Translation is not possible.

#ተውበት (#ጸጸት)

#ክፍል_3

#ሐዲሥ 12 / 15

የአላህ መልዕክተኛ አገልጋይ አቡ ሐምዛህ አነስ ኢብኑ ማሊክ መልዕክተኛው እንዲህ ሲሉ መናገራቸውን አስተላለፈዋል፦ \"ከእናንተ አንዳችሁ ምድረ በዳ መሬት ላይ ያጣትን ግመሉን በድንገት ሲያገኝ ከሚሰማው ደስታ የበለጠ አላህ በባሪያው ተውበት ንስሃ ይረካል።\" (ቡኻሪና ሙስሊም)

በሌላ ዘገባ ደግሞ በሚከተለው መልኩ ተወስቷል፦

\"ከእናንተ አንዳችሁ ምድረ በዳ መሬት ላይ ከግመሉ ላይ ነበር። አመለጠችው። ምግቡንም፥ መጠጡንም እንደያዘች። እንደማያገኛት ተስፋ ቆርጦ ከአንዲት ዛፍ ሥር ተደገፈ፤ ከጥላዋ ተጠለለ። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ላይ እያለ ግመሉ ከፊት ለፊቱ ቆማ አገኛት _በድንገት። ልጓሟን ያዘና ከደስታ ብዛት እንዲህ አለ፦ \"አላህ ሆይ! አንተ ባሪያዬ ነህ፤ እኔ ደግሞ ጌታህ ነኝ።\" ከደስታ ብዛት ስህተት ፈፀመ። አላህ በባሪያው ተውበት ከዚህ ሰው ደስታ ይበልጥ እርካታ ይሰማዋል።\"

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አላህ የባሮቹን ተውበት በመቀበል ምን ያህል ለነርሱ ፍቅርና ርኅራኄ እንዳለው ይህ ዘገባ ያመለክታል።

2/ ይህ ዘገባ ለተውበት ያነሳሳል።

3/ አንድን ነገር ይበልጥ ለማብራራትና ግልጽ ለማድረግ ምሳሌዎችን እየጠቀሱ ማስተማር ከነቢዩ የማስተማር ስልቶች አንዱ ነው።

4/ አንድን ነገር በአጽንኦት ለመግለጽና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ መሐላ መፈፀም ይፈቀዳል።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group