UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Seyifedin Ali shared a
Translation is not possible.

የከሰረው ነጋዴ‼️

አስመዒ የተባለው አሊም الله ይዘንለት መንገድ እየሄደ ያጋጠመውን ገጠመኝ እንዲህ ብሎ ያጫውታል።

👇

👇

👉" መንገድ ላይ እየሄድኩኝ አንዲት ልጅ በዘንቢል ነገር ሩማን የተባለው ፍሬ ተሸክማ ትሄዳለች።

አንድ ጎረምሳ ከኋላዋ ይከተላትና እሷ ሳታየው ከያዘችው ሩማን አንድ አንስቶባት(ሰርቆ) ይሄዳል። እኔም ጎረምሳውን ተከትዬ መሄድ ጀመርኩኝ።

ከሆነ ቦታ ላይ ሲደርስ አንድ ምስኪን ሰውዬ ያገኝና ከልጅቷ የሰረቀውን ሩማን ለምስኪኑ ሰውዬ ሰጠው።እኔም ተገረምኩኝና እንዲህ ብዬ ጠየኩት።

ከልጅቷ ስትሰርቃት እኮ እርቦህ መስሎኝ ነበር ግን ለሌላ ሰው ሰጠክ ስለው

👉 {እኔማ ከጌታዬ ጋ እየነገድኩኝ ነኝ} አለኝ

እንዴት ነው ከጌታህ ምትነግደው? ስለው

=> {ከልጅቷ ስሰርቃት 1 ወንጀል ተፅፎብኛል፣ ሰደቃ ሳደርገው ግን 10 አጅር ተፅፎልኛል ዘጠኝ አተረፍኩ ማለት ነው} አለኝ

እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት

👇

👉 ከልጅቷ ስትሰርቃት 1 ወንጀል ተፅፎብሀል ሰደቃ ስታደርገው ግን ምንም አጅር አልተፃፈልህም።

   ምክንያቱም

    👇👇👇👇👇👇

إن الله طيب لا يقبل إلا طيبا

/አላህ ንፁህ ነው ንፁህ የሆነ ነገር እንጂ አይቀበልም/

ብዬው ተለያየን"  ይላል

👌 የሚገርመው ይህ አይነቱ ተግባር በዘመናችን በጣም በዝቶ ይታያል

ብዙሀኖች ለራሳቸውም ይሁን ለሌላው ያለ ዕውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፣

ለባጢል ይከራከራሉ በነሱ ዕይታ ብቻ ሀቅ ስለ መሰላቸው

   ጠመውም ያጠማሉ

🤲 አላህ ጠቃሚ የሆነ ዕውቀትና ተቀባይነት ያለው ስራ ይወፍቀን

منقول

https://t.me/httsibnutemamAbumahi114

Telegram: Contact @httsibnutemamAbumahi114

Telegram: Contact @httsibnutemamAbumahi114

ሀሳብ መቀበያ @muke_1 ‍ ኢስላማዊ ጠቃሚ መረጃ የሚለቀቅበት ይሆናል ቻናሉን join @ share ሀቅን መርዳት ቢያቅትክ ሀቅን አትገፍትር ለእውነት መቆም ቢያቅትክ ለውሸት አጨብጫቢ አትሁን? አቡ ማሂ ሙከረም ኢብኑ ተማም
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group