#ተውበት (#ጸጸት)
#ክፍል_6
#ሐዲሥ 12/ 18
አቡ ዐብዱረሕማን ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑ አል ኸጧብ እንዳስተላለፉት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦ \"የክብርና የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ አንድ ሰው በሞት አፋፍ ላይ እስካልሆነ ድረስ ተውበቱን (ንስሃውን) ይቀበላል።\" (ቲርሚዚይ ዘግበውታል፥ ሐዲሡ \'\'ሐሰን\'\' ነውም ብለዋል)
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ አንድ ሰው የሚሞትበት የመጨረሻ ቁርጥ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ተውበት (ንስሃ) ማድረጉ ከተውበት መስፈርቶች አንዱ ነው።
(1) ሐሰን፦ በቀጥተኛ የዐረበኛ ቋንቋ ትርጓሜው ጥሩ ወይም መልካም ማለት ነው። በሥነ ሐዲሥ (በነቢዩ ሐዲሥ ጥናት) ሙያዊ ትርጓሜው ከአላህ መልዕክተኛ በቀጥታ ከሶሓባው (ሐዲሡን ካስተላለፈው) የተመዘገበ ዘጋቢዎቹ (አስተላላፊዎቹ) በመጥፎ ወይም በሐሰት የማይወነጀሉ ሐዲሡም ከሐሰት የጠራ ነገር ግን \"በጣም ትክክል\" (ሶሒሕ) ተብሎ ከሚጠራው ትንሽ ዝቅ ያለ የሐዲሥ ዓይነት ነው። (አርታኢው)
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1