የፍልስጤም ጉዳይ የሀይማኖት ጉዳይ አይደለም። የዘር ጉዳይም አይደለም። ከፍልስጥኤማውያን ጎን መቆምም ከእስልምና ጎን አሊያም ከአረብ ጎን መቆም አይደለም። እናም ከፍልስጤም ጎን መቆም ከፍትሕ ጎን መቆም ነው። ለእውነት መቆም ነው። አፓርታይድን አለመደገፍ ነው።
ደቡብ አፍሪካን ተመልከት 80 ከመቶ ሕዝቧ ክሪስቲያን ነው። ሙስሊሙ 4 ከመቶ በታች ነው። ANC ውስጥ አንድም ሙስሊም አመራር የለም። ስለ ፍልስጤም ግን አብዝቶ የሚናገሩት የአፓርታይድን ጠባሳ ስላዩ ነው።
የሴልቲክ ደጋፊን ተመልከት.... አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም የሚከተለውን የካቶሊክ እምነት ተከታይ ናቸዉ። ከሬንጀርስ ደጋፊዎች ጋርም አንዱ ልዩነታቸው ሀይማኖት እንደሆነ ይታወቃል (Catholic Vs Protestant)።
እናም ለፍልስጤማውያን ድጋፋቸውን ሲገልፁ አረብ ወይም እስልምናን እየደገፉ አይደለም። ይልቁንም እውነትን እየደገፉ ነው። ከባንዲራው ጋር ሰዋዊ ክብርን ከፍ አርጎ እያውለበለቡ ነው። በትላንት ምሽቱ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታም የታየው ይሄው ነው። ሴልቲኮች የሚጠብቃቸውን ቅጣት ሳይፈሩ በድጋሚ ለእውነት እና ፍትሕ ታምኗዋል። “You’ll Never Walk Alone” እያሉ በቦምብ አረር እየተገረፉ ላሉ ፍልስጤማዊያን አጋርነታቸውን ገልፀዋል። Free Palestine ሲሉ ስለ ነፃነታቸው ትልም መፈክር አሰምተዋል። Victory to the resistance! ብሎ መከራ ውስጥ ላሉት ለነገው ብርሃን ይሆናቸው ዘንድ የተስፋ ቃልን አዋጥተዋል።
Palestine ምናልባት ምናልባት አንድ ቀን በሁለት እግር መቆም ችላ ሹክረን! ጀዛከላህ! ትላቸው ይሆናል...ለዛ ቀን ያብቃት...