Translation is not possible.
በረመዳን ፍፃሜ እነዚህ ስራዎች ላይ ትኩረት ያሻሉ፦
"ተዋደየዕ" ​የትህትና አስፈላጊነት፦ ረመዳን ሲጠናቀቅ በሰራናቸው መልካም ስራዎች እና ኢባዳዎች (አምልኮዎች) ልባችን በትዕቢት እንዳይሞላ እስቲግፋር ማድረግ ይገባል። በሰራው ስራ የሚኩራራና ራሱን የሚያደንቅ ሰው ለጥፋት የተጋለጠ ነው።
​የስራዎቻችን ጉድለት ማስተዋል፦ በእውነተኛ ልብ ምህረትን የሚጠይቅ ሰው ስራው የቱንም ያህል የበዛ ቢሆን በውስጡ ጉድለት እንዳለበት ያውቃል። በአላህ ፊት በመተናነስ የቀረበ ጥቂት ስራ፣ በትዕቢት ከተሞላ ብዙ ስራ ይበልጣል።
​የምንዳ (አጅር) መብዛት፦
አላህ ለአንዳንዶች መልካም ስራቸውን እስከ 700 እጥፍ ያባዛላቸዋል፤ ለሌሎች ግን ላይባዛ ይችላል። ይህ የሚወሰነው በልባችን ውስጥ ባለው ቅንነትና ትህትና ነው።
​ሁልጊዜም ኢስቲግፋር ማድረግ ፦ ማንኛውም መልካም ስራ በእስቲግፋር ሊደመደም ይገባል። ነብዩ መሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ግዴታ የሆኑ ሶላቶችን እንኳን ሲጨርሱ ሶስት ጊዜ "አስቲግፊሩላህ" (አላህ ሆይ ምህረትህን እለምናለሁ) ይሉ ነበር።
​ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦ እስቲግፋር በምላስ ብቻ ሳይሆን በልብ የታጀበ መሆን አለበት። ማንኛውም ስራ ከመጀመሩ በፊት፣ በሂደት ላይ እያለ እና ከተጠናቀቀ በኋላም ጉድለቶች ሊኖሩት ስለሚችሉ ኢስቲግፋር የሙስሊሞች የዘወትር ተግባር መሆን አለበት።
ሸይኽ ዐብዱ አሰ–ሰላም አሽ–ሹወይዒር
Send as a message
Share on my page
Share in the group