UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
1 year Translate
Translation is not possible.

አልሐምዱ ሊላህ ተነሳን! በሕይወት ተኝቶ ሞቶ ያደረ ስንት ሰው አለ!

ምስጋና ከገደለን በኋላ ሕያው ላደረገን አሏህ ይሁን ። መመለሻችንም ወደርሱ ነው።

ምስጋና ላበላን፣ ላጠጣን ለደገፈን፣ መጠጊያ ለሰጠን አሏህ ይሁን። ስንት አለ መጠጊያና መደገፊያ የሌለው !

ምስጋና ወደርሱ ለመመለስም፣ ስህተቶቻችንን ለማረምም፣ ነገሮችን ለማስተካከልም ተጨማሪ ቀን ተጨማሪ ዕድል ለሠጠን አሏህ ይሁን።

አምልኮ ማለት ከአሏህ ፈላጊ ሆኖ መዋል ማደር ሁሌም የሱ ጥገኛ ሆኖ መዝለቅ ነው።

በራሴ የቆምኩ ራሴን የቻልኩ ነኝ የሚል ማን አለ?

   🌹ሰባሐል ኸይር🌹

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ጋዛ የኢማሙ ሻፊዒይ ሀገር ናት!

-----

በጋዛ የተወለዱት የአህሉ ሱንና ወል ጀመዓ ኢማም ሙሐመድ ኢብን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ እንዲህ ብለው ነበር።

"ከቁርአን ውስጥ አንዲት አያት አለች። በበዳዮች (ለዟሊሞች) ላይ አውዳሚ ቀስት ስትሆን፣ ለተበዳዮች ደግሞ ተስፋ ናት"

"ያቺ አያት (አንቀጽ) የትኛዋ ናት?" ተብለው ሲጠየቁ የሚከተለው አንቀጽ መሆኑን ተናገሩ።

” ﻭﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﺭﺑﻚ ﻧﺴﻴﺎ “

“ጌታህም ረሺ (ዘንጊ) አይደለም”

(መርየም 64)

-------

አዎን! ጌታችን በዳዮች የሚሰሩትን እያንዳንዱን ግፍ እየተመለከተ ነው። ደግሞም በዳዮች ከሰሩት ግፍ አንዱንም አይረሳም። ሁሉም ነገር በእርሱ ዘንድ እየተመዘገበ ነው። እርሱ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ ደግሞ ለግፈኞችና ለበዳዮች የእጃቸውን ይሰጣቸዋል።

አብሽር! አብሽር!

-----

ፎቶው የጋዛ ከተማ ከሜድትራኒያን ባሕር ስትታይ የነበራትን ገጽታ ያሳያል። ዛሬ ሁሉም ነገር አፈር እየለበሰ ነው።

ይህም ያልፋል እንግዲህ።

Free Palestine.

End the Occupation

Via afendi muteki

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group