Translation is not possible.
ከትዳር በፊት ፍቅር የለም ብዬ የኸዲጃን ፍቅር ገደል አልከተውም… ምክንያቱ ምንም ይሁን አፍቅራ እንዳገባቻቸው አልጠራጠርም… በሪራ በሚሏት ሰሓቢት ፍቅር ተለክፎ በመዲና መንገዶች ላይ ከኋላዋ እየተከተለ… የእንባ ቋንጣውን በመዲና አድማስ ሲወረውር የነበረውን ሰሓባው ሙጊስ … አፍቃሪ አልነበርክም ልለው አልችልም… ቀድመው ቢለያዩና ከዚያ በኋላ ባያገባትም “ሙጊስ ለበሪራ ባለው ፍቅር፣ በሪራ ደግሞ ለሙግስ ባላት ጥላቻ አልተገረምክም ወይ” የተባለለት አፍቃሪ ነው… ያውም በረሱል አንደበት።
 
አንድ ነገር ግን አምናለሁ… ፍቅር በስሙ የሚደረጉ ኃጥያቶችን እንደማያውቃቸውና የአፍቃሪ መድሀኒቱም ትዳር እንደሆነ… ማንነትህን ፣ እምነትህንና ጉዞህን የሚያመክንብህ ከሆነ በሽታ እንደሆነ… አምናለሁ። ነብይህ “ለተዋደዱ ሰዎች ከኒካህ ውጪ (አማራጭ) አላየሁም” ሲሉም… ከትዳር በፊት መዋደድ እንዳለና ኒካህ ካልታከለበት ግን የኪሳራ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ነው… አፍቅርሃል? በበር በኩል ና በቃ … በፍቅር ስም ሙድ አትያዝ!!
t.me/abdu_rheman_aman
Send as a message
Share on my page
Share in the group