#ትዕግሥት (#ሶብር)
#ክፍል_18
#ሐዲሥ 3 / 42
ኢብኑ መስዑድ እንዳስተላለፉት፦ የሑነይን ዘመቻ ዕለት ነበር። የአላህ መልዕክተኛ በምርኮ አከፋፈል ላይ ለተወሰኑ ሰዎች ከሌሎች ብልጫ ያለው ድርሻ ሰጡ። ለአረዕ ኢብኑ ሐቢብ መቶ ግመሎችን ለገሡ። ለዐየነህ ኢብኑ ሒሰንም እንዲሁ። ከዐረብ ታላላቅ ሰዎች ለተወሰኑትም ድርሻቸውን ሰጡ። በጊዜው ከሌሎች ብልጫ ያለው ድርሻ ነበር የሰጧቸው። \"በእውነቱ ይህ ክፍፍል ፍትህ የጎደለውና የአላህ ውዴታ ያልተከጀለበት ክፍፍል ነው\" ሲል አንድ ሰው ተናገረ። \"በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ቃልህን ለአላህ መልዕክተኛ እነግራቸዋለሁ\" አልኩት። እርሳቸው ዘንድ በመቅረብ ያለውን ነገርኳቸው። ፊታቸው ተለዋወጠ። ፍም መሰለ። \"አላህና መልዕክተኛው ፍትሃው ካልሆኑ ማን ነው ፍትሃዊ ሊሆን የሚችለው?\" ካሉ በኋላ፥ \"ለሙሳ አላህ ይዘንለት። ከዚህ ይበልጥ መከራ ደርሶበት በትዕግስት አሳልፎታል።\" አሉ። \"ከእንግዲህ እንዲህ ዓይነቱን ወሬ አላደርስላቸውም\" አልኩ። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ለአላህ፣ ለመልዕክተኛውና ለሙእሚኖች ታማኝ ሆኖ መገኘት።
2/ ምግባረ ብልሹነትንና ጥፋትን በይቅርታ ማለፍ የነቢያት ባሕሪ ነው።
3/ መልዕክተኛ የሰዎችን ልቦናዎች ለማዋሃድና ለማጣጣም ይጠቀሙበት የነበረውን ጥበብ የተሞላበት ስልትና ትዕግስታቸውን ይህ ዘገባ በጉልህ ያሳያል።
4/ መልዕክተኛ የነቢያት ወንድሞቻቸውን አርአያነት መከተላቸው።
5/ መልዕክተኛ ሰው እንደመሆናቸው ሰዎች የሚሰማቸው የደስታ፣ የሐዘን ወዘተ.. ስሜቶች ይሰሟቸዋል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1