#ትዕግሥት (#ሶብር)
#ክፍል_14
#ሐዲሥ 3 / 38
ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ -ከነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ ገባሁ፤ አሟቸው ነበር ልጠይቃቸው። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከፍተኛ የህመም ስሜት ይሰማዎታል?” አልኳቸው። “አዎ! ከናንተ ሁለት ሰዎች የሚሰማቸውን ያህል የህመም ስሜት ይሰማኛል” አሉ። “ይህ ማለት እርስዎ እጥፍ ምንዳ ያገኛሉ ማለት ይሆን? በማለት ጠየቅኳቸው። “አዎ! ነገሩ እንዲያ ነው። እሾህም ትሁን ከዚያ በላይ የሆነ አዋኪ ነገር የሚያገኘው አንድም ሙስሊም የለም፡ አላህ በርሷ (ሰበብ) ወንጀሉን ያበሰለት፤ ከዛፍ ላይ ቅጠል እንደሚረግፍ ሁሉ ኃጢአቱ የተራገፈለት ቢሆን እንጅ” በማለት ተናገሩ። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ አንዳች ችግር በሚያጋጥም ወቅት ትዕግሥት ከታከለበት ምንዳ እንደሚያስገኝ።
2/ ከሰው ሁሉ ይበልጥ ፈተናና ችግር የሚደርስባቸው ነቢያት ናቸው። ምክንያቱም እነርሱ ከማንም የላቀ የትዕግስት ችሎታና ጽናት አላቸውና። አላህም ለሰው ዘር አርአያ አድርጓቸዋል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1