UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Musema Jemal shared a
Translation is not possible.

#ከተረሱ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች ዉስጥ:-✍️

1. አልፎ አልፎ በባዶ እግር መጓዝ

2. በሶስት ጣቶች ብቻ ምግብን መመገብ እና ጣቶችን በሶፍት ወይም በሌሎች መሰል ማበሻዎች ከማጽዳት በፊት በምላስ መላስ

3. ከእንቅልፍ ሲነቁ ፊትን በእጆች ማበስ

4. ወንጀል ላይ ከወደቁ በኋላ ዉዱእን ባማረ መልኩ አድርጎ ሁለት ረከዓ የተውባ ሶላቶችን መስገድና ቀጥሎም የአላህን ማርታ መጠየቅ

5. ከተቀመጡበት ሲነሱ ፣ቁርአንን አንብበው ሲጨርሱ ወይም ዉዱእን ሲያጠናቅቁ ሱብሀነከ አላህመ ወቢሀምዲከ ላኢላሃ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ የሚለዉን ዱዓእ ማድረግ

6. በሌሊት ሰአት እቃዎችን ሁሉ መክደን ወይም መታሰር የሚችሉ ነገሮችን ማሰር

7. ለሁሉም ሶላቶች እና ለሁሉም ዉዱእ ጥርስን መፋቅ

8. ለእያንዳንዱ ፈርድ ሶላት ዉዱእን ማደስ

9. ሰዎች ቤት ለመግባት ሲያስቡ ሶስት ጊዜ ፍቃድን መጠየቅ

10. ከቤት ሲወጡ ወይም ወደ ቤት ሲገቡ ሁለት ረከዓ መስገድ

11. ቤት ሲገቡ በሲዋክ መጀመር

12. ለህጻናቶች ኢስላማዊ ሰላምታን ማቅረብ

13. ተራራማ (ዳገትማ ) ቦታዎች ላይ ሲወጡ ትንሽ ድምጽን ከፍ አድርጎ አላህ አክበር ማለት እና ረባዳ ወይም ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ሲደርሱ ሱብሀን አላህ ማለት

14. ለሚያውቁትንም ይሁን ለማያውቁት ሰው ኢስላማዊ የሆነዉን ሰላምታ ማቅረብ

15. ቁጭ ብሎ መጠጣት

16. ሶላት ላይ ወስዋስ ሲያጋጥመው ከሸይጧን በአላህ ከተጠበቁ በኋላ ወደ ግራ ጎኑ ሶስት ጊዜ ቱፍ ቱፍ ማለት

17. ሲተኙ በዉዱእ ሆኖ መተኛት

18. ፈገግታን ማንጸባረቅ

19. በጫማዎች መስገድ

20. ምግብን አለማነወር

21. ከእንቅልፍ በፊት የሚነበቡ ምእራፎችን ማንበብ

22. የዱሀ ሶላትን መስገድ

23. ገላን ከመታጠብ በፊት ዉዱእ ማድረግ

24. አድስ ልብስ ሲለብሱ ዱዓእ ማድረግ

25. የዶሮ ጩኸትን ሲሰሙ ዱዓእ ማድረግ / የአህያን ድምጽ ሲሰሙ ከሸይጧን መጠበቅ

26. ከእያንዳንዷ ሶላት በኋላ አያተልኩርሲይን መቅራት

27. ከመንገድ( ሰፈር ) ሲመለሱ መጀመሪያ መስጂድ ላይ ማረፍ እና ሁለት ረከዓዎችን መስገድ

28. ቋሚ የሆኑ ሱና ሶላቶችን ማዘውተር( በየእለቱ 12 ወይም 10 ረከዓዎቹን)

29. ሽበትን ከጥቁ ር ዉጭ ባለ ቀለም ማቅለም

30. ዊትር ሶላትን አዘውትሮ መስገድ

31. ወተት እና መሰል መጠጦችን ከጠጡ በኋላ መጉመጥመጥ

32. ሱና ሶላቶችን ቁጭ ብሎ መስገድ ( በእንቅልፍ ወይም በድካም ምክንያት

33. ለወንድም በስዉር ( በሩቅ) ዱዓእ ማድረግ

34. አስደሳች ዜና ሲያጋጥም የምስጋና ሱጁድ ማድረግ

35. አድስ ዝናብ በሚወርድበት ጊዜ ሰውነትን ገልጦ ማስመታት( ዐውራህ ያልሆነዉን )

36. የወደቀ ምግብን ካነሱ በኋላ የነካዉን ቆሻሻን አስወግዶ መብላት

37. ሌሊቱ ሲገባ ልጆች ከቤት እንዳይወጡ መቆጣጠር

38. ከመተኛት በፊት ፍራሹን መጥረግ

39. ለህመም ዱዓእ ሲያደርጉ እጆችን ህመም ከሚሰማብን ቦታ ላይ አስቀምጦ ዱዓዉን ማድረግ

40. ከእንቅልፍ ሲነሱ ወዲያዉኑ በአፍንጫ ዉሀን በመሳብ ከዚያም በኋላ ወደዉጭ ማስወጣት

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Musema Jemal Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group