UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

بسم الله الرحمن الرحيم

*بعض أحكام الأضحية وفضلها*

*ኡድሂያ : በኡድሂያ ዙርያ መሰረታዊ ነጥቦች*

1 - ኡድሂያ ማለት በዙልሂጃ ወር አስርኛው ቀን ከሰላተል ኢድ በኋላ ወደ አላህ ለመቃረብ ተብሎ የሚታረድ እርድ ነው ።

2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍቅር ፣ፍራቻ፣ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ነው ። አላህ እንዲህ ብሏል፤

{ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37

(አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» )አል ሐጅ 37

4— የኡድሂያ ትሩፋቱ: ከዓኢሻ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-“ከነህር /እርድ/ ቀን ሥራዎች ውስጥ የአደም ልጅ ደምን ከማፍሠስ በላይ ወደ አላህ ተወዳጅ የሆነ አንድም ሥራ አልሠራም። እርዷም የቂያማ ቀን ከነቀንዷ ፣ ፀጉሯና ጥፍሯ ትመጣለች። ደሙም መሬት ላይ ከማረፉ በፊት ከአላህ ዘንድ ቦታ ይይዛል። በዚህም ነፍሣችሁን አስደስቱ (ደስ ይባላችሁ)።” ቱርሙዝይ ዘግበውታል ።

5— ኡድሂያ ለማረድ የተዘጋጀ ሰው ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን የሰውነቱን መንካት የለበትም። ከኡሙ ሰለማ (ረ.ዓ) በተላለፈው ሀዲስም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡-“አንዳችሁ ኡድሂያ ለማረድ አስቦ አሥርቱ ቀናት የገቡ እንደሆነ ከፀጉሩም ሆነ ከሰውነቱ አንዳቸም ነገር አይንካ።” ብለዋል። (ሙስሊም እና ነሣኢ ዘግበውታል።)

6- ወቅቱ ፣ ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው ። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

7- የመጨረሻ ቀኑ ከዒድ (10 ዙልሂጃ) ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛ ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

8- የሚታረደው እንስሳ ጾታው ወንድ ወይም ሴት መሆን ይችላል ። እድሜ ፣ ግመል ከሆነ5 አመት ፣ ከብት 2 አመት ፣ በግ 6 ወር ፍየል 1 አመት የሆናቸው ለኡድሂያ እርድ ይሆናሉ ።

9- ለኡድህያ ማይሆኑ እንስሳዎች፣ የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት ለኡድሂያ እንዳናርድ ከልክለዋል።

ሀ— አንድ አይኑ የታወረ፣ የታመመ

ለ— ስብራት ያለበት፣ የሚያነክስ

ሐ—የከሳና የደከመ

መ—የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

10- የኡድሂያ አንድ እንስሳን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ግመል ወይም ከብት መጋራትም ይቻላል በግ ወይም ፍየል ግን ለአንድ ሰው ብቻ ነው ።

11–ለገፋፊው የድካሙ ዋጋ ከስጋው ወይም ቆዳው መሆን የለበትም የልፋቱ ዋጋ ከዚህ ውጭ በሆነ ነገር መሆን አለበት : ዋጋው ተከፍሎት በተጨማሪ ስጋ ወይም ቆዳው ቢሰጠው ችግር የለውም።

12- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ ነይቶ ሊያርድ ይችላል።

13- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ምግቡን አዘጋጅቶ ሰው ጠርቶ ማብላት ጥሩ ነው ።

14— ከዚህ በዓል (ኢድ አል አድሃ) ጋር ተያይዞ አላህን መዘከር ማብዛት እና አቅም በፈቀደው መጠን ቤተሰብን ዘና ማድረግ ተወዳጅ ነው ፣ ውዱ ነብያችን ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ ፣

(أيَّامُ التَّشريقِ أيَّامُ أكلٍ وشُربٍ وبِعالٍ)

★ ሸርጡን ጠብቆ ከሚተገብሩት አላህ ያድርገን

t.me/ustazmuhammadferej

Send as a message
Share on my page
Share in the group