Translation is not possible.
ይሄው ለማንም እንደሚታየው ቡርሃኑዲን አልሐለቢይ ማለትም ሲብጡ ኢብኒል ዐጀሚ ራሱ ሀካሪን “ሸይኹል ኢስላም” ብለው ነው የጠሯቸው። ሐሰን ታጁ ይህንንም ቆርጦ አስቀርቶታል። ሰው እንዴት በዚህ ልክ በውሸት ሱስ ናላው ይዞራል! ክፉ ልክፍት!
4ኛ:- ደግሞም “ሐዲሥ በመፈብረክ ተወንጅሏል” ያሉት እሳቸው አይደሉም። ይህም የሐሰን ታጁ ሌላ ቅጥፈት ነው። ታሪክ የሚገልፅ ሰው ጥሩውንም መጥፎውንም የተባለውን ማስፈር ስለነበረባቸው ነው የኢብኑ ነጃርን ንግግር ያሰፈሩት እንጂ እሳቸውማ “ሸይኹል ኢስላም” ነው ያሉት።
#ቅጥፈት_አምስት
“እዚህ ላይ የታዘብኩት ነገር በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ‹‹ሸይኹል ኢስላም›› የሚለዉ ማዕረግ ከዕዉቀትና በስብዕና ጥራት ይልቅ በቡድን ስሜት በዘፈቀደ ሊሰጥ የመቻሉን ነገር ነዉ፡፡”
መልስ፦
1ኛ፦ በዚህ መልኩ የሚወነጅለው ዘሀቢን፣ ኢብኑል ቀዪምን እና አልባኒን ነው። ነገር ግን ሀካሪን “ሸይኹል ኢስላም” እያሉ የጠሩ አስር ዓሊሞችን ዘርዝሬያለሁ። ሁሉም ሐሰን ታጁ የውንጀላ ጣቱን አይሰነዝርባቸውም ብዬ የምገምታቸውን ብቻ ነው ያቀረብኩት። ሰበብ ላለመስጠት ስል እሱ በቡድንተኝነት ስሜት የሚወርፋቸውን ዘሀቢን፣ ኢብኑል ቀዪምን፣ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲን ማካተት አልፈለግኩም።
ሀካሪን ሸይኹል ኢስላም ከማለት በተጨማሪ ኢብኑል ጀዊዚይ፣ ኢብኑ ኸሊካን እና ሌሎችም ኸይራቸውና ዒባዳቸው የበዛ፣ ከአህለሱናህ የሆኑ ሰው ናቸው” እያሉ ገልፀዋቸዋለዋል። [አልሙንተዞም፡ 17/7] [ወፈያት፡ 3/345] እነዚህን ሁሉ በቡድንተኝነት ይወርፋቸው ይሆን?
ማጠቃለያ፦
ሐሰን ታጁ ትናንት በለጠፋት በአንዲት አጭር የፌስቡክ ልጥፍ ስንት ውሸት እንደ ዋሸ ተመልከቱ። ሰው እንዴት በኢስላም ስም እየፃፈ በዚህ ልክ ይቀልላል! በነገራችን ላይ ስራዎቹ በሙሉ እንደዚህ ናቸው። እፍኝ መነሻ ይይዝና ማያያዣውም፣ መዳረሻውም እንዳለ በውሸት የተጥለቀለቀ ድምዳሜ ነው የሚሰራው። ውሸትን የጠላቶቹ መለያ መታወቂያ ያደረገው ጌታ ጥራት ይገባው ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 30/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor
2/2
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group