UMMA TOKEN INVESTOR

2 day Translate
Наган дахаан йохтахам.

ከ ሶሻል ሚድያ ያገኘሁት አስተማሪ የ ሂወታችን መንገድ ለወዳጅ ዘመድ ሼር ማድረግ አንርሳ :-

አሜሪካዊው ቢሊዬነር #ስቲቭ_ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))

በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣

,

አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥

,

✔አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥

,

✔ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥

,

✔አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣

,

✔በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣

,

★ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣

,

★ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ

,

👉እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል

,

👉በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣

,

👉የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣

,

👉ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣

,

👉ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣

,

…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል

,

👉አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ፣

,

✋እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥

ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣

,

5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …

☝ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣

,

☝ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣

,

☝የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣

,

☝"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥

,

☝ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣

,

☝በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

ወንድሙን ለመከፈን ተራውን እየጠበቀ👇😭😭

🇵🇸

ዘኩ የከዲጃ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

ኢስራዔል ያለ ርህራሄ በቦምብ ሳታፈራርሰው በፊት

ይህ ከተማ ለብዙዎች መኖሪያ ነበር😭👇

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

የኡም ዩሱፍ ታሪክ💔💔

- እማዬ, ርቦኛል, መብላት እፈልጋለሁ.

- አትፍራ ሀቢቢ...ቆየኝ እሺ ትንሽ የቲማቲም ስልስ እሰራልሃለሁ....

የዩሱፍን ረሃብ ለመዝጋት ሁለት ቲማቲሞችን ፍለጋ ወደ ጊዜያዊ ጎረቤቴ ወደ ኡሙ መሀሙድ ቤት ወጣሁ....

አባቱ ሆስፒታል ውስጥ ሆኖ ግዳጁን እየፈፀመ ስለነበርና ከኔ ውጪ ማንም መሄድ ስለማይችል እስክመለስ ድረስ በሩን አጥብቆ እንዲዘጋው ነግሬው አላህ እንዲጠብቅልኝ እየለመንኩት ፈጥኜ ወጣው።

የኡም መሀሙድን በር ደጋግሜ አንኳኳሁ ነገር ግን ማንም መልስ አልሰጠኝም.....ከእሱ መራቅን እጠላለው ነገር ግን በቤቱ ውስጥ የሚበላ ነገር የለም፤ ​​እነዚህ የጦርነት ቀናት በጣም ከባድ ናቸው ከሁሉም ነገር በላይ.... ስለዚህ ከመንገዱ ማዶ ወደሚገኘው የአልሚቅዳድ ቤተሰብ ቤት ሄድኩኝ.... ለዩሱፍ ሁለት ቲማቲሞች አገኛለው ብዬ ተስፋ በማድረግ....

- እንዴት ነሽ እናቴ ልጆችሽስ እንዴት ናቸው... የቦምብ ጥቃቱ አልደረሰባችሁም...ደህና ናችሁ አይደል ?

- አልሀምዱሊላህ ደህና ነን...አላህ ይጠብቀን.... ብላ በአንድ ቃል መለሰችልኝ....

በጦርነት ውስጥ ያሉ ሰዎች የረዥም ጊዜ ንግግር ቅንጦት የላቸውም ፣እያንዳንዱ ሰከንድ የመጨረሻ ሊሆን ይችላልና....እኔም መልሱን ለኡሙ ሚቅዳድ ደገምኩና ቲማቲም ያላት እንደሆን ጠየኳት... እና ሰጠችኝ...

ቲማቲሙን ይዤ ኡሙ ሚቅዳድን ተሰናብቼ ልወጣ ስል.... ጠራችኝ እና...

ዱዐ አድርጊልን እስቲ ኡሙ ዩሱፍ - ስለ እኛ ጸልይ... እንደምታይው ሁኔታዎች ከባድ ናቸው ...

- አላህ ቤተሰባችሁን እና ህዝቡን ይጠብቅልን... ይህ ሁሉ ችግር ኢንሻአላህ በአላህ እርዳታ ያልፋል...

ከዚያም አንድ ትልቅ ፍንዳታ ተሰማ...

የማስታውሰው ነገር ቢኖር ጥቁር ደመና ሁሉንም ነገር እንደሸፈነው ነው...በፍንዳታው ሃይል ምክንያት ለጊዜው መስማት የተሳነኝ ቢሆንም አንድ ነገር በአእምሮዬ ውስጥ ነበር፡ የሱፍ ደህና ነው ወይስ አይደለም?

- ያጀማዐ ዩሱፍን አይታችዋል..? እዚህ አካባቢ አንድ ትንሽ ልጅ አይታችዋል?

ያ ኡማ ...አላውቅም የተጎዱት ወደ ሆስፒታል በመሄድ ላይ ናቸው, እዚያ ይከተሉዋቸው....

በዶክተርነት የሚሰራውን አቡ ዩሱፍ ትዝ አለኝ... ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ቤት አልተመለሰም.....

በአምቡላንስ ተቀምጬ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ የመኪናው በር ከመዘጋቱ በፊት የማስታውሰው የመጨረሻዋ ሰአት....በዩሱፍ ላይ የዘጋሁት በር አሁን ላይ እንደሌለ ነው....

