Translation is not possible.

بسم الله الرحمن الرحم

❓❓❓ስለ አያመል ቢድ ያውቃሉ?

👉አያመል ቢድ ማለት በሁሉም ወራት ጨረቃ የሚያበራበትና ሙሉ የሚሆንባቸው በአረቦች አቆጣጠር 13፣14 እና 15ኛ ቀኖች ናቸው።

📚አብዱልመሊክ ኢብኑ ቁዳማ ኢብኑ ሚልሃን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት አባቱ (ረዐ) እንዳሉት:-‘የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በብሩህ ሌሊቶች (ሶስት) ቀናት እንድንፆም ያዙን ነበር(አያመል ቢድ)። 13ኛው፣ 14ኛው እና 15ኛው [በጨረቃ ወር]። [ናሳኢ]

ስለ አያመል ቢድ ማብራሪያ

https://www.facebook.com/share..../v/18M9f5GLNB/?mibex

🎁እነዚህን ቀናቶች ከፆምን ወሩን ሙሉ እንደፆምን ይቆጠርልናል::ይህንንም በየወሩ ከተገበርን ዓመቱን ሙሉ እንደመፆም ይሆንልናል:: ምክንያቱም እያንዳንዱ መልካም ስራ በ10 የሚባዛ በመሆኑ ነው::

⚡️ከላይ ካሉት ሀዲሶች እንደምንረዳው በወር 3 ቀን መፆም እጅግ ወሳኝ ሱና ነው:: ሊያመልጠን አይገባም:: እስከዛሬ ይህን አጅር የማግኘት እድሉ ካልገጠመን አሁን ልንጠቀምበት እንችላለን::

የዚህኛው ወር የአሁኑ ጁመዐ የሚጀምር ይሆናል::

سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ ، أَشْهَدُ أَنْ لا إِلَهَ إِلا أَنْتَ ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتُوبُ إِلَيْكَ

Send as a message
Share on my page
Share in the group