☀️ #ዕለቱን_በታሪክ_ቁጥር1_ለ☀️
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ዛሬ በሒጅራ አቆጣጠር ጀማዱል ኣኺር 26ኛ ቀን ነው!
የዛሬ 612 አመታት ወደ ኋላ ስንመለስ በ835 ሒጅራ ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ገና በወጣትነቱ #ቆስጠንጥያን በመክፈት የረሱልን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የድል ትንብይት እውን ያደረገው ጀግና ሱልጣን #ሙሐመድ_አል_ፋቲህ የተወለደበት ቀን ነው።
ምንም እንኳን ሱልጣኑ የተወለዱት ረጀብ 26ኛው ቀን ነው የሚሉ መረጃዎች በመኖራቸው በታሪክ ምሁራን መካከል ሁለት አመለካከቶች ቢኖሩም ጀማዱል ኣኺር 26ኛ ነው ባሉት ምሁራን መሰረት ታሪኩን ከውልደት እስከ ህልፈት እና ከታሪኩ የምንማራቸውን ቁም ነገሮች ለማንበብ በሚመች አቀራረብ አዘጋጅቸላችኋለሁ።
ሱልጣኑ የተወለዱት ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ነው ያሉ ምሁራንን ማስረጃ መጨረሻ ላይ ታገኛላችሁ!
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ታላቁ የኡስማንያ መሪ ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ (መሐመድ ዳግማዊ) በታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው መሪዎች አንዱ ነው።የቁስጥንጥንያ(ኢስታንቡል) ድል አድራጊ በመሆኑም \"አል-ፋቲህ\" (ድል አድራጊው) የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል።
በዛሬው“ዕለቱን በታሪክ”አምዳችን የዚህን ጀግና ታሪክ በወፍ በረር ከውልደት እስክ
ህልፈቱ ላስዳስሳችሁ እሞክራለሁ መልካም ንባብ።
https://t.me/Seyfel_Islam
📌ክፍል1:የሙሐመዱል ፋቲህ ውልደት፣እድገት፣እንድሁም ስለ ወላጆቹ እና በግዜው ስለነበረው ሁኔታ በአጭሩ📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ መጋቢት 30 ቀን 1432 እ.ኤ.አ ወይንም በጀማዱልኣኺር 26/835ሒጅራ(በብዙ መረጃዎች ደግሞ ረጀብ 26፣835 ሂጅራ የሚል ተጠቅሶ እናገኛለን)በወቅቱ የኡስማንያ (ኦቶማን) ግዛት ዋና ከተማ በነበረችው #ኤድርኔ (Edirne) ተወለደ።
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ከመወለዱ በፊት የነበረው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ በትቂቱ ይሄን ይመስል ነበር:-
📍1ኛ:የቢዛንታይን ግዛት መዳከም⚡️
~~~~
በአንድ ወቅት ኃያል የነበረው የቢዛንታይን (የምስራቅ ሮም) ግዛት ተዳክሞ በቁስጥንጥንያ ቅጥር ግቢ ብቻ ተወስኖ ነበር።ሆኖም ከተማዋ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ምክንያት አሁንም ለንግድና ለጦርነት ቁልፍ ነበረች።
📍2ኛ:የኡስማንያ ግዛት መረጋጋት⚡️
~~~~
ግዛቱ ከአንካራ ጦርነት ሽንፈት (ከቲሙር ላንግ ጋር ከነበረው ግጭት) በኋላ መልሶ እያገገመና እየተጠናከረ የነበረበት ወቅት ነበር።
📌የነብዩ ሙሐመድ-ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም-ትንቢት📌
=======================
ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)“ቁስጥንጥንያ በእርግጥ ትከፈታለች፤እሷን የሚከፍተው መሪ ምንኛ ምርጥ መሪ ነው!ያ ሰራዊትም ምንኛ ምርጥ ሰራዊት ነው!”ሲሉ የተናገሩትን ትንቢት ለመፈጸም ለ800 ዓመታት ሲመኙ ነበር።
📌የወላጆቹ ሁኔታ📌
======================
📍አባቱ -ሱልጣን ሙራድ ዳግማዊ📍
~~~~
አባቱ ሱልጣን ሙራድ ጠንካራ መሪና ፍትሃዊ ሰው ነበሩ።ግዛቱን በማስፋፋትና የውስጥ አመጾችን በማርገብ ይታወቃሉ። ሙራድ ዳግማዊ ልጃቸው ሙሐመድ ለታላቅ ዓላማ እንዲበቃ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
📍እናቱ - ሁማ ሃቱን📍
~~~
ስለ እናቱ ማንነት የታሪክ ምሁራን የተለያዩ ሃሳቦችን ይሰነዝራሉ።ነገር ግን እርሷ በልጇ አስተዳደግና ስብዕና ላይ ትልቅ ሚና የነበራት፣ለልጇ ሃይማኖታዊና ስነ-ምግባራዊ እሴቶችን ያወረሰች እናት ነበረች።
📌አስተዳደግና ትምህርት📌
========================
የሙሐመድ አል-ፋቲህ አስተዳደግ “ለታላቅነት የታጨ”ሰው አስተዳደግ ነበር ማለት ይቻላል።
በልጅነቱ እልከኛና ትንሽ አስቸጋሪ እንደነበር ይነገራል።ነገር ግን አባቱ ሱልጣን ሙራድ በወቅቱ የነበሩ ታላላቅ ምሁራንን በመመደብ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ አድርገዋል።ለምሳሌ:
📍አቅ ሸምሰዲን⚡️
~~~~
ሙሐመድ ላይ ትልቁን ተጽዕኖ ያሳረፉት መምህራቸው ናቸው።እርሳቸው ለሙሐመድ “ቁስጥንጥንያን የምትከፍተው አንተ ነህ” የሚለውን መንፈስ በውስጡ የዘሩትና በመንፈሳዊ ጥንካሬ ያነጹት ሰው ናቸው።
📍ሁለገብ እውቀት⚡️
~
ሙሐመድ ሃይማኖታዊ እውቀትን (ቁርኣን፣ ሐዲስ፣ ፊቅህ) ብቻ ሳይሆን ሳይንስን፣ ፍልስፍናን፣ ጂኦግራፊንና ስነ-መንግስትን ተምሯል።
📍የቋንቋ ችሎታ⚡️
~~~
በቋንቋ በኩል እጅግ የተዋጣለት ነበር።ቱርክኛ፣አረብኛ፣ፋርስኛ፣ግሪክኛ፣ላቲን፣ሰርቢያኛ እና ዕብራይስጥ ቋንቋዎችን በደንብ ይናገርና ይረዳ ነበር።ይህም ለወደፊቱ ዲፕሎማሲያዊ ስራው ትልቅ በር ከፍቶለታል።
📍የተግባር ልምድ⚡️
~~~
ገና በ12 ዓመቱ አባቱ ለተወሰነ ጊዜ ስልጣን በውክልና ሰጥተውት ነበር።ይህ የልጅነት የንግስና ልምድ የአስተዳደርን ከባድነትና የፖለቲካን ሴራ ቀድሞ እንዲረዳ አስችሎታል።
📌ክፍል ሁለት፡ወደ ስልጣን መምጣትና ለታላቁ ድል የተደረጉ ዝግጅቶች📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
የሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ወደ ስልጣን መምጣትና ለቁስጥንጥንያ ከበባ ያደረገው ዝግጅት፣ በታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሆኑ ስልታዊ እቅዶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
⚡️ወደ ስልጣን መምጣት (ሁለተኛው ንግስና)⚡️
========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በ12 ዓመቱ ወደ መንበሩ ቢወጣም፣ በልጅነቱና በውጭ ወራሪዎች ስጋት ምክንያት አባቱ ሱልጣን ሙራድ ዳግማዊ ወደ ስልጣን ተመልሰው ነበር።በ1451 እ.ኤ.አ አባቱ ሲያርፉ፣በ19 ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሱልጣን ሆነ።
⚡️የውስጥ ተቃውሞ⚡️
~~~~ብዙዎች “ገና ወጣት ነው፣ግዛቱን መምራት አይችልም!” ብለው ንቀውት ነበር።
⚡️የቢዛንታይን ስህተት⚡️
~~~~
የቢዛንታይን ንጉስ ቆስጠንጢኖስ 11ኛ፣ ሙሐመድን እንደ ልምድ የሌለው ወጣት በመቁጠር የግዛቱን ወሰን ለማስገፋትና የተለያዩ ጥያቄዎችን ለማቅረብ ሞከረ። ይህ ስህተታቸው ለሙሐመድ ወሳኝ እርምጃ እንዲወስድ ምክንያት ሆነው።
⚡️ስልታዊ ዝግጅቶች(Strategic Preparation)⚡️
=========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ስልጣን እንደያዘ ዋነኛ ትኩረቱ \"የማይደፈረውን\" የቁስጥንጥንያ ግንብ ሰብሮ መግባት ነበር።ለዚህም የሚከተሉትን ተግባራት አከናወነ፡-
📌ነኛ:ሩሜሊ ሂሳሪ(Rumeli Hisarı) ግንብ መገንባት⚡️
========+===============
ቁስጥንጥንያ ከጥቁር ባህር የሚመጣላትን እርዳታ ለማቋረጥ፣ በቦስፈረስ ባህረ ሰላጤ (Bosphorus Strait) አውሮፓዊው ክፍል ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ምሽግ በ4 ወራት ውስጥ ብቻ አስገነባ።ይህ ምሽግ ከባህር የሚመጡ መርከቦችን ለመቆጣጠር አስቻለው።
📌2ኛ:ግዙፉ መድፍ(The Great Cannon/Urbans\'s Gun)⚡️
=======================
የቁስጥንጥንያ ግንቦች እጅግ ወፍራም በመሆናቸው በወቅቱ በነበሩ መሳሪያዎች አይሰበሩም ነበር። #ሙሐመድ_ኡርባን የተባለ #ሃንጋሪያዊ የመድፍ ባለሙያን ቀጥሮ፣በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ መድፍ አሰራ።ይህ መድፍ ግማሽ ቶን የሚመዝን ድንጋይ ከአንድ ማይል በላይ መወርወር የሚችል ነበር።
📌3ኛ:የባህር ኃይል ግንባታ⚡️
========================
ከተማዋ በሶስት አቅጣጫ በውሃ የተከበበች በመሆኗ፣ሱልጣኑ ከ400 በላይ ትናንሽና ትላልቅ መርከቦችን በማዘጋጀት የባህር ኃይሉን አጠናከረ።
⚡️ድንቅ ስልታዊ ብልሃት፡መርከቦችን በየብስ ላይ ማጓጓዝ⚡️
=======================
ይህ የሙሐመድ አል-ፋቲህ ድንቅ ወታደራዊ ጥበብ የታየበት ክስተት ነው።
ሆኖም ቢዛንታይኖች የ\"ጎልደን ሆርን\" (Golden Horn) የባህር ወሽመጥን በግዙፍ ሰንሰለት ዘግተውት ነበር። የኦቶማን መርከቦች ወደዚያ መግባት ሳይችሉ ቀሩ።
🔐ነገር ግን ሙሐመድ አልፋቲሕ ለዚህ መፍትሄ መርከቦቹን በባህር ፋንታ በየብስ (በመሬት) ላይ እንዲጓጓዙ አዘዘ።በአንድ ሌሊት ውስጥ፣በቅባት በተቀቡ እንጨቶች ላይ በማንሸራተት 70 የሚሆኑ መርከቦችን ከኮረብታ ጀርባ በማሳለፍ ወደ ወሽመጡ አስገባቸው‼አሏሁ አክበር!ምን አይነት ብልሃት ነው?!
ጠዋት ላይ የቢዛንታይን ሰራዊት መርከቦቹን ከጀርባቸው ሲያይ ድንጋጤ ውስጥ ወደቀ!
⚡️መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት⚡️
=========================
ሙሐመድ ሰራዊቱን ለማነቃቃት የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ትንቢት ዘወትር ያስታውሳቸው ነበር።መምህሩ አቅ ሸምሰዲን በየቀኑ በድንኳኖች ውስጥ እየተዘዋወሩ ሰራዊቱን በዱዓ እና በንግግር ያጠናክሩ ነበር። ሱልጣኑ ራሱ ሳይንቲስትና መሐንዲስ ስለነበር፣ የጦርነቱን ካርታና ምህንድስና በራሱ እጅ ይነድፍ ነበር።
⚡️የመጨረሻው ጥቃት መጀመር⚡️
========================
ሚያዝያ 6፣1453 እ.ኤ.አ ከበባው በይፋ ተጀመረ።ለ53 ቀናት የዘለቀው ይሄ ከበባ፣ ዓለምን ለዘላለም የሚቀይር የታሪክ ምዕራፍ መጀመሪያ ነበር!
📌ክፍል ሦስት፡ታላቁ ድል፣ የቁስጥንጥንያ መውደቅ እና የድል አድራጊው ሰብዓዊነት📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በዚህ ክፍል የ53 ቀናት ከበባ እንዴት ወደ ፍጻሜ እንደመጣ እና ዓለምን የለወጠው ያ ታሪካዊ ቀን እንዴት እንደነበረ በዝርዝር እናያለንደ
⚡️የመጨረሻው ጥቃት (ግንቦት 29፣ 1453)⚡️
=========================
ከ53 ቀናት ተከታታይ ከበባ እና ድካም በኋላ፣ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ሰራዊቱን ለታላቁና ለመጨረሻው ጥቃት አዘጋጄ!
📌መንፈሳዊ ዝግጅት:
~~~
ግንቦት 28 ምሽት ላይ፣ሱልጣኑ መላው ሰራዊት እንዲጾም፣እንዲጸልይና በየድንኳኑ መብራት እንዲያበራ አዘዘ።ሌሊቱን ሙሉ የ\"ተክቢራ\" ድምፅ በቁስጥንጥንያ ቅጥር ዙሪያ ያስተጋባ ነበር።አሏሁ አክበር!
📌የጥቃቱ ስልት፦
~~~
ጥቃቱ ጎህ ሳይቀድ በሦስት አቅጣጫ ተጀመረ።መጀመሪያ “አዘቦች”(መደበኛ ያልሆነ ሰራዊት)፣ቀጥሎ የአናቶሊያ ሰራዊት፣በመጨረሻም የሱልጣኑ ምርጥ የጦር ክፍል የሆኑት “ጃኒሰሪዎች” እንዲገቡ ተደረገ።
📌ግንቡ መጣስ⚡️
=======================
በኡርባን ግዙፍ መድፍ የተመታው የቅዱስ ሮማነስ ደጃፍ (St. Romanus Gate) በመጨረሻ #ፈረሰ።አሏሁ አክበር!
#ሀሳን_አል_ሉባትሊ የተባለ ወጣት ወታደር ከ30 ጓደኞቹ ጋር በመሆን፣ ቀስቶችና ድንጋዮች እየዘነቡበት የግንቡ አናት ላይ በመውጣት የመጀመሪያውን የኡስማንያ ሰንደቅ ዓላማ #ሰቀለ‼
ይህ ክስተት ለኦቶማን ሰራዊት ትልቅ ወታደራዊ ወኔ ሰጠ!
