~ኢላሂ!… የልቤን ምሥጢር አንተው ታውቃለህ። በሰዎች ዘንድ አስመስል ይሆናል እንጂ አንተ ዘንድ ፈፅሞ አይቻለኝም። እንደማትከለክለኝ ባውቅም ልጠይቅህ አፍራለሁ። የምታውቀው እኔነቴን ላንተ አላስረዳም። አንተን ብቻ ግን እከጅላለሁ። ከእንግዲህ ላንተ ካልሆነ በቀር አንዲትም እንባ እንዳላፈስ እርዳኝ።
• ከ አሁን በፊት ብዙ ነገር ፈልግያለሁ። በፍላጎቴ ውስጥ ግን አንተ አልነበርክምና አንዱም ያገኘሁት አላስደሰተኝም።ኢላሂ… አንተን ብቻ እፈልጋለሁ። መቼ እንደተሰበርኩ፣ ምን እንደሰበረኝ፣ እንዴት እያሳለፍኩ እንደሆነ ካንተ በቀር ማንም አያውቅም። አንተ ካልሆንክ በቀር ማንም አይረዳኝም። ያረሂም… የደካማ ደካማ የሆንኩት ባርያህ ነኝና ውደደኝ። በልቤ ከምከጅለው ነገር ሁሉ አንተ ቅደም።
ያ ረሒም!…ሁሌም መንገድ እስታለሁ። ርቄህ ተውከኝ እያልኩ አንተን እወቅሳለሁ። ደግሞ ሁሉንም አካልዬ መንገድ እንደሌለኝ ሳውቅ መልሼ ወዳንተው እመጣለሁ።ረቢ… ሁለንተናዬን ሁሉ ወዳንተ አድርግልኝ። መረን ካጣች ነፍሴ እየታገልኩ አንተን እናፍቃለሁ። ፀዳሁ እያልኩ እመነችካለሁ። አፅዳኝ። የተገዛሁህ እየመሰለኝ እጅግ አምፅሀለው። እኔን ለእኔ አትተወኝ። ያረቢ ፍፃሜዬ ከጅማሬዬ ይበልጥ የተዋበ አድርግልኝ። ሞቴን ከህይወቴ ይበልጥ አሳምርልኝ። እዝነትህን ከመልካም ስራዬና ከዱዓዬ አስቀድምልኝ። እየተወኩህ አልተውከኝምና እኔን ለእኔ አትተወኝ። ያረቢ አንዳንዴ ብቻ አይደለም ሁሌም አንተን ብቻ የምከጅል አድርገኝ።…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan