Translation is not possible.
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
#ከጀግኖቹ ጀርባ እነማን ነበሩ? 1
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
#የሙሐመድ_አልፋቲህ እናት ዘወትር ማለዳ እጁን አጥብቃ ጨብጣ ረዥም ርቀቶችን ተጉዛ የቆስጠንጢኒያን አጥሮች እያሳየችው "ልጄ ሆይ! የቆስጠንጢኒያ አጥር ይታይሀል ያ እሱ ነው አዎ ያ የቆስጠንጢኒያ አጥር ነው ድል አድርገህ የምትከፍተውም አንተ ነህ" እያለች ግብና ዓላማውን ከፍ አድርጎ እንዲያስብ አድርጋ ኮትኩታ አሳደገችው።
እሱም አላሳፈራትም።
ይህቺን ከተማ ለመክፈት 23 ጊዜ የሙስሊሞች ሠራዊት ዘመተ። ግና እጅግ ጠንካራ በሆኑ ግንቦች እና በጣም በሰለጠኑ የሮም ባይዛንታይን ወታደሮች የምትጠበቀውን የምስራቅ ሮማ ዋና ከተማ ኮንስታንትኖፕልን መክፈት አንዳቸውም አልተሳካላቸውም ነበር።
#በ12 ዓመቱ የዑስማኒያን ኺላፋ ሥልጣን የተረከበው ተዓምረኛው ሙሐመድ አልፋቲህ ባይዛንታይኖች ቆስጠንጢኒያን ለመከላከል ባህሩን በሰንሰለት ባጠሩት ጊዜ 70 መርከቦች ተሰርተው በየብስ ተጎትተው #golden Hore ወደተሰኘው ከተማ እንዲገቡ አዘዘ። በዚህ ጊዜ እንዴት ይህ ይቻላል እንዴት መርከብ በየብስ ላይ ይጓዛል?! በማለት የጦር መሪዎቹ ጥያቄ አነሱ። ሙሐመድ አልፋቲህም እንዲህ አለ:- "#የመቻል_ጥግ_እስከየት_እንደሆነ_ለማየት_የማይቻለውን_መሞከር_አለባችሁ_እናቴ_በዓላማ_ፅናት_ላይ_አንፃ_አሳድጋኛለችና\\"
#በአልፋቲህ ድል አድራጊነት ቆስጠንጢኒያ ተከፍታ የዓለም ኃያልነት በሙስሊሞቹ ኺላፋ በኦቶማን እጅ ሙሉ ለሙሉ ገባ። ከዚያ በኋላ ምስራቅ እና ደቡብ አውሮፓ በሙሉ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር ዋሉ።
#ሙሐመድ አልፋቲህ ይህን ሁሉ ገድል ሲፈፅም #ዕድሜው 21 ነበር። እርሱ በዚያ ለጋ እድሜው ከዓለማችን የምንጊዜም ኃያል መሪዎች ውስጥ
አንዱ ለመሆን በቃ።
አላህ ይተካቸው
Send as a message
Share on my page
Share in the group