UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Translation is not possible.
♥️ባዶ'ኮ ነው ዋሽንት
ኦና'ኮ ነው ውስጡ፣
ትንፋሽ ስታውሰው
ህይወት ቢሰጥህም
በዜማ በድምጡ፣
ታድያልህ...
ብልህ ምን ይማራል ከንዲህ ያለው ኻለት፣
'ባዶነት አይደለም ባዶ መኾን ማለት!'
#Rumi🌹
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
. . .ምን ተሻለኝ!
|
ሲጠራኝ ጊዜ መልኩን ሲያሳየኝ
ድቅድቅ ለሊቴ. .. .
ኮከብ የራቀው ምሽቴ
ማዕበል የሞላው ባህር ይሆናል ፡
ጠፍቶኝ ምሆነው ከአካሌ ሩሄ ይርቃል
እንደው ምን ላድርግ...ምንስ ተሻለኝ
አሽረኝ አሽረኝ!
እኔኑ ገድለህ ላ'ንተ አኑረኝ!
እርሱን ባላየው ዝምታና ሀዘን ውስጤ ይዘልቃል፣
የልቤ ጩኸት ፡
ምድርን አልፎ የሰማይን በር ይደልቃል...
ፈራሽ ገላዬ ሊያጥረኝ አይችልም፣
አጽናፈ ሰማይ አይከልለኝም..
ላይ እዘልቃለሁ
ሁሉን አውቃለሁ. . . ስል ተሰብሬ
አላውቅምን ሳውቅ ቀና መስመሬ
እምባዬ ማብቅያ እንደሌለው የክረምት ዝናብ ይፈስሳል
አባሽ ናፋቂ ጉንጮቼ በናፍቆት እምባ ረስርሶዋል ፤
ኩምትር አካሌ የቅጣት መላእክት
ወደ ገሃነም ልክ እንደ ጣሉት
"ስቃይን ቅመሷት" እንደተባሉት ሆኖዋል...
ባይተዋርነት ውስጤ ዋልሏል. . .
ትልቁ ፍርሀት. .
ትልቁ ቅጣት
ቅጣተ ፍቅር
በተፈቃሪ አለመፈቀር. . . |
አትቅጣን ጌታዬዋ!
•[ አብዱ ሩሚ ]•
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group