Translation is not possible.
✨ የየመን እና የሻም (ሶርያ) ምድር በሐዲሦች ብርሃን ✨
فعن أبي هريرة عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: أتاكم أهل اليمن هم أرق أفئدة وألين قلوبا الإيمان يمان والحكمة يمانية والفخر والخيلاء في أصحاب الإبل والسكينة والوقار في أهل الغنم. متفق عليه.
አቢ ሁረይረህ ረዲየሏሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
"የየመን ሰዎች ወደ እናንተ መጥተዋል። እነርሱ ልባቸው በጣም ለስላሳ፣ ኅሊናቸውም እጅግ የረቀቀ ነው። እምነት የየመን ነው፣ ጥበብም የየመን ናት። ትዕቢትና ኩራት የግመል ባለቤቶች (የበረሃ ነዋሪዎች) ባሕሪ ሲሆን፣ ጸጥታና መከበር ግን የበግ ባለቤቶች (የየመን ሰዎች) ባሕሪ ነው።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ይህ ሐዲስ የየመን ሰዎችን ልስላሴ፣ የጥበብ ባለቤትነታቸውን እና የእምነት ጥንካሬያቸውን ያመላክታል።
وعن زيد بن ثابت قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: طوبى للشام قلنا لأي ذلك يا رسول الله؟ قال: لأن ملائكة الرحمن باسطة أجنحتها عليها. رواه أحمد والترمذي.
ዘይድ ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-
"ለሻም ደስታ ይገባታል (ጡባ ሊሻም)!"
እኛም "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" ብለን ስንጠይቅ፦
እርሳቸውም፦ "ምክንያቱም የአር-ረሕማን (የአዛኙ) መላእክት ክንፎቻቸውን በላዩ ላይ ዘርግተዋልና!" (አሕመድ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል።)
 
وعن ابن حوالة قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: سيصير الأمر إلى أن تكونوا جنودا مجندة جند بالشام وجند باليمن وجند بالعراق. فقال ابن حوالة خر لي يا رسول الله، إن أدركت ذلك، فقال: عليك بالشام فإنها خيرة الله من أرضه يجتبي إليها خيرته من عباده فأما إن أبيتم فعليكم بيمنكم واسقوا من غدركم فإن الله توكل لي بالشام وأهله. رواه أحمد وأبو داود والترمذي وصححه الألباني.
 
ኢብኑ ኸውላ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐወ) እንድህ አሉ:-
“ነገሩ ሁሉ ወደተሰባሰበ ጦርነት ይለወጣል።አንድ ጦር በሻም፣አንድ በየመን እና አንድም በዒራቅ ይሆናል!”
ኢብኑ ኸውላም“የአሏህ መልእክተኛ ሆይ!ያንን ዘመን ካገኘሁ የት እንድኖር ትመርጥልኛለህ?”ብሎ ጠየቀ።
እርሳቸውም መለሱ፦"ሻምን ያዝ! እርሷ የአሏህ ምርጥ ምድር ናትና!ከባሮቹ መካከል ምርጦቹን ወደ እርሷ ይሰበስባል።እምቢ ካላችሁ ደግሞ የመናችሁን ያዙና ከውሃ መቋጠሪያዎቻችሁ ጠጡ።አሏህ የሻምንና የሕዝቦቿን ነገር ተረክቦኛል።" (አሕመድ፣ አቡ ዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
وعن ابن عمر أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: اللهم بارك لنا في شأمنا اللهم بارك لنا في يمننا، قالوا: وفي نجدنا، قال: اللهم بارك لنا في شأمنا وبارك لنا في يمننا، قالوا: وفي نجدنا، قال: هناك الزلازل والفتن وبها أو قال منها يخرج قرن الشيطان. رواه الترمذي وقال: هذا حديث حسن صحيح غريب من هذا الوجه. وقال الشيخ الألباني: صحيح.
 
ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ሆይ! በሻማችን ላይ በረከትን አውርድልን። አላህ ሆይ! በየመናችን ላይ በረከትን አውርድልን።" (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለሻምና ለየመን በረከትን ሲጠይቁ ባልደረቦቻቸው “በነጅዳችንስ (የመካና የመዲና መካከለኛ የምስራቅ ክፍል)?” ብለው በጠየቋቸው ጊዜ
"አላህ ሆይ! በሻማችን ላይ በረከትን አውርድልን፣ በየመናችንም ላይ በረከትን አውርድልን።" ሲሉ ደግመው መለሱ።
በድጋሚ ሲጠየቁም እንዲህ አሉ፦ "እዚያ የመሬት መንቀጥቀጦችና ፈተናዎች አሉ፣ የሰይጣን ቀንዶችም የሚወጡት ከዚያ ነው።" (ቲርሚዚይ ዘግበውታል
وعن أبي الدرداء قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: بينا أنا نائم إذ رأيت عمود الكتاب احتمل من تحت رأسي، فظننت أنه مذهوب به فأتبعته بصري، فعمد به إلى الشام، ألا وإن الإيمان حين تقع الفتن بالشام. رواه أحمد والطبراني وقال الهيثمي ورجال أحمد رجال الصحيح.
አቡ ደርዳእ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-
"ተኝቼ ሳለሁ የኪታቡ(የእስልምና) ምሰሶ ከራሴ ስር ሲነሳ አየሁ። ተወስዶብኛል ብዬ አሰብኩና በዓይኖቼ ተከተልኩት።ሲሄድም ወደ ሻም አመራ። ንቁ!ፈተናዎች በሚከሰቱ ጊዜ እምነት የሚኖረው በሻም ውስጥ ነው!”(አሕመድና ጠበራኒ ዘግበውታል)
 
وعن عبد الله بن عمر قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: تخرج نار من نحو حضرموت -أو من حضرموت- تسوق الناس. قلنا: يا رسول الله فما تأمرنا، قال: عليكم بالشام. رواه أبو يعلى وقال الهيثمي رجاله رجال الصحيح.
 
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)የሚከተለውን መናገራቸውን አስተላልፈዋል:-
“ከሰዎች ሁሉ ወደ ሐድረመውት (የየመን ክፍል) አቅጣጫ - ወይንም ከሐድረመውት - ሰዎችን የምትነዳ እሳት ትወጣለች!”
እኛም“የአሏህ መልእክተኛ ሆይ!(በዚያን ጊዜ)ምን እንድናደርግ ታዘናለህ?”ብለን ጠየቅን።
እርሳቸውም፦“ሻምን አጥብቃችሁ ያዙ!” አሉን።(አቡየዕላ ዘግበውታል)
 
وعن أبي هريرة عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: لا تزال عصابة من أمتي يقاتلون على أبواب دمشق وما حوله، وعلى أبواب بيت المقدس وما حوله، لا يضرهم خذلان من خذلهم، ظاهرين على الحق إلى أن تقوم الساعة. رواه أبو يعلى وقال الهيثمي رجاله ثقات.
 
አቡ ሁረይራህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)እንድህ ብለዋል:-
"ከኡመቴ(ከሕዝቦቼ)የሆነ ቡድን በደማስቆ ደጆችና በዙሪያዋ፣ እንዲሁም በይተል መቅዲስ ደጆችና በዙሪያዋ ላይ ሆነው ከመዋጋት አይወገዱም።የተዋቸው ሰው መተው ምንም አይጎዳቸውም፤እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በሐቅ ላይ ግልጽ ሆነው ይቀጥላሉ!”
(አቡየዕላ ዘግበውታል)
✍️ Seyfel Islam AlHabeshi
https://t.me/Seyfel_Islam
Telegram: View @Seyfel_Islam

Telegram: View @Seyfel_Islam

قال ابن تيمية -رحمه الله-: {قوام الدين كتاب يهدي وسيف ينصر وكفى بربك هادياونصيرا} مجموع الفتاوى [10/13] ሙስሊሞችን ለሚመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች ቤተሰብ ይሁኑን
Send as a message
Share on my page
Share in the group