#አላህ_ጀነት_ውስጥ_ለአማኞች_ያዘጋጀላቸው_ጸጋዎች
#ክፍል_4
#ሐዲሥ 372 / 1883
ሙጊርት ኢብኑ ሹዕባህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ \"ሙሳ አምላካቸውን፦ \'ከጀነት ሰዎች የመጨረሻ ዝቅተኛ የሆነው ሰው የሚያገኘው ደረጃ እንዴት ዓይነት ነው?\' በማለት ጠየቁ። አላህም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ \'ይህ ሰው፥ ሰዎች ሁሉ ጀነት ገብተው ከጨረሱ በኋላ የሚመጣው ነው። \'ወደ ጀነት ግባ\' ይባላል። \'ጌታዬ ሆይ! ሁሉም ሰዎች ማረፊያቸውን በያዙበት ሰዓት፣ የየድርሻቸውንም በወሰዱበት ሁኔታ እንዴት እገባለሁ?\' ይላል። \'በምድረ ዓለም ውስጥ አንድ ንጉሥ የነበረውን ያህል ግዛት እንዲኖርህ ትፈልጋለህን?\' ይባላል። \'ጌታዬ ሆይ! እፈልጋለሁ\' ይላል። \'እርሱን እና እርሱን የሚያክል ሌላ ተሰጥቶሃል\' ይባላል። በአምስተኛው \'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ\' ይላል። እስከሁን የተሰጠህን አሥር እጥፍ ታክሎልሃል። ነፍስህ የፈለገችው፣ ዓይኖችህን የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ይሰጡሃል\' ይባላል። \'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ\' ይላል። ሙሳም፦ \'ከፍተኛ ቦታ ያለው ሰው የሚያገኘው ደረጃስ?\' በማለት ጠየቁ። አላህም ሲመለስ፦ \'የነርሱን ልዕልና በእጄ ሠራሁት፣ አሸግኩትም። (የሚጠብቃቸውን ድሎት) ዓይኖች አላዩትም፣ ጆሮዎችም አልሰሙትም፤ የሰዎች ልቦናዎችም አስበውት አያውቁም\' ይላል።\" (ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ የአላህ ችሮታ ስፋት። የጀነት የመጨረሻ ደረጃ ያለው ሰው የሚያገኘው ጸጋ ስፋትና ብዛት።
2/ ጀነት ውስጥ የተለያዩ እርከኖችና ደረጃዎች መኖራቸው።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
ሙጊርት ኢብኑ ሹዕባህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ "ሙሳ አምላካቸውን፦ 'ከጀነት ሰዎች የመጨረሻ ዝቅተኛ የሆነው ሰው የሚያገኘው ደረጃ እንዴት ዓይነት ነው?' በማለት ጠየቁ። አላህም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ 'ይህ ሰው፥ ሰዎች ሁሉ ጀነት ገብተው ከጨረሱ በኋላ የሚመጣው ነው። 'ወደ ጀነት ግባ' ይባላል። 'ጌታዬ ሆይ! ሁሉም ሰዎች ማረፊያቸውን በያዙበት ሰዓት፣ የየድርሻቸውንም በወሰዱበት ሁኔታ እንዴት እገባለሁ?' ይላል። 'በምድረ ዓለም ውስጥ አንድ ንጉሥ የነበረውን ያህል ግዛት እንዲኖርህ ትፈልጋለህን?' ይባላል። 'ጌታዬ ሆይ! እፈልጋለሁ' ይላል። 'እርሱን እና እርሱን የሚያክል ሌላ ተሰጥቶሃል' ይባላል። በአምስተኛው 'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ' ይላል። እስከሁን የተሰጠህን አሥር እጥፍ ታክሎልሃል። ነፍስህ የፈለገችው፣ ዓይኖችህን የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ይሰጡሃል' ይባላል። 'አምላኬ ሆይ! ተስማምቻለሁ' ይላል። ሙሳም፦ 'ከፍተኛ ቦታ ያለው ሰው የሚያገኘው ደረጃስ?' በማለት ጠየቁ። አላህም ሲመለስ፦ 'የነርሱን ልዕልና በእጄ ሠራሁት፣ አሸግኩትም። (የሚጠብቃቸውን ድሎት) ዓይኖች አላዩትም፣ ጆሮዎችም አልሰሙትም፤ የሰዎች ልቦናዎችም አስበውት አያውቁም' ይላል።" (ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ የአላህ ችሮታ ስፋት። የጀነት የመጨረሻ ደረጃ ያለው ሰው የሚያገኘው ጸጋ ስፋትና ብዛት።
2/ ጀነት ውስጥ የተለያዩ እርከኖችና ደረጃዎች መኖራቸው።
Umma Life
ቴሌግራም/ telegram/