⚡️ወደ ከተማዋ መግባት⚡️
=========================
የቢዛንታይን ንጉስ ቆስጠንጢኖስ 11ኛ እስከ መጨረሻው ተዋግቶ በጦርነቱ ሜዳ ላይ #ወደቀ።በዚያው እለት ከሰዓት በኋላ፣ ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ በነጭ ፈረሱ ላይ ሆኖ በታላቅ ግርማ ወደ ከተማዋ #ገባ!!አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ!
⚡️የመጀመሪያው ስግደት⚡️
=========================ሱልጣኑ በቀጥታ ወደ #አያ_ሶፊያ(Hagia Sophia) አመራ።እዚያም ከፈረሱ ወርዶ ሱጁድ አደረገ!
አያ ሶፊያም ወደ መስጂድነት ተቀየረች! የመጀመሪያው የጁምዓ ሶላትም እዚያው ተሰገደ!!!
📌አዲስ ስም⚡️
~~~
ከተማዋ #ኢስላምቡል” (የእስልምና ከተማ)የሚል ስም ተሰጣት፣ይህም በኋላ ወደ “ኢስታንቡል” ተቀየረ።
⚡️የድል አድራጊው ሰብዓዊነትና ፍትህ⚡️
========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ከተማዋን ሲቆጣጠር ያሳየው ስነ-ምግባር በወቅቱ ለነበረው ዓለም አስገራሚ ነበር፦
📌የምህረት አዋጅ⚡️
~~~~
በአያ ሶፊያ ውስጥ ተሸሽገው በድንጋጤ ይንቀጠቀጡ ለነበሩ #ክርስቲያኖች “ወደ ቤታችሁ በሰላም ሂዱ፣ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ቅጣት የለም!ነፃነታችሁና ህይወታችሁ የተጠበቀ ነው!” የሚል የደህንነት ዋስትና ሰጣቸው‼
እስልምና እንድህ ነው!
📌የሃይማኖት ነጻነት⚡️
~~
የግሪክ #ኦርቶዶክስ_ቤተክርስቲያን_መሪ (Patriarch) እንዲመረጥ ፈቀደ! #የአይሁድና የሌሎች እምነት ተከታዮችም የራሳቸው ፍርድ ቤትና የሃይማኖት ነጻነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ “የሚሌት ስርዓት (Millet System)” ዘረጋ!
📌ከተማዋን መልሶ መገንባት⚡️
~~
ጦርነቱ ያፈራረሳቸውን ህንጻዎች በፍጥነት እንዲጠገኑ አዘዘ።ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ነጋዴዎችንና ሳይንቲስቶችን ወደ ኢስታንቡል ጋበዘ።
⚡️የድሉ ውጤቶች(Global Impact):
የመካከለኛው ዘመን ማብቂያ⚡️
========================= የታሪክ ምሁራን የቁስጥንጥንያ መውደቅን የ\"መካከለኛው ዘመን (Middle Ages)” ማብቂያና የ“ህዳሴ(Renaissance)” መጀመሪያ እንደሆነ ይቆጥሩታል።
📌የሐር መንገድ መዘጋት⚡️
~~~~
አውሮፓውያን ወደ ምስራቅ (ህንድና ቻይና) የሚወስደው የየብስ መንገድ በኦቶማን ቁጥጥር ስር ስለዋለ፣አዳዲስ የባህር መንገዶችን መፈለግ ጀመሩ(ይህም የአሜሪካን መገኘት መንገድ ከፍቷል)።
📌የእስልምና የበላይነት⚡️
~~~~
ለዘመናት ሙስሊሞች ሲመኙት የነበረው ትንቢት በመፈፀሙ፣የኡስማንያ ግዛት በሙስሊሙ ዓለም ላይ ያለው ክብርና ተሰሚነት ከፍተኛ ሆነ።
📌ክፍል አራት፡የሥልጣኔ ግንባታ፣ ሌሎች ድሎች እና የሱልጣኑ ሕልፈት📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
የቁስጥንጥንያ ድል የሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ የጉዞ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልነበረም።በቀሪው የንግስና ዘመኑ ግዛቱን በማስፋፋትና የዓለም የሳይንስ ማዕከል በማድረግ አሳልፏል።
⚡️ግዛቱን የማስፋፋት ስራዎች⚡️
=========================
ከቁስጥንጥንያ ድል በኋላ ለቀጣዮቹ 28 ዓመታት ሱልጣኑ ሳይያርፍ ተዋግቷል።ዋና ዋናዎቹም፡-
📌የባልካን አገራት ድል⚡️
~~
ሰርቢያን፣ቦስኒያን እና አልባንያን በሙሉ በቁጥጥሩ ስር አደረገ።
📌የጥቁር ባህር ቁጥጥር⚡️
~~~~
የክራይሚያን ባሕረ ገብ መሬት በማሸነፍ ጥቁር ባህርን “የኦቶማን ባህር” አደረጋት።
📌ወደ ጣሊያን ያደረገው ጉዞ⚡️~~~~የሱልጣኑ ትልቁ ህልም #ሮምን መያዝ ነበር።በ1480 እ.ኤ.አ የጣሊያኗን #ኦትራንቶ(Otranto) ከተማ ተቆጣጠረ።ሆኖም ወደ ሮም ለመጓዝ ሲዘጋጅ ህይወቱ በማለፉ የሮም መያዝ ሳይሳካ ቀረ።
https://t.me/Seyfel_Islam
📚የሳይንስና የጥበብ ሰው🌱📚
=========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ተራ ተዋጊ ሱልጣን ብቻ አልነበረም።ይልቁንም ለእውቀትና ለጥበብ ትልቅ ቦታ የሚሰጥ የጥበብ ሰውም ነበር።
⚡️በኢስታንቡል ውስጥ በወቅቱ የነበሩትን ከፍተኛ የሳይንስና የሃይማኖት ትምህርቶችን የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችን መሰረተ።
📌የቤተ-መጻሕፍት ፍቅር⚡️
~~~
በግሪክ፣በላቲን እና በፋርስ ቋንቋዎች የተጻፉ በሺዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ሰብስቧል።የአውሮፓ ሰዓሊያንን (ለምሳሌ፦ ጄንቲሌ ቤሊኒ) ወደ ቤተ-መንግስቱ በመጋበዝ ስነ-ጥበብን ያበረታታ ነበር።
📌የሕግ ማሻሻያ⚡️
~~
“ቃኑን ናሜ(Kanunname)” የተባለውን የሕግ መድብል በማዘጋጀት የኡስማንያን አስተዳደራዊ መዋቅር ዘመናዊ አደረገ።
⚡️የሱልጣኑ ሕልፈት(1481እ.ኤ.አ)
========================
ግንቦት 3 ቀን 1481 እ.ኤ.አ ሱልጣኑ ለሌላ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ሰራዊቱን ይዞ ከወጣ በኋላ በመንገድ ላይ በድንገት ታመመ።
📌የህልፈቱ ምክንያቶች⚡️
~~~~
አንዳንዶች በህመም (Gout) ምክንያት እንደሞተ ሲናገሩ፣ሌሎች ደግሞ በሐኪሞቹ አማካኝነት #መርዝ ሳይሰጠው እንዳልቀረ በታሪክ ይገምታሉ።
ያም ሆነ ይህ በተወለደ ገና በ49 ዓመቱ እጅግ ታሪካዊ ጀብዱ ከፈፀመ እና የዓለምን ካርታ ከቀየረ በኋላ ወደማይቀረው አኼራ ሄደ።
إنالله وإنا إليه راجعون
📌የሱልጣኑ ሌጋሲ📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ሙሐመድ አል-ፋቲህ በታሪክ ውስጥ የሚታወሰው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፡-
📌የእምነት ምልክት⚡️
~
የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ትንቢት እውን በማድረጉ በሙስሊሙ ዓለም ትልቅ ክብር አለው።
📌የመቻቻል ምሳሌ⚡️
~
ድል አድራጊ ሆኖ ሳለ ለተሸናፊዎች ያሳየው ምህረትና የሃይማኖት ነጻነት ዛሬም ድረስ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል።
📌የኢስታንቡል መስራች⚡️
~~~~ኢስታንቡል የዓለም የንግድ፣የጥበብና የፖለቲካ ማዕከል እንድትሆን መሰረቱን የጣለው እርሱ ነው።
⚡️ማጠቃለያ⚡️
=====================
ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ የጥንካሬ፣ የዕውቀት እና የፍትህ ድምር ውጤት ነበር።
“መሬትን በሰይፍ፣ልብን ደግሞ በፍትህ የገዛ መሪ!”ይባላል።
⚡️የአሁኑ ሙስሊም ወጣት እና ታዳጊ ከሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ስብዕና እና የሕይወት ታሪክ ሊቀስሟቸው የሚገቡ እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ቁም ነገሮች⚡️
=========================
📌ትልቅ ራዕይና ዓላማ መያዝ (Having a Vision)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ገና በልጅነቱ ነበር “ቁስጥንጥንያን እከፍታለሁ” የሚል ትልቅ ራዕይ የሰነቀው።
🔐ወጣቶች በጊዜያዊ መዝናኛ ብቻ ሳይወሰኑ፣ለሕይወታቸው ትልቅና ዓለምን የሚቀይር ግብ ሊኖራቸው ይገባል።ራዕይ የሌለው ወጣት ጉዞው አቅጣጫ እንደሌለው መርከብ ነው!
