ሙስሊም ሰው Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ሙስሊም በመሆኔ ብቻ ጌታዬን አመሰግነዋለው። በቢሊዮን የሚቆጠሩ ካፊሮች ባሉበት አለም ላይ እኔን አመፀኛ ባሪያውን እስልምናን የሰጠኝ ቢወደኝ ነው ብዬ ስለማስብ በጌታዬ ደስ ይለኛል።!

Translation is not possible.

በርሊን (IP) - በጀርመን ፀረ-ጽዮናዊ ሰልፎችን ማካሄድ የተከለከለ ቢሆንም የፍልስጤም ደጋፊዎች እንደገና በርሊን ውስጥ ተሰብስበው ለጋዛ ህዝብ አጋርነታቸውን አወጁ።

ኢራን ፕሬስ/ አውሮፓ፡  የፍልስጤም ደጋፊ ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ደጋፊዎች ቅዳሜ ማምሻውን በመሀል በርሊን ተሰብስበው በጋዛ ሰርጥ የጽዮናውያን መንግስት የፈፀመውን ወንጀል አውግዘዋል።

ሰልፈኞቹ የፍልስጤም ባንዲራ በመያዝ የጋዛ ጦርነት እና የፍልስጤም እልቂት እንዲቆም ጠይቀው “ ነፃ ፍልስጤም ” የሚል መፈክር አሰሙ።

የአመፅ መሳሪያ የለበሱ መኮንኖች በተሰበሰበው ህዝብ ፊት ራሳቸውን አዘጋጁ።

በጀርመን ዋና ከተማ ከ8,000 እስከ 10,000 የሚገመቱ ሰዎች ሰልፍ ወጡ። ፀረ እስራኤል ንግግሮችን ለመከላከል በከፊል 1,000 የሚሆኑ ፖሊሶች ተሰማርተዋል።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ አብዛኛው የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፎች በበርሊን ታግደዋል ምክንያቱም የአካባቢው ባለስልጣናት የኃይል ፍንዳታ ወይም ፀረ ሴማዊነት ይነሳሉ። ይሁንና ውሳኔው የመሰብሰብ ነፃነትን የሚጋፋ ነው ተብሎ ተችቷል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የቅዳሜውን ሰልፍ ጨምሮ በርካታ ተቃውሞዎች ተፈቅደዋል።

ዘገባው የኢራን ፕሬስ ነው!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኦክቶበር 30፣ 2023 ቋንቋዎች

ዩኒሴፍ፡ በጋዛ የህጻናት ሁኔታ በጣም አስፈሪ ነው።

ሰኞ፣ ኦክቶበር 30፣ 2023 10:14

ፌስቡክ ትዊተር ኢሜል ዋትስ አፕ አጋራ

አይፒ - የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ እንዳሉት፡ የሆስፒታሎችን ጥበቃ፣ በጋዛ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የሰብአዊነት መሻገሪያዎች እንዲፈጠሩ እና ለሲቪሎች ሰብአዊ ርዳታ ቀጣይነት ያለው እና ቀጣይነት እንዲኖረው እንጠይቃለን።

የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ቶቢ ፍሪከር የጽዮናውያን አገዛዝ በጋዛ ባደረገው ጥቃት ሰማዕት የሆኑ ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡ በጋዛ ያሉ ሕጻናት ሁኔታ አስከፊ ነው በዚህ አካባቢ የብዙ ሕጻናት ግድያ እጅግ አስከፊ ነው።

ከጥቅምት 7 ጀምሮ በጋዛ ውስጥ ቢያንስ 8,005 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል.በእስራኤል ውስጥ በሃማስ ጥቃት ከ 1,400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል, የፍልስጤም ምንጮች እንደገለጹት.

እስራኤል "በአፋጣኝ" እንድትለቀቅ ካዘዘች በኋላ እና የቦምብ ድብደባው በቀጠለበት በጋዛ አል ቁድስ ሆስፒታል ላይ ሊደርስ ይችላል የሚል ፍራቻ እያደገ ነው ። የዓለም ጤና ድርጅት "በጣም አሳስቦኛል" ብሏል።

እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ በየአመቱ በዓለም ዙሪያ በተከሰቱ ግጭቶች ከሚሞቱት አጠቃላይ ህጻናት በጋዛ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የተገደሉ ህጻናት ቁጥር ይበልጣል ሲል መንግስታዊ ያልሆነው የህጻናት አድን ድርጅት አስታወቀ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"ዓለም የሚጠፋው ክፉ በሚያደርጉ ሰዎች ሳይሆን ምንም በማያደርጉት በሚቆሙት ነው እንጂ"

አልበርት አንስታይን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሰላሙአለይኩም ወርሀመቱሊላሂ ወበረካቱ

እራሴን ወቀስኩት!!😭😭😭

እናቴ አላህ ይዘንላትና ወደ አኼራ ስትሄድ ገና የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ። ጊዜው ቅዳሜ ቀን የካቲት 18- 1992 በሰአቱ የኮልፌ ሙስሊም መቃብር ጊቢው ሞልቶ ከጊቢው ውጪ ሜዳ ላይ ነበር የሚቀበረውና እናቴም እዛ ቦታ ላይ አረፈች።

ከተቀበረች ቡሀላ በተደጋጋሚ በህልሜ እየመጣች ልክ ድሮ በህይወት እያለች እንደምታቅፈኝ ታቅፈኝ ነበር፤ ልክ እንደ ድሮ በህይወት እንዳለች ፀጉሬን እየደባበሰች ታወራኝ ነበር። በህልሜ ውስጥ ሆኜ እናቴ ከሞት የሞተመለሰችልኝ ይመስለኝ ነበር ደስታዬ ልዩ ነበር። ከእንቅልፌ ስነቃ ግን አንዴ ከወሰደ የማይመልሰው ጥፍጥና ቆራጩ መራራው ሞት የእውነት እንደወሰዳት ሳስብ ሆድ ይብሰኛል። ከዛ ቀብሯ ጋር በመሄድ አለቅስ ነበር።

