Translation is not possible.
በህይዎቴ ጆሮዬ ሰምቶት የማያውቅ ጉድ ላስደምጣችሁ‼
============================
✍️ በወቅታዊ ስሜት ብቻ ተገፋፍቶ መሰረታዊ የዐቂዳህ ልዩነቶችን መዘንጋት ትልቅ ስህተት ነው።
እስኪ የዚህን ሰው ንግግር አዳምጡ፤ ትርጉሙ ለሚቸግራችሁ ያነሳቸውን የጥመት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
√ ዐሊ ፀሐይን በእጁ ይዟል።
√ ዐሊ ፀሐይን ያሽከረክራል።
√ ዐሊ ዓለምን (ከውኑን) ያስተዳድራል።
√ ዐሊ ጌታችን ነው። (ኢናሊላሂ!)
√ ዐሊ የቂያማ ቀን ጌታችን ነው። (ወሏሁ-ል-ሙስተዓን!)
√ በቁርኣን ውስጥ «አላህ» የሚለው ቃል የተፈለገበት ዐሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ነው። (ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ!)
√ በቁርኣን የተጠቀሰችው ትንኝ (በዐውዷ) ዐሊ ነው።
√ "ዳበቱል አርድ" (የምድር እንስሳ) ዐሊ ነው።
√ "በሰማይም በምድርም ውስጥ አምላክ እርሱ ነው" የተባለው ዐሊ ነው። (ይህን ከኢማም አል-ባቂር እንደተላለፈ ይናገራሉ!)
√ «እኔ የምድር ጌታ ነኝ፣ አላህ ደግሞ የሰማይ ጌታ ነው!» (ይህን ኢማም አል-ባቂር እንደተናገረው ያምናሉ!)
√ ዐሊ ገና የ3 ቀን ህፃን እያለ፣ ቁርኣን ከመውረዱ 10 ዓመት በፊት ቁርኣንን ቀርቷል። (ያ አላላላህ!)
ይህ ግልፅ የሆነ ሽርክ (ክህደት) ነው። እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች ግልፅ የሆነ ሽርክ (በአላህ ማጋራት) እና ኩፍር (ክህደት) ናቸው። የአላህን ጌትነት (ሩቡቢያ) እና መለኮታዊ ባህሪያት (ኡሉሂያ) ለፍጡር ለሆነው ዐሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና) መስጠት ነው። ዐሊ ራሳቸው ከዚህ የጥመት እምነት ንፁህ ናቸው።
ብዙዎች ሰሞኑን ሺዓዎችን እየደገፉ ያሉት ሲከራከሩ «ሁሉም እንደዚህ አይደሉም!፣ ጠማማዎቹ ብቻ ናቸው» ይላሉ።
ነገር ግን የሺዓህ ዐቂዳህ መሰረቱ በራሱ የተበላሸ ነው። ኢማሞቻቸው ከስህተት የፀዱ (መዕሱም) ናቸው ብሎ ማመን፣ ለነብያት የሚገቡ ደረጃዎችን መስጠት፣ የነብዩን ﷺ ምርጥ ባልደረቦች (አቡበክርን፣ ዑመርን፣ ዑሥማንን) መርገምና ማክፈር የብዙሃን ሺዓዎች የጋራ እምነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው አይነት ከባድ ጥመት የሚፈልቀው ከዚሁ ከተበላሸ መሰረት ነው።
ልብ በሉ! የፖለቲካ አቋም ዐቂዳን አይለውጥም‼ ኢራን ከእስራኤል ጋር መዋጋቷ ወይም «ፍልስጤምን እደግፋለሁ!» ማለቷ የዐቂዳህ ጥመቷን ትክክል አያደርገውም። የአንድን ቡድን መሰረታዊ የኃይማኖት ጥመት እያወቅን በፖለቲካ አቋሙ ብቻ ልንደግፈውና ልናሞግሰው አይገባም። ይህ በእውቀት ላይ ሳይሆን በስሜት ላይ የተመሰረተ አቋም መሆኑን ያሳያል።
አቋማችን ግልፅ ሊሆን ይገባል።
ወራሪዋን እስራኤልን በበደሏና በወረራዋ እንቃወማለን፣ ከምድረ ገፅ ትጠፋ ዘንድም ምኞታችን ነው።
በተመሳሳይ መልኩ፣ ሽርክና ኩፍር ላይ የተመሰረተውን የሺዓዎችን የዐቂዳህ ጥመትም አጥብቀን እንቃወማለን።
የአንዱ ጥፋት የሌላውን ጥመት ትክክል አያደርገውም። ምኞታችንም አላህ እስራኤልን ያስልማት ወይም ከምድረ ገፅ ያጥፋልን፤ የኢራንንም ህዝብ ከዚህ ጠማማ የሺዓህ አስተሳሰብ አውጥቶ ወደ ትክክለኛው የሱብና መንገድ ይመልስልን፤ በትክክለኛ ሸሪዓህና በትክክለኛ ሙስሊሞች የምትመራ ያድርግልን።
||
t.me/MuradTadesse
3 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group