📌ሁለገብ ዕውቀትን መገብየት (Multidisciplinary Learning)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ፋቲህ ሃይማኖታዊ ዕውቀትን ከዘመናዊ ሳይንስ (ሒሳብ፣ ምህንድስና፣ ጂኦግራፊ) እና ከቋንቋ ጋር አጣምሮ ተምሯል።
🔐የዛሬ ወጣቶችም በአንድ ዘርፍ ብቻ ሳይወሰኑ ዕውቀታቸውን ማስፋት አለባቸው።በተለይም ቋንቋዎችን መማር ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ያለውን ፋይዳ ከእርሱ መማር ይቻላል።
“አንድ ቋንቋ አንድ ሰው ነው” እንደሚባለው እርሱ 7 ቋንቋዎችን ማወቁ ለስኬቱ ቁልፍ ነበር!
📌 ለምሁራንና ለመምህራን ክብር መስጠት⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ለታላቁ መምህሩ ለ አቅ ሸምሰዲን የነበረው አክብሮት እጅግ ከፍተኛ ነበር።ምንም እንኳ ንጉስ ቢሆንም በመምህሩ ፊት ትሁት ነበር።
🔐የዛሬው ትውልድም ዕውቀትን ከሚያስጨብጡት መምህራንና ታላላቅ ምሁራን ጋር ያለው ግንኙነት በአክብሮት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።ስኬት የሚገኘው ከዕውቀት ጋር ስነ-ምግባር (አደብ) ሲታከልበት ነው!
📌ተስፋ አለመቁረጥና የፈጠራ ብልሃት (Innovation)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
መርከቦቹን በየብስ ላይ እንዲጓዙ ያደረገበት ስልት “የማይቻል ነገር የለም!” የሚል ትልቅ ትምህርት ይሰጣል።ግንቡን ለመስበር የነበረው መድፍ ሳይሳካ ሲቀር ተስፋ ቆርጦ አልተመለሰም፤ይልቁንም አዲስ የመድፍ ቴክኖሎጂ ፈጠረ!
🔐የዛሬ ወጣቶችም በሕይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች እንደ ማለቂያ ሳይሆን አዲስ የፈጠራ መንገድ መፈለጊያ አድርገው ሊጠቀሙባቸው ይገባል!
📌ስነ-ምግባርና መቻቻል (Character and Tolerance)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ከተማዋን ድል ካደረገ በኋላ በጠላቶቹ ላይ የበቀል እርምጃ አልወሰደም! ይልቁንም ለሃይማኖቶች ነጻነት ሰጠ፤ ለሰብዓዊ መብት ቅድሚያ ሰጠ።
🔐ኃይል ወይም ዕውቀት ሲገኝ በትዕቢት ከመወጠር ይልቅ ለሌሎች እውቅና መስጠት፣መቻቻልና ፍትሃዊ መሆን ለዘላቂ ስኬት ወሳኝ ነው!
📌በራስ መተማመንና የኃላፊነት ስሜት⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በ19 ዓመቱ ግዙፍ ግዛት የመምራት ኃላፊነት ሲረከብ “ገና ወጣት ነኝ” ብሎ አልሸሸም።ይልቁንም በራሱና በፈጣሪው በመተማመን ኃላፊነቱን ተወጣ!
🔐ወጣቶች ዕድሜያቸውን ለኃላፊነት እንደ ማገጃ መጠቀም የለባቸውም።በቂ ዝግጅትና በራስ መተማመን ካለ በማንኛውም ዕድሜ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል‼
🌱በአጭሩ የሙሐመድ አል-ፋቲህ ሕይወት ለዛሬው ወጣት ዕውቀትን ከእምነት፣ጀግንነትን ከትሕትና እንዲሁም ራዕይን ከሥራ ጋር እንዴት አቀናጅቶ መጓዝ እንደሚቻል የሚያሳይ ታላቅ ትምህርት ቤት ነው!📌
#ማሳሰቢያ!
መግቢያ ላይ እንደጠቀስኩላችሁ የሱልጣኑን የሒጅራ አቆጣጠር የልደት ቀን በተመለከተ ሁለት አስተያየቶች(ረጀብ 26ኛው እና ጀማዱልኣኺር 26ኛው) ያሉ ሲሆን የሱልጣን ሙሐመድ አልፋቲህ የተወለዱት በዛሬው ቀን ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ካሉ የታሪክ ምሁራን መካከል:
1ኛ: #አሕመድ_ቢን_ሉጥፉላህ ወይም በታሪክ “ሙነጂም ባሺ”
“ጃሚዕ አድ-ዱወል” በሚባል ታዋቂ መፅሐፋቸው
⚡️የኦቶማን መንግስት መዛግብት በብዙ የጥንት የኦቶማን ታሪክ ተመራማሪዎች በጠቀሱት መሠረት ጀማዱል ኣኺር 26 ነው!
⚡️ኢስማኢል ሐሚ ዳኒሽመንድ (Ismail Hami Danişmend) የተባሉት እጅግ ታዋቂ የጥንታዊ ቱርክ ታሪክ ፀሀፊ \"Izahli Osmanli Tarihi Kronolojisi\" (የኦቶማን ታሪክ የዘመን አቆጣጠር ማብራሪያ) በተባለው ዝነኛ መጽሐፉ፣የሱልጣኑን ልደት አስመልክቶ ያሉትን ልዩነቶች መርምሮ #ጀማዱል_ኣኺር_26፣835 ሂጅሪያ መሆኑን ፅፏል።
========================
✍𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃 𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
(Seyfel Islam AlHabeshi)
ጀማዱል ኣኺር 26/1447
December 17/2025
ታህሳስ 8/2018
እንደዚህ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማግኘት በቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ!👇
https://t.me/Seyfel_Islam
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ዛሬ በሒጅራ አቆጣጠር ጀማዱል ኣኺር 26ኛ ቀን ነው!