በልጅነት አዕምሮዬ አላህ ለምን ሳናድግ ወሰደብን ምን ይጠቀማል?? እኛ እንድናለቅስ እንድናዝን ለምን ይፈልጋል ብዬ አስብ ነበር።

ጊዜ ጊዜን ሲተካ ጉርምስናም መጣ የቀብር ቦታውም ጊቢው ማስፋፊያ አድርጎ አጠረው የሷም ቀብር ያለበት ቦታ ጢሻ ሆኖ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆነና መሄዱ ቀረ። 18 አመት ቡሀላ ደግሞ ቦታው መልሶ በመጠቀም አሰራር ሌላ ሰው ተቀበረበት። ሄጄ ሳየው ከፋኝ በጣም እናቴ ቀብር እንኳን የላትም በቃ ብዬ አዘንኩኝ!!!

ዕድሜዬ ከፍ ሲል ሰላትን እንዳመቸኝ እሰግድ ነበር በቀን ከአምስቱ 3 ወይም ሁለት ያመልጠኝ ነበር። በትክክል የማያመልጠኝ የጁምአ ሰላት ብቻ ነበር።

አንድ ቀን ወንድሜና እህቶቼ ወላሂ ነው ምላቹ ረጅም ጊዜ አይቻት የማላውቀው እናቴ ከረጅም ጊዜ ቡሀላ በህልሜ መጥታ ራቅ ብላ ቆማ ጣቷን በምስጠንቀቅ ወደኔ እያመላከተች " ልጄ ነግሬሀለው ሰላትህን በደንብ ስገድ ቀብር ከባድ ነው " እያለች አስጠንቅቃኝ ሄደች። ይሄ ህልም ሶስት ቀን በተከታታይ አጋጠመኝ። ቆም ብዬ አሰብኩኝ ከዛ ጊዜ ቡሀላ ሰላቴን ቀጥ አርጌ ለመስገድ ወሰንኩኝ!!! አልሀምዱሊላህ እናቴን ስበብ አርጎ ወደ ሰላት የመራኝ ጌታ!🙏🙏

ወደ ዋናው ጉዳዬ ስገባ እናቴ ታማ አያቴ እና እህቴ አስታመዋት ስትሞት በወግ ማዕረግ ተከፍና ተቀበረች አልሀምዱሊላህ። ያኔ ያልገባኝ ማዕረግ ዛሬ ገባኝ!!

ዛሬ ጠዋት አብረው የነበሩ እናት እና አባት በቦንብ ድብደባ በእሳት እና ፍርስራሽ ውስጥ ሞተው በአግባቡ እንኳን ከፍኖ ለመቅበር ሲያስቸግር ሳይ ጌታዬ አስታሞ በወግ ማዕረግ መቅበር ለካ ማዕረግ ነው!!!

በልጆቻቸው በወንድሞቻቸው እና በወላጆቻቸው ሞት ሀዘን የማይበረታባቸው እነዛ ጀግና ህዝቦች ነገ በአላህ እዝነት በአኼራ እንደሚገናኙ እያሰቡ ፈገግ ሲሉ ሳይ እኔ 22 አመት ዱአ ከማረግ ይልቅ እንባ የሚቀድመኝ ምን አይነት ሰው ነኝ ብዬ እራሴን ወቀስኩት።

በከፈን እጥረት ሙሉ ቤተሰብ አንድ ላይ ሲከፈን ሳይ የእኔ እናት ምን አጣች ማመስገን እንጂ ጌታዬን ማማረሬ ልክ አለመሆኑ ገባኝና እራሴን ወቀስኩት።

በፍርስራሽ ውስጥ ሰውነታቸው በደም ተለውሶ ፊታቸውን መለየት እስከሚያስቸግር ጅናዛ ሲሰበስቡ ሳይ አልጋ ላይ በሞቀ ብርድ ልብስ ውስጥ በክብር ለሞተችው እናቴ አላህን ማማረሬን ሳስበው በራሴ አዘንኩኝ።

በፍርስራሽ ውስጥ ጀነዛ ፍለጋ ሲሰቃዮ ሳይ በክብር ለተቀበረችው ማመስገን ሲገባኝ ቀብሩ ተነሳ ብዬ ክፉኛ ማዘኔ ልክ አለመሆኑ ሲገባኝ አዘንኩኝ!!

ዛሬ ላይ ሆኜ ወደኋላ ሳየው ሁሉም ነገር እንድናመሰግን እንጂ እንድናማርር አለመሆኑ ገባኝ!!!

እነዛ በሀዘናቸው ውስጥ ቆራጥነት በህይወታቸው ውስጥ ጀግንነት በእምነታቸው ውስጥ መተማመንን ለያዙ ከህፃን እስከ ሽማግሌ ፈገግታ የማይለያቸውን ፍልስጤማውያንን ያየ ማመስገን እና ማመስገን ብቻ ነው አማራጩ!!🙏🙏

ሁላችንንም በጀነት ይሰብስበን!!🙏🙏

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሰላሙአለይኩም

ውድ የአኼራ ወንድምና እህቶቼ ስለዚህ ፕላት ፎርም ለሌሎች በማጋራት ሙስሊሙን ከፌስቡክ እንዲወጣ እየጣርን ነው?🤔🤔 ሁላችንም እንጠራራ!

Send as a message
Share on my page
Share in the group