Translation is not possible.
አንድ ሰው ነብኑን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰልም) አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጌታዬን እንዴት አድርጌ ልጠይቀው (ልማፀነው)? ብሎ ሲጠይቃቸው እንዲህ በል አሉት፦
 
“አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝ፣ ጤነኛ አድርገኝ፣ ሲሳይን ለግሰኝ”!!
 
▲ ይህ የዱንያና የአኺራ ጉዳዮችን ላንተ ጠቅልሎ ይዞልሃል።
 
#ሙስሊም_ዘግበውታል
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እናም ተማሪዎች አርአያችን የአላህን መልዕክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰልም) ናቸውና እኛም ሁሌም ይህንን ዱዓ እናድርግ። ጌታችንን ተናንሰን እንማፀነው‼️
 
 
ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር:-
 
እኛ ጥረት እያደረግንም ሆነ ጥረት ካደረግን በኋላ መመካት ያለብን በጥረታችን ((በልፋታችን)) ሳይሆን በአላህ ነው። በአላህ በመመካት እሱ (አላህ) እንዲያሳካልን ሁሌም ልንለምነው ይገባል። «በአላህ ፍቃድ ይሳካልኛል፣ ጥሩ ውጤት አመጣለሁ» በማለት ንባባችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን‼️
 
 
 
⭕️ አደራችሁን መልዕክቱን ለሁሉም ተማሪዎች አድርሱልኝ።
 
✍️ በናተው ወንድም ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group