sebrin yasin Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

sebrin yasin shared a
7 month Translate
Translation is not possible.

ኢማም አህመድ -رحمه الله- ተጠየቁ

ከሰዎች ሰላም ለመሆን መንገዱ እንዴት ነው?

እንዲህ ብለው መለሱ

ትሰጣቸዋለህ ከነሱ አትወስድም،

? አዛ ያደርጉሀል አዛ አታደርጋቸውም،

ጥቅማቸውን ታስጠብቅላቸዋለህ ያንተን ጥቅም እንዲያስጠብቁልህ አትጠይቃቸውም

ጠያቂው: ኢማም ሆይ ይሔ ይከብዳል

ኢማም አህመድ: ታዲያ እንዴት ሰላም ትሆናለህ (ሰላም አትሆንም)!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
sebrin yasin shared a
Translation is not possible.

የተክሪት ሀገረ ግዛት አስተዳዳሪ የሆነው ነጅሙ ዲን ለረጅም አመታት ያለ ሚስት ቆይቷል። (525 አ.ሂ)

«ወንድማለም ለምን አታገባም?» ብሎ ጠየቀው ወንድሙ።

«ምትሆነኝን አላገኘሁማ!» አለው፤ እንደዘመናችን ወንዶች።

«ታድያ እኔ ልጭልሃ!» ወንድማዊ እዝነት።

«ማንን» ብሎ ጠየቀው።

«የንጉሰ ነገስቱን ምክትል ጠቅላይ አስተዳዳሪ ልጅ የሆነችውን ልጭልህ» ሲል ተማፀነው ወንድማለም።

«አይ አትሆነኝም ስልህ» ብሎ አሻፈረኝ አለው።

በአግራሞት እና በወንድማዊ እዝነት እየተመለከተው፦ «ትድያ ላንተ ማን ናት ምትሆንህ?»

«ለኔ ምትሆነኝ ምርጥ መልካም የሆነች ሚስት፤ እኔን እጄን ይዛ ወደ ጀነት የምትሄድ እና ከኔ ጀግና ልጅ ወልዳ በመልካም አስተዳደግ አሳድጋ ልጄንም አጀግና ያ ጀግና ልጇም በይተል መቅዲስን ለሙስሊሞች የሚያስረክብ ከሆነ ነው።» ህልሙን ነገረው።

ወንድም ንግግሩ ምንም አልጣመውም፤ ከባድ ህልም ነው ማይታሰብ።

«ታድያ እንዲህ ያለች ሚስት ከየት ነው ሚመጣልህ?» ጠየቀው።

«ኒያውን ለአላህ ያጥራራ፤ አላህ ይለግሰዋል» ብሎ መለሰለት።

ያ ቀን አለፈ።

ከዕለታት አንድ ቀን አስተዳዳሪው ነጅሙ ዲን ከመስጅዱ ቁጭ ብሎ ከአንድ ሸይክ ጋ እያወጉ ሳለ ድንገት ከመጋረጃው ጀርባ አንዲት እንስት መጥታ ሸይኩን ጠራችው።

ሸይኩ አስተዳዳሪውን አስፈቅደውት ልጅቱን ሊያገኟት ጠጋ አሉ። ሸይኩ ከሷ ጋ ሲያወጉ ድምፃቸው ለአስተዳዳሪው በግልፅ ይሰማ ነበር።

«ልጄ ትናንት እንዲያገባሽ ቤታችሁ የላኩትን ወጣት ለምን እንቢ ብለሽ መለሽው? »

«ኡስታዝ ልጁ ቆንጆ፣ ሀብታም እና መልከ መልካም ነው፤ ግና ለኔ አይሆነኝም» ብላ ትመልስላቸዋለች።

«ታድያ ምን አይነት ነው አንች ምትፈልጊው!» ሸይኩ ይጠይቋታል።

«ኡስታዝ! እኔ ምፈልገው ባል እጄን ይዞ ወደ ጀነት የሚመራኝ፣ ጀግና ልጅን ከሱ የምወልደውን፣ ልጁም ጎርምሶ ሲጀግን በይተል መቅዲስን ለሙስሊሞች የሚያስረክብ ሲሆን ነው» ፈላጊ እና ተፈላጊ ግጥምጥም አሉ።

«ኧረ ኡስታዝ እችን ልጅ ለኔ ይዳሩኝ» አላቸው።

«ይህች እኮ የከተማው ድሃ ልጅ ናት» አሉት፤ የግዜው ንጉሳን የድሃ ልጆችን እንደማያገቡ ስለሚያውቁ።

«አይይይይ...እኔ ምፈልጋት በቃ ይች ናት» ሙጥኝ አለ።

የሀገረ ግዛቱ አስተዳዳሪ ነጅሙ ዲን ልጅቱን አገባት። በመቀጠልም አንድ ቆንጅዬ ልጅ ወልደው ልጁ ሲጎረምስ ለዘመናት ከሙስሊሞች እጅ ተነጥቆ የቆየውን በይተል መቅዲስን ወደ ሙስሊሞች እጅ አስመለሰላቸው።

#ሰላሁዲን_አል_አዩቢ.....ከሁለቱ ጥንዶች ተወልዶ እናት እና አባቱ ያሰቡትን አሳካ ዱአ ይዘገያል እንጂ አይቀርም ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
sebrin yasin shared a
7 month Translate
Translation is not possible.

ኢማም አህመድ -رحمه الله- ተጠየቁ

ከሰዎች ሰላም ለመሆን መንገዱ እንዴት ነው?

እንዲህ ብለው መለሱ

ትሰጣቸዋለህ ከነሱ አትወስድም،

? አዛ ያደርጉሀል አዛ አታደርጋቸውም،

ጥቅማቸውን ታስጠብቅላቸዋለህ ያንተን ጥቅም እንዲያስጠብቁልህ አትጠይቃቸውም

ጠያቂው: ኢማም ሆይ ይሔ ይከብዳል

ኢማም አህመድ: ታዲያ እንዴት ሰላም ትሆናለህ (ሰላም አትሆንም)!

Send as a message
Share on my page
Share in the group