UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
khalid Abdulkadir Сhanged his profile picture
7 month
Наган дахаан йохтахам.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

...ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም ...

ርእስ- ለዐለና ነተፈከር...

ታች ክፍል እንደነበርኩ ፊዚክስ ስንማር optics ላይ behaviour of magnetic wave አካባቢ 7 ከለሮችን ለመሸምደድ VIBGYOR የሚል ኮድ ተጠቅሜ ነበር ...

ስንተነትነውም ፦

1. V - violet 2. I - indigo

3. B - brown 4. G - green

5. Y - yellow 6. O - orange

7. R - red

ነዉ ።

ለማንኛውም ብዙ ጊዜ ቁርዐን ውስጥ ቁጥራዊ ተዐምር አለ ሲባል እንድናስተነትን ነውና ዛሬም እንድናስተነትን ይረዳን ዘንድ አንድ ቁጥራዊ ተዐምር ይዤ መጥቻለሁ ተከተሉኝ

☝ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ዋና ዋና ከለሮች የሚባሉት 7 ቱ የቀስተደመና ከለሮች ቀይ,ደማቅ ሰማያዊ,ቡናማ,አረንጓዴ ,ቢጫ , ብርቱካናማ እና ሀምራዊ ናቸዉ ። በሚገርም ሁኔታ በተመሳሳይ ቁርዐን ውስጥ አልዋን (ቀለም) የሚለው ቃል 7 ጊዜ ተጠቅሷል። የተጠቀሰበት ቦታም እንደሚከተለው ነዉ

1.ሱረቱ ነሕል አያት ቁጥር 13.

2.ሱረቱ ነሕል አያት ቁጥር 69.

3.ሱረቱ ሩም አያት ቁጥር 22.

4.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 27.

5.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 27.

6.ሱረቱ ፋጢር አያት ቁጥር 28.

7.ሱረቱ ዙመር አያት ቁጥር 21.

->7 ቀለማት 7 አልዋን (ቀለም) ከሚል የቁርአን ቃል ጋር ...

ይህ የአላህን ተዐምር በግልፅ የሚያሳይ ነዉ ።

👉በተጨማሪም ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) በሀዲሳቸው ጀሀነም መጀመሪያ ቀይ ከዛ ነጭ ከዛ ጥቁር እንደሆነ እና አሁን ጥቁር እንደሆነ አስገንዝበዋል ። ጀነትን ደግሞ ከአረንጓዴ ጋር ማያያዝ እንችላለን የቁርአን አያም ስላለ, እንዲሁም የጀሀነም በር ብዛት 7 ሲሆን የጀነት ደግሞ 8 ነው።

፨ በቁርዐን ውስጥ አረንጓዴ የሚለው ቃል 8 ጊዜ እንዲሁም ጥቁር የሚለው ቃል 7 ጊዜ ተጠቅሰዋል ።

✌ ይህም ሌላው የቁርዐንን ድንቅ ተዐምር የሚያሳይ ነዉ ።

~ሱብሐነ መን ዐዘ ፈርተፈዕ~

አላሁመ ጅዐልና ሚነል ሙህተዲን

ምንጭ : Dr. Abduldaim kaheel

ጸሀፊ : Eng. ረዩ ሀቢብ...

Send as a message
Share on my page
Share in the group