀማል
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Mubarak kedir Сhanged his profile picture
2 years
Translation is not possible.
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group