የዛሬ 612 አመታት ወደ ኋላ ስንመለስ በ835 ሒጅራ ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ገና በወጣትነቱ #ቆስጠንጥያን በመክፈት የረሱልን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የድል ትንብይት እውን ያደረገው ጀግና ሱልጣን #ሙሐመድ_አል_ፋቲህ የተወለደበት ቀን ነው።
ምንም እንኳን ሱልጣኑ የተወለዱት ረጀብ 26ኛው ቀን ነው የሚሉ መረጃዎች በመኖራቸው በታሪክ ምሁራን መካከል ሁለት አመለካከቶች ቢኖሩም ጀማዱል ኣኺር 26ኛ ነው ባሉት ምሁራን መሰረት ታሪኩን ከውልደት እስከ ህልፈት እና ከታሪኩ የምንማራቸውን ቁም ነገሮች ለማንበብ በሚመች አቀራረብ አዘጋጅቸላችኋለሁ።
ሱልጣኑ የተወለዱት ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ነው ያሉ ምሁራንን ማስረጃ መጨረሻ ላይ ታገኛላችሁ!
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ታላቁ የኡስማንያ መሪ ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ (መሐመድ ዳግማዊ) በታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው መሪዎች አንዱ ነው።የቁስጥንጥንያ(ኢስታንቡል) ድል አድራጊ በመሆኑም "አል-ፋቲህ" (ድል አድራጊው) የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል።
በዛሬው“ዕለቱን በታሪክ”አምዳችን የዚህን ጀግና ታሪክ በወፍ በረር ከውልደት እስክ
ህልፈቱ ላስዳስሳችሁ እሞክራለሁ መልካም ንባብ።
📌ክፍል1:የሙሐመዱል ፋቲህ ውልደት፣እድገት፣እንድሁም ስለ ወላጆቹ እና በግዜው ስለነበረው ሁኔታ በአጭሩ📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ መጋቢት 30 ቀን 1432 እ.ኤ.አ ወይንም በጀማዱልኣኺር 26/835ሒጅራ(በብዙ መረጃዎች ደግሞ ረጀብ 26፣835 ሂጅራ የሚል ተጠቅሶ እናገኛለን)በወቅቱ የኡስማንያ (ኦቶማን) ግዛት ዋና ከተማ በነበረችው #ኤድርኔ (Edirne) ተወለደ።
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ከመወለዱ በፊት የነበረው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ በትቂቱ ይሄን ይመስል ነበር:-
📍1ኛ:የቢዛንታይን ግዛት መዳከም⚡️
~~~~
በአንድ ወቅት ኃያል የነበረው የቢዛንታይን (የምስራቅ ሮም) ግዛት ተዳክሞ በቁስጥንጥንያ ቅጥር ግቢ ብቻ ተወስኖ ነበር።ሆኖም ከተማዋ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ምክንያት አሁንም ለንግድና ለጦርነት ቁልፍ ነበረች።
📍2ኛ:የኡስማንያ ግዛት መረጋጋት⚡️
~~~~
ግዛቱ ከአንካራ ጦርነት ሽንፈት (ከቲሙር ላንግ ጋር ከነበረው ግጭት) በኋላ መልሶ እያገገመና እየተጠናከረ የነበረበት ወቅት ነበር።
📌የነብዩ ሙሐመድ-ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም-ትንቢት📌
=======================
ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)“ቁስጥንጥንያ በእርግጥ ትከፈታለች፤እሷን የሚከፍተው መሪ ምንኛ ምርጥ መሪ ነው!ያ ሰራዊትም ምንኛ ምርጥ ሰራዊት ነው!”ሲሉ የተናገሩትን ትንቢት ለመፈጸም ለ800 ዓመታት ሲመኙ ነበር።
📌የወላጆቹ ሁኔታ📌
======================
📍አባቱ -ሱልጣን ሙራድ ዳግማዊ📍
~~~~
አባቱ ሱልጣን ሙራድ ጠንካራ መሪና ፍትሃዊ ሰው ነበሩ።ግዛቱን በማስፋፋትና የውስጥ አመጾችን በማርገብ ይታወቃሉ። ሙራድ ዳግማዊ ልጃቸው ሙሐመድ ለታላቅ ዓላማ እንዲበቃ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
📍እናቱ - ሁማ ሃቱን📍
~~~
ስለ እናቱ ማንነት የታሪክ ምሁራን የተለያዩ ሃሳቦችን ይሰነዝራሉ።ነገር ግን እርሷ በልጇ አስተዳደግና ስብዕና ላይ ትልቅ ሚና የነበራት፣ለልጇ ሃይማኖታዊና ስነ-ምግባራዊ እሴቶችን ያወረሰች እናት ነበረች።
📌አስተዳደግና ትምህርት📌
========================
የሙሐመድ አል-ፋቲህ አስተዳደግ “ለታላቅነት የታጨ”ሰው አስተዳደግ ነበር ማለት ይቻላል።
በልጅነቱ እልከኛና ትንሽ አስቸጋሪ እንደነበር ይነገራል።ነገር ግን አባቱ ሱልጣን ሙራድ በወቅቱ የነበሩ ታላላቅ ምሁራንን በመመደብ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ አድርገዋል።ለምሳሌ:
📍አቅ ሸምሰዲን⚡️
~~~~
ሙሐመድ ላይ ትልቁን ተጽዕኖ ያሳረፉት መምህራቸው ናቸው።እርሳቸው ለሙሐመድ “ቁስጥንጥንያን የምትከፍተው አንተ ነህ” የሚለውን መንፈስ በውስጡ የዘሩትና በመንፈሳዊ ጥንካሬ ያነጹት ሰው ናቸው።
📍ሁለገብ እውቀት⚡️
~
ሙሐመድ ሃይማኖታዊ እውቀትን (ቁርኣን፣ ሐዲስ፣ ፊቅህ) ብቻ ሳይሆን ሳይንስን፣ ፍልስፍናን፣ ጂኦግራፊንና ስነ-መንግስትን ተምሯል።
📍የቋንቋ ችሎታ⚡️
~~~
በቋንቋ በኩል እጅግ የተዋጣለት ነበር።ቱርክኛ፣አረብኛ፣ፋርስኛ፣ግሪክኛ፣ላቲን፣ሰርቢያኛ እና ዕብራይስጥ ቋንቋዎችን በደንብ ይናገርና ይረዳ ነበር።ይህም ለወደፊቱ ዲፕሎማሲያዊ ስራው ትልቅ በር ከፍቶለታል።
📍የተግባር ልምድ⚡️
~~~
ገና በ12 ዓመቱ አባቱ ለተወሰነ ጊዜ ስልጣን በውክልና ሰጥተውት ነበር።ይህ የልጅነት የንግስና ልምድ የአስተዳደርን ከባድነትና የፖለቲካን ሴራ ቀድሞ እንዲረዳ አስችሎታል።
📌ክፍል ሁለት፡ወደ ስልጣን መምጣትና ለታላቁ ድል የተደረጉ ዝግጅቶች📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
የሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ወደ ስልጣን መምጣትና ለቁስጥንጥንያ ከበባ ያደረገው ዝግጅት፣ በታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሆኑ ስልታዊ እቅዶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
⚡️ወደ ስልጣን መምጣት (ሁለተኛው ንግስና)⚡️
========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በ12 ዓመቱ ወደ መንበሩ ቢወጣም፣ በልጅነቱና በውጭ ወራሪዎች ስጋት ምክንያት አባቱ ሱልጣን ሙራድ ዳግማዊ ወደ ስልጣን ተመልሰው ነበር።በ1451 እ.ኤ.አ አባቱ ሲያርፉ፣በ19 ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሱልጣን ሆነ።
⚡️የውስጥ ተቃውሞ⚡️
~~~~ብዙዎች “ገና ወጣት ነው፣ግዛቱን መምራት አይችልም!” ብለው ንቀውት ነበር።
⚡️የቢዛንታይን ስህተት⚡️
~~~~
የቢዛንታይን ንጉስ ቆስጠንጢኖስ 11ኛ፣ ሙሐመድን እንደ ልምድ የሌለው ወጣት በመቁጠር የግዛቱን ወሰን ለማስገፋትና የተለያዩ ጥያቄዎችን ለማቅረብ ሞከረ። ይህ ስህተታቸው ለሙሐመድ ወሳኝ እርምጃ እንዲወስድ ምክንያት ሆነው።
⚡️ስልታዊ ዝግጅቶች(Strategic Preparation)⚡️
=========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ስልጣን እንደያዘ ዋነኛ ትኩረቱ "የማይደፈረውን" የቁስጥንጥንያ ግንብ ሰብሮ መግባት ነበር።ለዚህም የሚከተሉትን ተግባራት አከናወነ፡-
📌ነኛ:ሩሜሊ ሂሳሪ(Rumeli Hisarı) ግንብ መገንባት⚡️
========+===============
ቁስጥንጥንያ ከጥቁር ባህር የሚመጣላትን እርዳታ ለማቋረጥ፣ በቦስፈረስ ባህረ ሰላጤ (Bosphorus Strait) አውሮፓዊው ክፍል ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ምሽግ በ4 ወራት ውስጥ ብቻ አስገነባ።ይህ ምሽግ ከባህር የሚመጡ መርከቦችን ለመቆጣጠር አስቻለው።
📌2ኛ:ግዙፉ መድፍ(The Great Cannon/Urbans's Gun)⚡️
=======================
የቁስጥንጥንያ ግንቦች እጅግ ወፍራም በመሆናቸው በወቅቱ በነበሩ መሳሪያዎች አይሰበሩም ነበር። #ሙሐመድ_ኡርባን የተባለ #ሃንጋሪያዊ የመድፍ ባለሙያን ቀጥሮ፣በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ መድፍ አሰራ።ይህ መድፍ ግማሽ ቶን የሚመዝን ድንጋይ ከአንድ ማይል በላይ መወርወር የሚችል ነበር።
📌3ኛ:የባህር ኃይል ግንባታ⚡️
========================
ከተማዋ በሶስት አቅጣጫ በውሃ የተከበበች በመሆኗ፣ሱልጣኑ ከ400 በላይ ትናንሽና ትላልቅ መርከቦችን በማዘጋጀት የባህር ኃይሉን አጠናከረ።
⚡️ድንቅ ስልታዊ ብልሃት፡መርከቦችን በየብስ ላይ ማጓጓዝ⚡️
=======================
ይህ የሙሐመድ አል-ፋቲህ ድንቅ ወታደራዊ ጥበብ የታየበት ክስተት ነው።
ሆኖም ቢዛንታይኖች የ"ጎልደን ሆርን" (Golden Horn) የባህር ወሽመጥን በግዙፍ ሰንሰለት ዘግተውት ነበር። የኦቶማን መርከቦች ወደዚያ መግባት ሳይችሉ ቀሩ።
🔐ነገር ግን ሙሐመድ አልፋቲሕ ለዚህ መፍትሄ መርከቦቹን በባህር ፋንታ በየብስ (በመሬት) ላይ እንዲጓጓዙ አዘዘ።በአንድ ሌሊት ውስጥ፣በቅባት በተቀቡ እንጨቶች ላይ በማንሸራተት 70 የሚሆኑ መርከቦችን ከኮረብታ ጀርባ በማሳለፍ ወደ ወሽመጡ አስገባቸው‼አሏሁ አክበር!ምን አይነት ብልሃት ነው?!
ጠዋት ላይ የቢዛንታይን ሰራዊት መርከቦቹን ከጀርባቸው ሲያይ ድንጋጤ ውስጥ ወደቀ!
⚡️መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት⚡️
=========================
ሙሐመድ ሰራዊቱን ለማነቃቃት የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ትንቢት ዘወትር ያስታውሳቸው ነበር።መምህሩ አቅ ሸምሰዲን በየቀኑ በድንኳኖች ውስጥ እየተዘዋወሩ ሰራዊቱን በዱዓ እና በንግግር ያጠናክሩ ነበር። ሱልጣኑ ራሱ ሳይንቲስትና መሐንዲስ ስለነበር፣ የጦርነቱን ካርታና ምህንድስና በራሱ እጅ ይነድፍ ነበር።
⚡️የመጨረሻው ጥቃት መጀመር⚡️
========================
ሚያዝያ 6፣1453 እ.ኤ.አ ከበባው በይፋ ተጀመረ።ለ53 ቀናት የዘለቀው ይሄ ከበባ፣ ዓለምን ለዘላለም የሚቀይር የታሪክ ምዕራፍ መጀመሪያ ነበር!
📌ክፍል ሦስት፡ታላቁ ድል፣ የቁስጥንጥንያ መውደቅ እና የድል አድራጊው ሰብዓዊነት📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በዚህ ክፍል የ53 ቀናት ከበባ እንዴት ወደ ፍጻሜ እንደመጣ እና ዓለምን የለወጠው ያ ታሪካዊ ቀን እንዴት እንደነበረ በዝርዝር እናያለንደ
⚡️የመጨረሻው ጥቃት (ግንቦት 29፣ 1453)⚡️
=========================
ከ53 ቀናት ተከታታይ ከበባ እና ድካም በኋላ፣ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ሰራዊቱን ለታላቁና ለመጨረሻው ጥቃት አዘጋጄ!
📌መንፈሳዊ ዝግጅት:
~~~
ግንቦት 28 ምሽት ላይ፣ሱልጣኑ መላው ሰራዊት እንዲጾም፣እንዲጸልይና በየድንኳኑ መብራት እንዲያበራ አዘዘ።ሌሊቱን ሙሉ የ"ተክቢራ" ድምፅ በቁስጥንጥንያ ቅጥር ዙሪያ ያስተጋባ ነበር።አሏሁ አክበር!
📌የጥቃቱ ስልት፦
~~~
ጥቃቱ ጎህ ሳይቀድ በሦስት አቅጣጫ ተጀመረ።መጀመሪያ “አዘቦች”(መደበኛ ያልሆነ ሰራዊት)፣ቀጥሎ የአናቶሊያ ሰራዊት፣በመጨረሻም የሱልጣኑ ምርጥ የጦር ክፍል የሆኑት “ጃኒሰሪዎች” እንዲገቡ ተደረገ።
📌ግንቡ መጣስ⚡️
=======================
በኡርባን ግዙፍ መድፍ የተመታው የቅዱስ ሮማነስ ደጃፍ (St. Romanus Gate) በመጨረሻ #ፈረሰ።አሏሁ አክበር!
#ሀሳን_አል_ሉባትሊ የተባለ ወጣት ወታደር ከ30 ጓደኞቹ ጋር በመሆን፣ ቀስቶችና ድንጋዮች እየዘነቡበት የግንቡ አናት ላይ በመውጣት የመጀመሪያውን የኡስማንያ ሰንደቅ ዓላማ #ሰቀለ‼
ይህ ክስተት ለኦቶማን ሰራዊት ትልቅ ወታደራዊ ወኔ ሰጠ!