የምድርን አደጋ በተፈጥሮዬ የእናትነት ደመነፍሴ ፈርቼ በሩንስ ዘጋሁት... ከሰማይ የሚመጣውን አደጋ እንዴት መዝጋት ልቻል?እየተብሰለሰልኩ ሆስፒታሉ ደረስኩ...

በአልሸፋ ሆስፒታል ሁለተኛ ፎቅ ላይ አባቱ አረንጓዴ ቲሸርቱን ለብሶ በጦርነት እና በማያቋርጥ ስራ ደክሞ ህይወቱን ለህዝብ አሳልፎ ሰጥቷል።

ዩሱፍ....የሱፍ.... ከስሙ ሌላ አንዲትንም ቃል አልተነፈስኩም... እዚህ የመገኘቴ ምክንያት ተረድቶታል.....መቼም ሰዎች የእግር ጉዞ ለማድረግ ወደ ሆስፒታል አይመጡማ....

የማፈላለግ ጉዞ ተጀመረ "ዩሱፍ የ7 አመት ልጅ ነጭ እና ቆንጅዬ የሆነ " አይታቹታል...? ለሚያጋጥመኝ ሰው ሁሉ ሀኪምም ይሁን ጋዜጠኛ ወይም የተጎዳ ሰው ይህን ቃል እደግመው ነበር የፈለኩት የሱፍ የት እንዳለ ማወቅ ብቻ ነበር።

ከበርካታ መታጠፊያዎች እና ክፍሎች በኋላ ደከመኝ... እግሮቼ ሊያነሱኝ ቢሞክሩም ፍርሃቴ ከብዶኝ በአቅራቢያው ባለ ወንበር ላይ ተደፋሁ።

አባቱ እሱን ለማፈላለግ በሄደበት ሳለ የዩሱፍ ህይወት በዓይኔ ፊት አለፈ፣

ከአመታት ትዳር በኋላ ያገኘውት የህይወቴ በረከት ነበር፣ እንደ ጨረቃ ቆንጆ ነበር፣ የሱ በህይወቴ ላይ መምጣቱ ለሀዘኔ ሁሉ ክፍያ ነበር....

ለዛም ነበር "ዩሱፍ" ብዬ የሰየምኩት....

አሳድጌው...

በሱም ተስፋን እተነፍስበት ነበር....

በህይወቴ በየቀኑ አዲስ ደስታ ነበረኝ...

ዩሱፍ በእጆቼ ሲያድግ አይቻለሁ...

ዩሱፍ መጫወት እና ማውራት ከጀመረ የትምህርት ጊዜው ደርሶበታል.... ዘንድሮ ትምህርት ቤት መላኩ ከብዶኝ ነበር .....

በየቀኑ ስምንት ሰአት ከሱ ርቄ እንዴት እሆናለሁ... በየቀኑ በሩ ፊት ለፊት እጠብቀው ነበር በእቅፌ የሚወደውን የቲማቲም ስልስ ይዤ..... እሱን ለመቀበል...

ለብቻዬ ተዉኝ.....

አቡ ዩሱፍ በህመም ሲናገር የሰማዋት ቃል ነበረች.. እየጮህኩ ወደ እሱ ዘልዬ ገባሁ.... ምናልባት እኮ እሱ አይደለም....እያልኩ እየጮህኩ... አባት አይደል...እንዴት የልጁ መልክ ይጠፋዋል... አይሳሳትም።

የእናትነት ደመነፍሴ ነገረኝ.... ሁሉም ነገር እንዳለቀ....

የመጨረሻ የስንብት ጊዜ ፈልጌ ነበር ነገር ግን ከለከሉኝ... ነጩ ልጄ ....የጥቅልል ፀጉር ባለቤቱ ዩሱፍ.....ቦንብ ፊቱን ከማበላሸቱ በፊት ቆንጆ ምስሉን በአእምሮዬ እንዳስቀምጥ ፈለጉ....

ለማን እንደምጽፍ ባላውቅም እንደ እናት ሀዘኔ ሊተረጎም የማይችል ነው..... ታዲያ እንዴት ነው የምገልጸው?

ለዩሱፍ መምጣት ያሳለፍኩትን የትዕግሥት ዓመታት እንዴት ላስረዳው...?

ዩሱፍ ለኔ ከአላህ የተቸረኝ የ ሀዘኔ ቀያሪ ደስታዬ ነበር.... ታዲያ የተነጠቅኩትን ማን ይካስልኝ?

በፍቅር አሳደኩት... ለሱ ለመስጠት ብዬ ነፍሴን ነፈግኩ....

ልክ እንደ ልጆቻችሁ normal ልጅ እንዲኖር ብዬ ብዙ መከራዎችን ታገስኩ....

የእናትነት ቀልቤ ይዞኝ እሱን ለመጠበቅ በሩን ዘጋሁት.... እሱም... በሩም... ሄዱ።

ዘኩ የከዲጃ

እናት ልጇን ከጦርነት እንዴት መጠበቅ ትችላለች?

በየእለቱ ከትምህርት ቤት ሲመለስ የሱፍን በር ላይ ጠብቄአለሁ...እሺ ካሁን ቡሀላስ....?

ዩሱፍ ተርቦብኝ ሄደ...🥺

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

የጋዛ እናት😭

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group