ነፍስህም ሀቅ አላት። ሁሉም ሰው በራሱ በኩል አንተን ስሌት ውስጥ ሳያስገባህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በርካታ ነገሮች አሉት። ለሆኑ ድንገታዊ ስሜቶች ብለህ የምትከፍላቸው "እውር መስዋትነቶች" ሊኖሩ አይገባም ብዬ አስባለሁ። ራስህን እንደሻማ ስላቀለጥክ ቆሞ የሚያጨበጭብልህ አይኖርም። ቢኖርም ምንም አይጠቅምህም። የሻማን ፍልስፍና ተወውና ራስህን ሳትጎዳ ሌሎችን ስለመጥቀም አስብ። አንዳንድ ሰዎች ለሰዎች መልካም መሆንና ራስን መበደል መሀል ያለው ልዩነት ገና አልገባቸውም። ኧረ የነፍስህን ሀቅ በመወጣት አሳርፋት።