⚡️ወደ ከተማዋ መግባት⚡️
=========================
የቢዛንታይን ንጉስ ቆስጠንጢኖስ 11ኛ እስከ መጨረሻው ተዋግቶ በጦርነቱ ሜዳ ላይ #ወደቀ።በዚያው እለት ከሰዓት በኋላ፣ ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ በነጭ ፈረሱ ላይ ሆኖ በታላቅ ግርማ ወደ ከተማዋ #ገባ!!አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ!
⚡️የመጀመሪያው ስግደት⚡️
=========================ሱልጣኑ በቀጥታ ወደ #አያ_ሶፊያ(Hagia Sophia) አመራ።እዚያም ከፈረሱ ወርዶ ሱጁድ አደረገ!
አያ ሶፊያም ወደ መስጂድነት ተቀየረች! የመጀመሪያው የጁምዓ ሶላትም እዚያው ተሰገደ!!!
📌አዲስ ስም⚡️
~~~
ከተማዋ #ኢስላምቡል” (የእስልምና ከተማ)የሚል ስም ተሰጣት፣ይህም በኋላ ወደ “ኢስታንቡል” ተቀየረ።
⚡️የድል አድራጊው ሰብዓዊነትና ፍትህ⚡️
========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ከተማዋን ሲቆጣጠር ያሳየው ስነ-ምግባር በወቅቱ ለነበረው ዓለም አስገራሚ ነበር፦
📌የምህረት አዋጅ⚡️
~~~~
በአያ ሶፊያ ውስጥ ተሸሽገው በድንጋጤ ይንቀጠቀጡ ለነበሩ #ክርስቲያኖች “ወደ ቤታችሁ በሰላም ሂዱ፣ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ቅጣት የለም!ነፃነታችሁና ህይወታችሁ የተጠበቀ ነው!” የሚል የደህንነት ዋስትና ሰጣቸው‼
እስልምና እንድህ ነው!
📌የሃይማኖት ነጻነት⚡️
~~
የግሪክ #ኦርቶዶክስ_ቤተክርስቲያን_መሪ (Patriarch) እንዲመረጥ ፈቀደ! #የአይሁድና የሌሎች እምነት ተከታዮችም የራሳቸው ፍርድ ቤትና የሃይማኖት ነጻነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ “የሚሌት ስርዓት (Millet System)” ዘረጋ!
📌ከተማዋን መልሶ መገንባት⚡️
~~
ጦርነቱ ያፈራረሳቸውን ህንጻዎች በፍጥነት እንዲጠገኑ አዘዘ።ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ነጋዴዎችንና ሳይንቲስቶችን ወደ ኢስታንቡል ጋበዘ።
⚡️የድሉ ውጤቶች(Global Impact):
የመካከለኛው ዘመን ማብቂያ⚡️
========================= የታሪክ ምሁራን የቁስጥንጥንያ መውደቅን የ"መካከለኛው ዘመን (Middle Ages)” ማብቂያና የ“ህዳሴ(Renaissance)” መጀመሪያ እንደሆነ ይቆጥሩታል።
📌የሐር መንገድ መዘጋት⚡️
~~~~
አውሮፓውያን ወደ ምስራቅ (ህንድና ቻይና) የሚወስደው የየብስ መንገድ በኦቶማን ቁጥጥር ስር ስለዋለ፣አዳዲስ የባህር መንገዶችን መፈለግ ጀመሩ(ይህም የአሜሪካን መገኘት መንገድ ከፍቷል)።
📌የእስልምና የበላይነት⚡️
~~~~
ለዘመናት ሙስሊሞች ሲመኙት የነበረው ትንቢት በመፈፀሙ፣የኡስማንያ ግዛት በሙስሊሙ ዓለም ላይ ያለው ክብርና ተሰሚነት ከፍተኛ ሆነ።
📌ክፍል አራት፡የሥልጣኔ ግንባታ፣ ሌሎች ድሎች እና የሱልጣኑ ሕልፈት📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
የቁስጥንጥንያ ድል የሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ የጉዞ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልነበረም።በቀሪው የንግስና ዘመኑ ግዛቱን በማስፋፋትና የዓለም የሳይንስ ማዕከል በማድረግ አሳልፏል።
⚡️ግዛቱን የማስፋፋት ስራዎች⚡️
=========================
ከቁስጥንጥንያ ድል በኋላ ለቀጣዮቹ 28 ዓመታት ሱልጣኑ ሳይያርፍ ተዋግቷል።ዋና ዋናዎቹም፡-
📌የባልካን አገራት ድል⚡️
~~
ሰርቢያን፣ቦስኒያን እና አልባንያን በሙሉ በቁጥጥሩ ስር አደረገ።
📌የጥቁር ባህር ቁጥጥር⚡️
~~~~
የክራይሚያን ባሕረ ገብ መሬት በማሸነፍ ጥቁር ባህርን “የኦቶማን ባህር” አደረጋት።
📌ወደ ጣሊያን ያደረገው ጉዞ⚡️~~~~የሱልጣኑ ትልቁ ህልም #ሮምን መያዝ ነበር።በ1480 እ.ኤ.አ የጣሊያኗን #ኦትራንቶ(Otranto) ከተማ ተቆጣጠረ።ሆኖም ወደ ሮም ለመጓዝ ሲዘጋጅ ህይወቱ በማለፉ የሮም መያዝ ሳይሳካ ቀረ።
📚የሳይንስና የጥበብ ሰው🌱📚
=========================
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ተራ ተዋጊ ሱልጣን ብቻ አልነበረም።ይልቁንም ለእውቀትና ለጥበብ ትልቅ ቦታ የሚሰጥ የጥበብ ሰውም ነበር።
⚡️በኢስታንቡል ውስጥ በወቅቱ የነበሩትን ከፍተኛ የሳይንስና የሃይማኖት ትምህርቶችን የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችን መሰረተ።
📌የቤተ-መጻሕፍት ፍቅር⚡️
~~~
በግሪክ፣በላቲን እና በፋርስ ቋንቋዎች የተጻፉ በሺዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ሰብስቧል።የአውሮፓ ሰዓሊያንን (ለምሳሌ፦ ጄንቲሌ ቤሊኒ) ወደ ቤተ-መንግስቱ በመጋበዝ ስነ-ጥበብን ያበረታታ ነበር።
📌የሕግ ማሻሻያ⚡️
~~
“ቃኑን ናሜ(Kanunname)” የተባለውን የሕግ መድብል በማዘጋጀት የኡስማንያን አስተዳደራዊ መዋቅር ዘመናዊ አደረገ።
⚡️የሱልጣኑ ሕልፈት(1481እ.ኤ.አ)
========================
ግንቦት 3 ቀን 1481 እ.ኤ.አ ሱልጣኑ ለሌላ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ሰራዊቱን ይዞ ከወጣ በኋላ በመንገድ ላይ በድንገት ታመመ።
📌የህልፈቱ ምክንያቶች⚡️
~~~~
አንዳንዶች በህመም (Gout) ምክንያት እንደሞተ ሲናገሩ፣ሌሎች ደግሞ በሐኪሞቹ አማካኝነት #መርዝ ሳይሰጠው እንዳልቀረ በታሪክ ይገምታሉ።
ያም ሆነ ይህ በተወለደ ገና በ49 ዓመቱ እጅግ ታሪካዊ ጀብዱ ከፈፀመ እና የዓለምን ካርታ ከቀየረ በኋላ ወደማይቀረው አኼራ ሄደ።
إنالله وإنا إليه راجعون
📌የሱልጣኑ ሌጋሲ📌
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ሙሐመድ አል-ፋቲህ በታሪክ ውስጥ የሚታወሰው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፡-
📌የእምነት ምልክት⚡️
~
የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ትንቢት እውን በማድረጉ በሙስሊሙ ዓለም ትልቅ ክብር አለው።
📌የመቻቻል ምሳሌ⚡️
~
ድል አድራጊ ሆኖ ሳለ ለተሸናፊዎች ያሳየው ምህረትና የሃይማኖት ነጻነት ዛሬም ድረስ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል።
📌የኢስታንቡል መስራች⚡️
~~~~ኢስታንቡል የዓለም የንግድ፣የጥበብና የፖለቲካ ማዕከል እንድትሆን መሰረቱን የጣለው እርሱ ነው።
⚡️ማጠቃለያ⚡️
=====================
ሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ የጥንካሬ፣ የዕውቀት እና የፍትህ ድምር ውጤት ነበር።
“መሬትን በሰይፍ፣ልብን ደግሞ በፍትህ የገዛ መሪ!”ይባላል።
⚡️የአሁኑ ሙስሊም ወጣት እና ታዳጊ ከሱልጣን ሙሐመድ አል-ፋቲህ ስብዕና እና የሕይወት ታሪክ ሊቀስሟቸው የሚገቡ እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ቁም ነገሮች⚡️
=========================
📌ትልቅ ራዕይና ዓላማ መያዝ (Having a Vision)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ገና በልጅነቱ ነበር “ቁስጥንጥንያን እከፍታለሁ” የሚል ትልቅ ራዕይ የሰነቀው።
🔐ወጣቶች በጊዜያዊ መዝናኛ ብቻ ሳይወሰኑ፣ለሕይወታቸው ትልቅና ዓለምን የሚቀይር ግብ ሊኖራቸው ይገባል።ራዕይ የሌለው ወጣት ጉዞው አቅጣጫ እንደሌለው መርከብ ነው!
