በሀገረ አሜሪካ በሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ጫጫታ ነግሷል። ሁለት እናቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰላም ተገላግለው "ሴቷ ያንቺ ናት እኔ የወለድኩት ወንድ ነው" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ ሆስፒታሉ በጩኸታቸው ተናውጧል። ሀኪሞቹ ልጆቹ ተምታቶባቸው ግራ ተጋብተዋል። ማንኛዋ ሴት የትኛዋስ ወንድ እንደወለደች ማወቅ ተስኗቸው መፍትሄ ሊያበጁ ከመሐል ገብተዋል።
በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ ውጤት መጠባበቅ ጀመሩ። አሁንም ግራ አጋቢ ነገር ተፈጠረ። ተቀራራቢ ውጤት በመታየቱ ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆኗል በማለት ለሆስፒታሉ ሃላፊዎች አሳወቁ።
ኃላፊዎቹም ረጅም ሰዓት ከተወያዩ በኋላ ይህንን ችግር መፍታት የሚችሉት ሙስሊም ዓሊሞች ናቸው በሚል ከመግባባት ላይ ደረሱ። ወደ አንድ ሙስሊም ሊቃውንትም አቀኑ። የተፈጠውን ሁሉ በዝርዝር አስረዱ። ምናልባት በሃይማኖታችሁ መፍትሄ ካለው ብለን እዚህ መጣን አሉ።
እሱም ክስተቱን አዳምጦ እንዳበቃ "መፍትሄው በጣም ቀላል ነው" አለ።ዶክተሮቹ እርስ በእርስ ተያዩ ንግግሩን ቀጠለ "አላህ በልጆቻችሁ ያዛችኋል፡፡ ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው" የሚለውን የቁርአን አንቀፅ ከነትርጉሙ አነበበላቸው "ከሁለቱም እናቶች የወተት ጠብታዎችን ውሰዱና መርምሩ። በጣም የበለጸገና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘችው የወተት ጡት ወንድ ልጅን የወለደችው እርሷ ናት" አለ። ንግግሩን ሰምተው እንዳበቁ አመስግነው ወደ ሐኪም ቤት አመሩ።
ከሁለቱም እንስቶች የወተቱን ናሙና ወስደው ላብራቶሪ አስገብተው መረመሩ። በመካከላቸው ያለውን ልዩነትም ተመለከቱ። ወንድና ሴት ልጅ የወለደው ማን እንደሆነ በዚህ መንገድ አወቁ።
"(ይኽም) ከአላህ የተደነገገ ነው፤ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና" [ሱረቱ ኒሳእ]
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ተገባ