Translation is not possible.
#ለወላጆች #መልካም #ስለመዋልና #ዝምድናን #ስለመቀጠል
 
#ክፍል_7
 
አላህ እንዲህ ብሏል፦
“ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቅ፤” (አን-ኒሳእ፡ 1)
 
#ሐዲሥ 40 / 320
 
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ አንድ ሰው (መልዕክተኛውን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፥ “የአላህ መልዕክተኛው ሆይ! ዘመዶች አሉኝ፤ እቀጥላቸዋለሁ፥ ይቆርጡኛል፤ በጐ እውልላቸዋለሁ፥ ክፉ ይውሉብኛል፤ እታገሳቸዋለሁ፥ መጥፎ ድርጊቶችን ይፈጽሙብኛል” አላቸው። እንዲህ አሉት (መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም))፦ “እንዳልከው ከሆነ፥ ረመጥ እያጐረስካቸው ነው፤ በዚህ (ባሕሪህ) እስከቀጠልክ ድረስ ከአላህ የሆነ ረዳት ከአንተ ጋር ከመሆን አይወገድም።” (ሙስሊም ዘግበውታል)
 
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
 
፨ ክፉ ለሚውል ሰው በጐ መመለስ ጽድቅ ተግባር ነው፤ ምክንያቱም ያ ክፉ የሚውል ሰው ከአድራጐቱ ሊታቀብ ይመቻልና። ያ ካልሆነ ደግሞ ይበልጥ ከአላህ እየራቀ ከመሄድ ውጭ በጐ በዋለው ሰው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት አይኖርም።
 
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
 
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group