📌ሁለገብ ዕውቀትን መገብየት (Multidisciplinary Learning)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ፋቲህ ሃይማኖታዊ ዕውቀትን ከዘመናዊ ሳይንስ (ሒሳብ፣ ምህንድስና፣ ጂኦግራፊ) እና ከቋንቋ ጋር አጣምሮ ተምሯል።
🔐የዛሬ ወጣቶችም በአንድ ዘርፍ ብቻ ሳይወሰኑ ዕውቀታቸውን ማስፋት አለባቸው።በተለይም ቋንቋዎችን መማር ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ያለውን ፋይዳ ከእርሱ መማር ይቻላል።
“አንድ ቋንቋ አንድ ሰው ነው” እንደሚባለው እርሱ 7 ቋንቋዎችን ማወቁ ለስኬቱ ቁልፍ ነበር!
📌 ለምሁራንና ለመምህራን ክብር መስጠት⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሙሐመድ አል-ፋቲህ ለታላቁ መምህሩ ለ አቅ ሸምሰዲን የነበረው አክብሮት እጅግ ከፍተኛ ነበር።ምንም እንኳ ንጉስ ቢሆንም በመምህሩ ፊት ትሁት ነበር።
🔐የዛሬው ትውልድም ዕውቀትን ከሚያስጨብጡት መምህራንና ታላላቅ ምሁራን ጋር ያለው ግንኙነት በአክብሮት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።ስኬት የሚገኘው ከዕውቀት ጋር ስነ-ምግባር (አደብ) ሲታከልበት ነው!
📌ተስፋ አለመቁረጥና የፈጠራ ብልሃት (Innovation)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
መርከቦቹን በየብስ ላይ እንዲጓዙ ያደረገበት ስልት “የማይቻል ነገር የለም!” የሚል ትልቅ ትምህርት ይሰጣል።ግንቡን ለመስበር የነበረው መድፍ ሳይሳካ ሲቀር ተስፋ ቆርጦ አልተመለሰም፤ይልቁንም አዲስ የመድፍ ቴክኖሎጂ ፈጠረ!
🔐የዛሬ ወጣቶችም በሕይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች እንደ ማለቂያ ሳይሆን አዲስ የፈጠራ መንገድ መፈለጊያ አድርገው ሊጠቀሙባቸው ይገባል!
📌ስነ-ምግባርና መቻቻል (Character and Tolerance)⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ከተማዋን ድል ካደረገ በኋላ በጠላቶቹ ላይ የበቀል እርምጃ አልወሰደም! ይልቁንም ለሃይማኖቶች ነጻነት ሰጠ፤ ለሰብዓዊ መብት ቅድሚያ ሰጠ።
🔐ኃይል ወይም ዕውቀት ሲገኝ በትዕቢት ከመወጠር ይልቅ ለሌሎች እውቅና መስጠት፣መቻቻልና ፍትሃዊ መሆን ለዘላቂ ስኬት ወሳኝ ነው!
📌በራስ መተማመንና የኃላፊነት ስሜት⚡️
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በ19 ዓመቱ ግዙፍ ግዛት የመምራት ኃላፊነት ሲረከብ “ገና ወጣት ነኝ” ብሎ አልሸሸም።ይልቁንም በራሱና በፈጣሪው በመተማመን ኃላፊነቱን ተወጣ!
🔐ወጣቶች ዕድሜያቸውን ለኃላፊነት እንደ ማገጃ መጠቀም የለባቸውም።በቂ ዝግጅትና በራስ መተማመን ካለ በማንኛውም ዕድሜ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል‼
🌱በአጭሩ የሙሐመድ አል-ፋቲህ ሕይወት ለዛሬው ወጣት ዕውቀትን ከእምነት፣ጀግንነትን ከትሕትና እንዲሁም ራዕይን ከሥራ ጋር እንዴት አቀናጅቶ መጓዝ እንደሚቻል የሚያሳይ ታላቅ ትምህርት ቤት ነው!📌
መግቢያ ላይ እንደጠቀስኩላችሁ የሱልጣኑን የሒጅራ አቆጣጠር የልደት ቀን በተመለከተ ሁለት አስተያየቶች(ረጀብ 26ኛው እና ጀማዱልኣኺር 26ኛው) ያሉ ሲሆን የሱልጣን ሙሐመድ አልፋቲህ የተወለዱት በዛሬው ቀን ጀማዱል ኣኺር 26ኛው ቀን ካሉ የታሪክ ምሁራን መካከል:
1ኛ: #አሕመድ_ቢን_ሉጥፉላህ ወይም በታሪክ “ሙነጂም ባሺ”
“ጃሚዕ አድ-ዱወል” በሚባል ታዋቂ መፅሐፋቸው
⚡️የኦቶማን መንግስት መዛግብት በብዙ የጥንት የኦቶማን ታሪክ ተመራማሪዎች በጠቀሱት መሠረት ጀማዱል ኣኺር 26 ነው!
⚡️ኢስማኢል ሐሚ ዳኒሽመንድ (Ismail Hami Danişmend) የተባሉት እጅግ ታዋቂ የጥንታዊ ቱርክ ታሪክ ፀሀፊ "Izahli Osmanli Tarihi Kronolojisi" (የኦቶማን ታሪክ የዘመን አቆጣጠር ማብራሪያ) በተባለው ዝነኛ መጽሐፉ፣የሱልጣኑን ልደት አስመልክቶ ያሉትን ልዩነቶች መርምሮ #ጀማዱል_ኣኺር_26፣835 ሂጅሪያ መሆኑን ፅፏል።
========================
✍𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃 𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
(Seyfel Islam AlHabeshi)
ጀማዱል ኣኺር 26/1447
December 17/2025
ታህሳስ 8/2018
እንደዚህ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማግኘት በቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ!👇
Comment
Share
Send as a message
Share on my page
Share in the group