Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
 
#ክፍል_19
 
#ሐዲሥ 13 / 135
 
የአላህ መልዕከተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን መናገራቸውን ጃቢር (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል፦ “አንድ ሙስሊም አትክልት ቢተክል፥ (በሰው ወይም በእንስሳ) የተበላበት፥ የተሰረቀው የተቀነሰበት ሁሉ ሶደቃ ይሆንለታል፡፡" (ሙስሊም ዘግበውታል)
ሌላ ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ ደግሞ፦ “አንድ ሙስሊም አትክልት ተክሎ፥ ዘር ዘርቶ ሰው፣ እንስሳ ወይም ሌላ ነገር (ከምርቱ) ከተመገበለት ሶደቃ ይሆንለታል" ማለታቸው ተወስቷል። ሁለቱም ዘገባዎች በአነስ (ረ.ዐ)
የተላለፉ ናቸው።
 
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገር
 
1/ አትክልትን መትከልና ዘርን መዝራት ያበረታታል። ትሩፋቱንም ይገልጻል። ይህ ተግባር ሰውየው በመሞቱ ምንዳቸው ከማይቋረጥ መልካም ተግባራት ውስጥ አንዱ ነው።
2/ የአላህን ፍጡራን ጥቅምና ምኞት ማስጠበቅ፥ ጉዳያቸውን መፈጸም ከጽድቅ ተግባራት ይካተታል።
3/ ሙስሊም በተሰረቀው ወይም በተቀማው ገንዘብ፥ ትዕግስት ካደረገ፥ ምንዳን ያገኛል፡፡
 
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
 
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group