Translation is not possible.
🌙 ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ሙስሊም ጀግኖች እና ለወላጆች!
ትምህርትን በኢማን እና በትጋት ወደ ስኬት 🚀
ውድ ልጆቻችን እና ወላጆች! አሁን እየተፈተናችሁት ላለው ሞዴል ፈተና፣ ለመጪዎቹ ተከታታይ ልምምዶች እና ለዋናው የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በሙሉ ልብና በተረጋጋ መንፈስ ለመዘጋጀት እነዚህን ነጥቦች ልብ ልንል ይገባል! ፈተና የዱንያ (የዚህ ዓለም) መለኪያ እንጂ የሁለንተናችን መመዘኛ አለመሆኑን በመረዳት አላህ ከኛ ጋር ነው! በሚል ጠንካራ እምነት እንዘጋጅ።
👦👧 ክፍል 1፡ ለጀግና ተማሪዎቻችን
1. ተወኩል (በአላህ መመካት) እና ትጋት
አሁን ያሉት ሞዴል ፈተናዎች ስህተታችሁን የምታውቁበት እና ራሳችሁን ለዋናው ፈተና የምታሻሽሉበት ትልቅ እድል መሆኑን አትርሱ።
✅ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- "የሚቻላችሁን አድርጉ፤ እኔም እረዳችኋለሁ።" እናንተ ትጉ፣ አላህ (ሱ.ወ) ደግሞ በረካውን (በረከቱን) ይጨምራል።
✅ ዱዓ (ፀሎት) የመሳሪያችሁ መሳሪያ ነው። ሁሌም አላህን ለእውቀት ብርሃንና ለስኬት ለምኑት።
2. ቂም የለሽ ልብ ለዒልም (እውቀት) ብርሃን
✅ ከጓደኛም ሆነ ከሌላ ሰው ጋር ያለባችሁን አለመግባባት ወይም ቅሬታ ይቅር ተባባሉ። ልብን ከጥላቻ ማጽዳት ለአእምሮ ሰላምን ይሰጣል።
3. በኢስላማዊ ስነምግባር (አደብ) ማጥናት
✅ አብራችሁ ስታጠኑም ሆነ ብቻችሁን አላህን መፍራት ዋነኛው መመሪያችሁ ይሁን።
🛑 የመጨረሻ እና ወሳኝ ማስጠንቀቂያ!
ፈተና ላይ ስትቀመጡ በፍጹም መፈፀም የሌለባችሁ አንድ ስህተት አለ!
⭕️ መኮረጅ (ማጭበርበር): ከአላህም ሆነ ከፈተናው አሰጣጥ አንፃር መኮረጅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። በሌላ ተማሪ ስራ መኮረጅ ወይም የፈተና ደንብን መጣስ የሁሉንም የፈተና ውጤት ለመሰረዝ ይዳርጋል። አላህ (ሱ.ወ) በሂደት እንጂ በማጭበርበር የሚመጣን ውጤት በረካውን አይሰጥበትም! በራስ ችሎታ ብቻ ለመስራት ቁርጠኛ ሁኑ!
📝 በሁሉም የፈተና ሳምንታት ልትተገብሩት የሚገቡ ጥንቃቄዎች
✅ ሰላት በወቅቱ: ሰላትን በአግባቡ መፈፀም ነፍስን ያረጋጋል፣ ስሜትን ይቆጣጠራል፣ አእምሮን ያሳርፋል።
✅ ዚክር (የአላህን ማውሳት): ወደ ፈተና ስትሄዱም ሆነ ስትቀመጡ አላህን አስታውሱ።
✅ የእንቅልፍ ሰዓት: ሰውነትና አእምሮ በቂ እረፍት ካላገኙ አያገለግሉምና በጊዜ ተኙ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
👨‍👩‍👧‍👦 ክፍል 2፡ ለውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች
1. ዱዓ እና ብርታት:
◆ የወላጆች ዱዓ ተቀባይነት አለው! ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ልጆቻችሁን በዒልም እንዲያብቁ፣ ልቦናቸውን እንዲከፍትላቸው እና ጭንቀትን እንዲያስወግድላቸው በብዛት ዱዓ አድርጉ።
2. አዎንታዊ ቃላት እና ተስፋ:
◆ "የቻልክውን ያህል ጥረት አድርግ፣ ውጤት የሚሰጠው አላህ ነው" በሏቸው። ትጋታቸውን አድንቁ፣ እንጂ በውጤቱ አትዝለፉ።
መጨረሻው ድል ነው!
አላህ (ሱ.ወ) ትጋታችሁን አይጥልም። በታማኝነትና በሰላም ተፈትናችሁ ስኬትን ተጎናጸፉ!
ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ይርዳችሁ!
ሁሉንም ነገር ያግራላችሁ፤ ለሙስሊሙ ማህበረሰብና ለሁሉም ሰው የሚጠቅም ዕውቀት ይስጣችሁ።
መልካም ፈተና! 🤲✨
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group